news

ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ተናፋቂዋ ጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ ስትውል የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ይዛላችሁ ትቀርባለች፡፡ ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ዘገባዋ ነገ ምንን ይዛ በመውጣት ታስነብቦት ይሆን? -በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሃቅ በላይ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከሆኑት አቶ ጳውሎስ ተሰማ ጋር በወቅታዊው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔዎች እና ከሃላፊነታቸው በመነሳታቸው ዙሪያ ረዘም ያለ የቃለ-ምልልስ ቆይታን አድርጎላቸው ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በነገው ሀትሪክ ላይ ምን ብለው ይሆን ?

ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ
በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ተናፋቂዋ ጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ ስትውል የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ይዛላችሁ ትቀርባለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ዘገባዋ ነገ ምንን ይዛ በመውጣት ታስነብቦት ይሆን?
-በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሃቅ በላይ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከሆኑት አቶ ጳውሎስ ተሰማ ጋር በወቅታዊው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔዎች እና ከሃላፊነታቸው በመነሳታቸው ዙሪያ ረዘም ያለ የቃለ-ምልልስ ቆይታን አድርጎላቸው ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በነገው ሀትሪክ ላይ ምን ብለው ይሆን ?
“የእኛ ስንብት የዲስፕሊን ኮሚቴውና ፌዴሬሽኑ
በአንድ ሳምባ እንደሚተነፍሱ ያረጋገጠ ነው” ሲሉ ለሌሎችም ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽን ሰጥተዋል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ሌላ ዘገባዋ ነገ የምታስነብቦት በፀጥታ ስጋት ምክንያት በተደጋጋሚ ጊዜ ሳይካሄድ ስለቀረው እና ነገ ሊጫወቱ ቀጠሮ ስለተያዘለት ኢትዮጵያ ቡናና መቐለ 70 እንደርታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ስለሚያደርጉትም ጨዋታ ነው፤ በግጥሚያው ዙሪያ የኢትዮጵያ ቡናው አማኑኤል ዮሃንስ እና የመቐለ 70 እንደርታው አሚን ነስሩ ምን ብለው ይሆን ከጋዜጣው አጠቃላይ ዘገባውን ታነቡታላችሁ፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዋስ ነገ ምን ታስነብቦታለች፡፡
ከእነዚህ መካከል ስላልተረጋጋው አርሰናል፤ ስለ ሄዲን ሀዛርድ “እኔ ጋላክቲኮ አይደለውም ስለማለቱና በነጩ ቤት ታሪክ መስራት እፈልጋለው ስለማለቱ እንዲሁም ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ፈራሚ ዳንኤል ጀምስ የሚያነቡትና የሚወዱት ዘገባ ይቀርብሎታል፡፡ የነገዋ ሀትሪክ አታምልጦት ከዛ ውጪም ሌሎች ያልተሰሙ ዘገባዎችን ሀትሪክ ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡
የሀትሪክን ትኩስ የሆኑ መረጃዎቿን ከጋዜጣዋ በተጨማሪ በርካታ ተከታታዮች ባሏት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ላይም ያገኛሉ። ይጎብኙን፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡

ሀትሪክ በነገው እትም ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እለት በገበያ ላይ ስትውል የሚከተሉትን ጉዳዮች ይዛ በመውጣት ለንባብ ትበቃለች፡፡

