ኢትዮጵያ ቡና ካሳዬ አራጌን ቀጣዩ አሰልጣኝ አድርጎ መርጧል

የኢትዮጵያ ቡና የስራ አመራር ቦርድ በአዲስ መልክ ካዋቀራቸው ኮሚቴዎች ውስጥ የእግር ኳስ ኦፕሬሽንና ቴክኒክ አስተዳደር ኮሚቴ (ቴክኒክ ኮሚቴ) አንዱ ነው። ይህ ኮሚቴ በቦርዱ በተሰጠው መመሪያ መሰረት የመጀመሪያ ስራ የአሰልጣኝ ቅጥርን ማከናወን ነበር።
በዚህም መሰረት በ2012 ዓ.ም የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ቡና ዋናው ቡድን አሰልጣኝ ለመምረጥ የተለያዩ መመዘኛዎች በማውጣትና የኢትዮጵያ ቡና የሚታወቅበትን የጨዋታ ዘይቤ በጥልቀት ይረዳል በሚል መነሻነት የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና የመሀል ሜዳ ቴክኒሻን ካሳዬ አራጌን መርጧል። ከሚኖርበት ሀገረ አሜሪካ በፍጥነት መጥቶ ባለው አጠቃላይ ሁኔታዎች ከቦርዱ ጋር ከተነጋገረ እና ስምምነት ላይ ከተደረሰ የ2011ዓ.ም የውድድር አመት ሳይጠናቀቅ የተጫዋቾች ምርጫ እንዲያደርግ ዛሬ ከውሳኔ ተደርሷል።

source – offical Ethiopia coffee sport club page…

hatricksport team

<p>Hatricksport team</p>

Facebook