ወልዋሎ አዲግራት በመጨረሻ ደቂቃ ላይ በተገኘች ግብ በሜዳው ከመሸነፍ ተርፏል

 

በ27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መቐለ ትግራይ ስታድየም ላይ የተካሄደው የወልዋሎ ና የእዳማ ጨዋታ በእቻ ውጤት ተጠናቋል።ወልዋሎ ባሳለፍነው ሳምንት ባህርዳርን ከገጠመው ስብስብ እንድም ቅያሪ ሳያደርግ ሲቀርብ እዳማ ከተማ ደደቢትን ካሸነፈው ቡድን እዲስ ህንፃን በከንእን ማርክነህ ምኞት ደበበን በተስፋዬ በቀለ ቀይረው ገብተዋል።

ብዙ ሙከራዎች ተመጣጣኝ ፋክክር በታየበት የመጀመርያው 45 በሁለቱም ቡድኖች ጥሩ ሙከራዎችን አሳይቷል።በ4-4-2 እሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት ወልዋሎዎች በፈጣን መልሶ ማጥቃት የግብ ሙከራዎችን መፍጠር ችለዋል።የጨዋታው የመጀመርያ ሙከራ እንየው ካሳሁን ከመሃል ሜዳ ወደ ፍፁም ቅጣት ሳጥን ውስጥ በመግባት የመታው ኳስ ከግቡ እናት ወደ ውጭ ወጥቷል።ከደቂቃዎች በኃላ እፎርቅ ሃይሉ ከርቀት እክርሮ የመታው ኳስ ጃኮ ፔንዜ ወደ ውጭ እውጥቶበታል።መሃል ሜዳ ላይ ብልጫ የወሰዱት እዳማ ከተማዎች እንደወሰዱት የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የግብ እድል መፍጠር አልቻሉም።የዚህም ዋና ተጠቃሽ ምክንያት ቡድኑ ተፎጥራእዊ እጥቂ ማጣቱ ነው።በፈጣን መልሶ ማጥቃት የእዳማ ፍፁም ቅጣት ሳጥን ላይ ሲደርሱ የነበሩት ወልዋሎዎች እሁንም በተመሳሳይ እንየው ኳሳሁን ከቀኝ መስመር ለ ራችሞንድ ኦዶንግ የሰጠው ኳስ በመጠቀም የሞከረው ኳስ ጃኮ ፔንዜ መልሶበታል።በእጫጭር ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ሲሞክሩ የነበሩት እዳማዎች የመጀመርያ እጋማሽ መጨረሻ ላይ የወልዋሎ ተከላካዮችን መዘናጋት ተጠቅሞ ከንእን ማርክነህ የመታው ኳስ አብዱላዚዝ ኬይታ መልሶበታል።

ሁለተኛው እጋማሽ ጥሩ ፋክክር ያልታየበት አዳማዎች መከላከልን ሲመርጡ ወልዋሎዎች በበኩላቸው ራችሞንድ ኦዶንግ ላይ ትኩረት ያደረጉ ረጃጅም ኳሶችን ሲያሻግሩ ታይቷል።ብርሃኑ እሻሞን በፕሪንስ ሰቨሪንሆ ቀይረው ያስገቡት ዮውሃንስ ሳህለ በመጀመርያ እጋማሽ በእዳማ የተወሰደባቸውን የመሃል ሜዳ ብልጫን በተወሰነ መልኩ መመለስ ችለዋል።በቡልቻ ሹራ ና ዱላ ሙላቱ እማካኝነት ከመስመር በመነሳት በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት ቢሞክሩም እንደጠበቁት ውጤታማ ሊሆን እልቻለም።ኢላማቸው የጠበቁ ሙከራዎችን ያላሳየው ሁለተኛው እጋማሽ በተጨማሪ 6 ደቂቃዎች ላይ ሁለት ግቦችን እስተናግዷል።በ92ኛው ደቂቃ ከቀኝ መስመር ከንእን ማርክነህ ወደ ፍፁም ቅጣት ሳጥን ይዞት የገባውን ኳስ መረብ ላይ እስቆጥሮ እዳማዎችን በደስታ እስፈንጥዝዋል።እዳማዎች ደስታቸውን እጣጥመው ሳይጨርሱ ተቀይሮ የገባው ሰመረ ካህሳይ ተቀይሮ ከገባው ስምኦን ማሩ የተቀበለውን ኳስ በጥሩ እጨራረስ ወልዋሎን እቻ ማድረግ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ ወልዋሎ ነጥባቸውን 37 በማድረስ 6ተኛ ላይ ሲቀመጡ እዳማዎች በ34 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

<p>Hatricksport website writer</p>

Twitter