ሀትሪክ በነገው እትም
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እለት በገበያ ላይ ስትውል የሚከተሉትን ጉዳዮች ይዛ በመውጣት ለንባብ ትበቃለች፡፡ ሀትሪክ በሀገር ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነት ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ “መቐለ 70 እንደርታ የክቡር ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ወኪል አይደለም፤
በርሳቸው አሳቦ እኛን መሳደብና መደብደብም ተገቢ አይደለም…”
ሉን የሚከፋን ተዋጊዎች ስላልሆንን ነው፤ የፖለቲካ
ሰዎች አይደለንም በዚህ አትጥሩን እኛ የስፖርት ሰዎች ነን”
“የመቐለ ህዝብ የራሱን ክለብ እስኪያገኝ ድረስ የቡና ደጋፊ ነበር…” በሚል የክለቡ እግር ኳስ ስራ አስኪያዥ ከሀትሪክ ጋዜጣ የቀረበላቸውን ድፍረት የተሞላበት ጥያቄ እሳኛውም በድፍረት የመለሱ ሲሆን ከዛ ውጪምይቀጥላል”
በአስቸኳይ የተጠራው የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ
በፕሬዝዳንቱ ኢሳያስ ጅራ ትዕዛዝ አዘል ንግግር ስለመጠናቀቁ እና የተቋረጠው ሊግ ሊጀመር ስለመሆኑ ታስነብቦታለች፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋም ክሪስ ስሞሊንግ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ኦልድትራፎርድ ላይ የሚያደረጉት ጨዋታ እየናፈቀው ስለመሆኑ የሪያል ማድሪዱ አዲሱ ፈራሚ ስለሆነው ሄዲን አዛርድን ሌሎችም ዘገባ አላት፤ የነገዋ ሀትሪክ አታምልጦት ከዛ ውጪም ሌሎች ያልተሰሙ ዘገባዎችን ሀትሪክ ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡
የሀትሪክን ትኩስ የሆኑ መረጃዎቿን ከጋዜጣዋ በተጨማሪ በርካታ ተከታታዮች ባሏት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ላይም ያገኛሉ። ይጎብኙን፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ድሬዳዋ ከተማ ላይ ቅጣት አስተላለፈ

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ የድሬዳዋ ከተማ አለአግባብ ከስራ አሰናብቶናል በማለት ጉዳያቸው እንዲታይላቸው አቤቱታቸውን ላቀረቡት ዮናታን ከበደ ወሰኑ ማዜ እና ሀይሌ እሸቱ የሚከተሉትን ውሳኔ ወስኗል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ ተጨዋቾቹ ባቀረቡት አቤቱታ የወሰነላቸው ውሳኔ ድሬዳዋ ልጆቹ ላይ ያሳለፈው የስንብት ውሳኔ እንዲሻር የግልግል ኮሚቴ በማቋቋም ጉዳዮ ን በሰላም መፍታት እንዲቻል እስካሁን የተቋረጠው የተጨዋቾች ደመወዝ በ10 ቀን ውስጥ እንዲከፈልና ክፍያው የማይፈጸም ከሆነ ከፌዴሬሽኑ ምንም አይነት ግልጋሎት ክለቡ የማያገኝ መሆኑ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል።


አፍሪካ | ካፍ ለግብፁ አፍሪካ ዋንጫ ከኢትዮጵያ ሁለት ዳኞችን መመረጡ በይፋዊ ገፁ አስታወቀ

 

ከሳምንታት በኃላ በሚጀመረው የ2019 አፍሪካ ዋንጫ ከኢትዮጵያ ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ እና ረዳት ዳኛ ሳሙኤል ተመሰገን ውድድሩን እንደሚመሩ የመጨረሻውን የዳኞች ዝርዝር ይፋ በማድረግ አስታውቋል።

 

የአፍሪካን አህጉር በዋናነት እሚመራው ካፍ ፣ በዋና ዳኝነት 26 ዳኞች እንዲሁም በረዳት ዳኘነት 30 ዳኞች በግብፅ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ትልቁን ወድድር እንደሚመሩ ተገልጿል።

ለህትመት ሰኞ ዕለት ማተሚያ ቤት የገባችው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1440ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለች በበዓሉ ምክንያት የእዚህ ሳምንት እትሟን በነገው ዕለት በገበያ ላይ ታውላለች፡፡

ለህትመት ሰኞ ዕለት ማተሚያ ቤት የገባችው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1440ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለች በበዓሉ ምክንያት የእዚህ ሳምንት እትሟን በነገው ዕለት በገበያ ላይ
ታውላለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ለገበያ ነገ ስትበቃም ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን? በሀገር ውስጥ ዘገባዋ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን አስመልክቶ ሊጉን ከሚመራው የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ተጨዋቾች መካከል ስለክለባቸው ውጤታማነት እና ሌሎችን ጉዳዮች በማንሳት ጠንካራ ተጨዋቻቸውን ሽመክት ጉግሳን በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግረነው ምላሽን ሰጥቷል፤ ሀትሪክ ከዛ ውጪ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እሁድ ዕለት መካሄድ ስለነበረበት እና ሳይካሄድ ስለቀረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኢትዮጵያ ቡናና የመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታና ግጥሚያው አዳማ ላይ በዝግ ስታድየም ይካሄዳል ስለመባሉና ቡና ስለሰጠው መልስ እንደዚሁም ደግሞ እየተባባሰ ስለመጣው የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ዙሪያ ዘገባ አላት፡፡
ሀትሪክ ሌላው ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የሲዳማ ቡናውን አሰልጣኝ ዘርኃይ ሙሉን በተጨዋችነት ዘመኑ ስለነበረው የስፖርት ህይወት፣ ስለስልጠና ዘመኑ፣ በአሁን ሰዓት ስላለው ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ችግሮች እንዲሁም ሌሎችም ጥያቄዎች ቀርቦለት ለጋዜጣው ምላሹን ሰጥቶበታል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ የነገ ዘገባዋም የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታን አስመልክቶ ስለ ባለ ድሉ ሊቨርፑል እና ስለ ቡድኑ ተጨዋች ሞ.ሳላ እንደዚሁም ደግሞ ቼልሲ በድል ስላጠናቀቀው እና የሀዛርድ ምሽት ስለተባለበት የአውሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ሀትሪክ በጥሩ ዘገባዋ ታስነብቦታለች፡፡
የነገዋ ሀትሪክ አታምልጦት ከዛ ውጪም ሌሎች ያልተሰሙ ዘገባዎችን ሀትሪክ ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡
የሀትሪክን ትኩስ የሆኑ መረጃዎቿን ከጋዜጣዋ በተጨማሪ በርካታ ተከታታዮች ባሏት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ላይም ያገኛሉ። ይጎብኙን፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ስራዎችን በኦንላይን ማስፈፀም እሚያስችለውን መተግበሪያ ድህረ-ገፅ አስመረቀ

 

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከኤ.ዱ.ዩ ኮሚዩኒኬሽን ጋር በመተባበር ዘመናዊ የሆነ ድህረገፅ በመስራት ዛሬ ፕላኔት ሆቴል ላይ ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ አስመርቋል።

 

በኤ.ድ.ዩ ኮሚኒኬሽን የተሰራው የኦንላይን ድህረገፅ የተለያዩ ስራዎችን በቀላሉ ክለቡ እንዲያካሂድ ከማስቻሉ በተጨማሪ የክለቡ የገቢ ምንጭም ይሆናል።ድህረገፁ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የማልያ ሽያጭ፣የስታድየም ትኬት ሽያጭ፣ደጋፊዎች የክለቡ አባል ማድረግ፣የገንዘብ መዋጮ እና ሌሎች ግልጋሎቶችን የሚሰጥ መሆኑን በጋዜጣዊው መግለጫ ላይ ተገልፆል ።

ፋሲል ከነማ ባህርዳር ከተማን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል

 

በ27ኛው ሳምንት እሁድ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአማራ ደርቢ ጨዋታ ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ እና ባህርዳር ከተማ ጨዋታ በፋሲል ከነማ አሸናፊነት ተጠናቋል።ፋሲል ከነማ ወደ ወላይታ ተጉዞ 2-1 ከተሸነፈው ቡድን ምንም አይነት ለውጥ ሳያደርግ ነበር ወደ ሜዳ የገባው በአንጻሩ እንግዳው ቡድን ባህርዳር ከተማ ውልዋሎ ጋር ነጥብ ከጣለው ስብስብ አስናቀ ሞገስ፣ ኤልያስ አህመድ እና ልደቱ ሞላን በ ሳላምላክ ተገኝ፣ ዜናው ፈረደ እና ስነ ጊዮርጊስን ቀይሮ ነበር ወደ ሜዳ የገቡት።

የፋሲል ከነማ ብልጫ በታየበት የመጀመርያ አጋማሽ በ4-3-3 አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት አጼዎቹ በተሻለ መልኩ ወደ ግብ ቀርበዋል።ጨዋታው ገና እንደተጀመረ በሙከራ የታጀበ ነበር። 3ኛው ደቂቃ ላይ ሰአድ ሀሰን በቀኝ መስመር ለኢዙ አዙካ ያሻገረለትን ኳስ ኢዙ አዙካ ተከላካዮችን አታሎ ይዞት በመግባት ወደ ግብ አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ምንተስኖት አሎ የተፋውን ሽመክት ጉግሳ አግኝቶ በ ቴስታ በቀላሉ አስቆጥሮ ፋሲሎች መሪ እንዲሆኑ አስችሉዋል።አጼዎቹ ከጎሎዋ መቆጠር በሁዋላ በተደጋጋሚ የ ባህርዳር ከተማን የጎል መስመር ሲፈትሹ ተስተውለናል፡፡በተለይ ሱራፌል ዳኛቸው 9ኛው ደቂቃ ላይ አክርሮ የመታው ኳስ እና በግቡ አግዳሚ ለጥቂት የወጣው አንዱ አስደንጋጭ ሙከራ ነበር።ረጃጅም ኳሶችን በሁለቱም መስመሮች በኩል ክሮስ እያደረጉ ተጭነው የተጫወቱት ፋሲሎዎች በ 25ተኛው ደቂቃ ላይ አምሳሉ ጥላሁን ከኤፍሬም አለሙ የተቀበለውን በቀጥታ ወደ ጎል ያሻማውን ኳስ የምንተስኖት አሎ ስህተት ተጠቅሞ ሙጅብ ቃሲም በቴስታ መረብ ላይ አሳርፏታል።ከጎሉ መቆጠር በሁዋላ ፋሲሎች በተደጋጋሚ ወደ ጎል ሲሞክሩ ተመልክተናል ሙከራቸውም ተሳክቶላቸው በ 31ደኛው ደቂቃ በእለቱ አስደናቂ ብቃቱን ሲያሳይ የነበርው እና የጨዋታው ኮኮብ ኢዙ አዙካ ከ መሀል ሜዳ የተቀበለውን ኳስ በሚገርም ሁኔታ 5 የጣና ሞገድ ተከላካዮች አታሎ በማለፍ ለፋሲል ሶስተኛዋን ጎል በሚገርም አጨራረስ እና ብቃት አስቆጥሩዋል።በፋሲል መሪነት የመጀመሪያ አጋማሽ ተጠናቁዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ባህርዳር ከተማ ተጫዋቾችን በመቀየር ወደ ጭዋታ ለመመለስ እና ተጭነው ለመጫወት ሞክረዋል፡፡ 69ኛው ደቂቃ ሚካኤል ቬራ ጃኮ አራፋት ከሳጥን ውጭ ያሻገረለትን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ አክርሮ ወደ ጎል የመታው እና ሚካኤል ሳማኪ በ ግሩም ሁኔታ ያወጣበት በጭዋታው ለጣና ሞገድ ብቸኛ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ነበር፡፡ፋሲሎች በአንጻሩ ኳስ ይዘው ለመጫወት ሙከራ ሲያደርጉ አስተውለናል።73ተኛው ደቂቃ ላይ ሙጅብ ቃሲም ከዮሴፍ ዳሙየ ጋር አንድ ሁለት ተጫውቶ በጭዋታው ለእራሱ ሁለተኛውን ለቡድኑ ፋሲል አራተኛውን እንዲሁም በውድድር አመቱ 14 ተኛውን ጎሉን አስቆጥሮ ጭዋታው ተጠናቁዋል።

ጭዋታው ፍጹም ጭዋነት የተሞላበት እና የደጋፊዎች ድባብ በጣም የሚያምር እና ታሪካዊ ጭዋታ ነበር፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 52 በማሳደግ መሪነቱን አጠናካሩዋል በአንጻሩ እንግዳው ቡድን ባህርዳር ከነማ 37 ነጥብ በመያዝ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጡዋል።

ሪፖርተር:ከድር ጀማል
ከ ባህርዳር

ወልዋሎ አዲግራት በመጨረሻ ደቂቃ ላይ በተገኘች ግብ በሜዳው ከመሸነፍ ተርፏል

 

በ27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መቐለ ትግራይ ስታድየም ላይ የተካሄደው የወልዋሎ ና የእዳማ ጨዋታ በእቻ ውጤት ተጠናቋል።ወልዋሎ ባሳለፍነው ሳምንት ባህርዳርን ከገጠመው ስብስብ እንድም ቅያሪ ሳያደርግ ሲቀርብ እዳማ ከተማ ደደቢትን ካሸነፈው ቡድን እዲስ ህንፃን በከንእን ማርክነህ ምኞት ደበበን በተስፋዬ በቀለ ቀይረው ገብተዋል።

ብዙ ሙከራዎች ተመጣጣኝ ፋክክር በታየበት የመጀመርያው 45 በሁለቱም ቡድኖች ጥሩ ሙከራዎችን አሳይቷል።በ4-4-2 እሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት ወልዋሎዎች በፈጣን መልሶ ማጥቃት የግብ ሙከራዎችን መፍጠር ችለዋል።የጨዋታው የመጀመርያ ሙከራ እንየው ካሳሁን ከመሃል ሜዳ ወደ ፍፁም ቅጣት ሳጥን ውስጥ በመግባት የመታው ኳስ ከግቡ እናት ወደ ውጭ ወጥቷል።ከደቂቃዎች በኃላ እፎርቅ ሃይሉ ከርቀት እክርሮ የመታው ኳስ ጃኮ ፔንዜ ወደ ውጭ እውጥቶበታል።መሃል ሜዳ ላይ ብልጫ የወሰዱት እዳማ ከተማዎች እንደወሰዱት የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የግብ እድል መፍጠር አልቻሉም።የዚህም ዋና ተጠቃሽ ምክንያት ቡድኑ ተፎጥራእዊ እጥቂ ማጣቱ ነው።በፈጣን መልሶ ማጥቃት የእዳማ ፍፁም ቅጣት ሳጥን ላይ ሲደርሱ የነበሩት ወልዋሎዎች እሁንም በተመሳሳይ እንየው ኳሳሁን ከቀኝ መስመር ለ ራችሞንድ ኦዶንግ የሰጠው ኳስ በመጠቀም የሞከረው ኳስ ጃኮ ፔንዜ መልሶበታል።በእጫጭር ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ሲሞክሩ የነበሩት እዳማዎች የመጀመርያ እጋማሽ መጨረሻ ላይ የወልዋሎ ተከላካዮችን መዘናጋት ተጠቅሞ ከንእን ማርክነህ የመታው ኳስ አብዱላዚዝ ኬይታ መልሶበታል።

ሁለተኛው እጋማሽ ጥሩ ፋክክር ያልታየበት አዳማዎች መከላከልን ሲመርጡ ወልዋሎዎች በበኩላቸው ራችሞንድ ኦዶንግ ላይ ትኩረት ያደረጉ ረጃጅም ኳሶችን ሲያሻግሩ ታይቷል።ብርሃኑ እሻሞን በፕሪንስ ሰቨሪንሆ ቀይረው ያስገቡት ዮውሃንስ ሳህለ በመጀመርያ እጋማሽ በእዳማ የተወሰደባቸውን የመሃል ሜዳ ብልጫን በተወሰነ መልኩ መመለስ ችለዋል።በቡልቻ ሹራ ና ዱላ ሙላቱ እማካኝነት ከመስመር በመነሳት በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት ቢሞክሩም እንደጠበቁት ውጤታማ ሊሆን እልቻለም።ኢላማቸው የጠበቁ ሙከራዎችን ያላሳየው ሁለተኛው እጋማሽ በተጨማሪ 6 ደቂቃዎች ላይ ሁለት ግቦችን እስተናግዷል።በ92ኛው ደቂቃ ከቀኝ መስመር ከንእን ማርክነህ ወደ ፍፁም ቅጣት ሳጥን ይዞት የገባውን ኳስ መረብ ላይ እስቆጥሮ እዳማዎችን በደስታ እስፈንጥዝዋል።እዳማዎች ደስታቸውን እጣጥመው ሳይጨርሱ ተቀይሮ የገባው ሰመረ ካህሳይ ተቀይሮ ከገባው ስምኦን ማሩ የተቀበለውን ኳስ በጥሩ እጨራረስ ወልዋሎን እቻ ማድረግ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ ወልዋሎ ነጥባቸውን 37 በማድረስ 6ተኛ ላይ ሲቀመጡ እዳማዎች በ34 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ኢትዮጵያ ቡና ካሳዬ አራጌን ቀጣዩ አሰልጣኝ አድርጎ መርጧል

የኢትዮጵያ ቡና የስራ አመራር ቦርድ በአዲስ መልክ ካዋቀራቸው ኮሚቴዎች ውስጥ የእግር ኳስ ኦፕሬሽንና ቴክኒክ አስተዳደር ኮሚቴ (ቴክኒክ ኮሚቴ) አንዱ ነው። ይህ ኮሚቴ በቦርዱ በተሰጠው መመሪያ መሰረት የመጀመሪያ ስራ የአሰልጣኝ ቅጥርን ማከናወን ነበር።
በዚህም መሰረት በ2012 ዓ.ም የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ቡና ዋናው ቡድን አሰልጣኝ ለመምረጥ የተለያዩ መመዘኛዎች በማውጣትና የኢትዮጵያ ቡና የሚታወቅበትን የጨዋታ ዘይቤ በጥልቀት ይረዳል በሚል መነሻነት የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና የመሀል ሜዳ ቴክኒሻን ካሳዬ አራጌን መርጧል። ከሚኖርበት ሀገረ አሜሪካ በፍጥነት መጥቶ ባለው አጠቃላይ ሁኔታዎች ከቦርዱ ጋር ከተነጋገረ እና ስምምነት ላይ ከተደረሰ የ2011ዓ.ም የውድድር አመት ሳይጠናቀቅ የተጫዋቾች ምርጫ እንዲያደርግ ዛሬ ከውሳኔ ተደርሷል።

source – offical Ethiopia coffee sport club page…

የ2011 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በቀጥታ ውጤት /LIVESCORE/ ይከታተሉ

  የ2011 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች 


 ማክሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2011

9:00
  ኢትዮጵያ ቡና 
   ?-?   
 መቐለ 70 እ.

እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2011

   FT
  ደደቢት 
    2-3
ቅዱስ ጊዮርጊስ
 
 69′ ፋሱይኒ ኑሁ     08′ አሜ መሀመድ
  78′ ሔኖክ መርሹ   42’ሪቻርድ አርተር 
                                         76′ አስቻለው ታመነ (ፍ)
  FT
 ድሬዳዋ ከተማ 
    1-1
  ስሑል ሽረ
 
  74′ ዳኛቸው በቀለ 75’ቢስማክ አፒያ
  FT
ፋሲል ከነማ 
   4-0
 ባህርዳር ከተማ 
05’ሽመክት ጉግሳ
22′  73′ሙጂብ ቃሲም
32’ኢዙ አዙካ 
   FT
 ወላይታ ድቻ
    3-0
 ጅማ አባጅፋር

(በፎርፌ)


ቅዳሜ ግንቦት 24 ቀን 2011

 FT
  መከላከያ 
   4-1
 ሲዳማ ቡና

 10′ ፍፁም ገ/ማርያም  45′ ሀብታሙ ገዛኸኝ 

  24′ ቴድሮስ ታደሰ

  25′ ፍሬው ሰለሞን

 60′ ፍቃዱ አለሙ

 FT
 ወልዋሎ አ. 
    1-1
አዳማ ከተማ
 
 90+5′ ሰመረ ካህሳይ |90+3′ ከነአን ማርክነህ 
 FT
  ደቡብ ፖሊስ 
    3-2
 ሐዋሳ ከተማ
 
 47′ 77′ የትሻ ግዛው   30 ደስታ ዮሐንስ 

   50′ ብሩክ ኤልያስ            39 መስፍን ታፈሰ