ፋሲል ከነማ ባህርዳር ከተማን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል

 

በ27ኛው ሳምንት እሁድ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአማራ ደርቢ ጨዋታ ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ እና ባህርዳር ከተማ ጨዋታ በፋሲል ከነማ አሸናፊነት ተጠናቋል።ፋሲል ከነማ ወደ ወላይታ ተጉዞ 2-1 ከተሸነፈው ቡድን ምንም አይነት ለውጥ ሳያደርግ ነበር ወደ ሜዳ የገባው በአንጻሩ እንግዳው ቡድን ባህርዳር ከተማ ውልዋሎ ጋር ነጥብ ከጣለው ስብስብ አስናቀ ሞገስ፣ ኤልያስ አህመድ እና ልደቱ ሞላን በ ሳላምላክ ተገኝ፣ ዜናው ፈረደ እና ስነ ጊዮርጊስን ቀይሮ ነበር ወደ ሜዳ የገቡት።

የፋሲል ከነማ ብልጫ በታየበት የመጀመርያ አጋማሽ በ4-3-3 አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት አጼዎቹ በተሻለ መልኩ ወደ ግብ ቀርበዋል።ጨዋታው ገና እንደተጀመረ በሙከራ የታጀበ ነበር። 3ኛው ደቂቃ ላይ ሰአድ ሀሰን በቀኝ መስመር ለኢዙ አዙካ ያሻገረለትን ኳስ ኢዙ አዙካ ተከላካዮችን አታሎ ይዞት በመግባት ወደ ግብ አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ምንተስኖት አሎ የተፋውን ሽመክት ጉግሳ አግኝቶ በ ቴስታ በቀላሉ አስቆጥሮ ፋሲሎች መሪ እንዲሆኑ አስችሉዋል።አጼዎቹ ከጎሎዋ መቆጠር በሁዋላ በተደጋጋሚ የ ባህርዳር ከተማን የጎል መስመር ሲፈትሹ ተስተውለናል፡፡በተለይ ሱራፌል ዳኛቸው 9ኛው ደቂቃ ላይ አክርሮ የመታው ኳስ እና በግቡ አግዳሚ ለጥቂት የወጣው አንዱ አስደንጋጭ ሙከራ ነበር።ረጃጅም ኳሶችን በሁለቱም መስመሮች በኩል ክሮስ እያደረጉ ተጭነው የተጫወቱት ፋሲሎዎች በ 25ተኛው ደቂቃ ላይ አምሳሉ ጥላሁን ከኤፍሬም አለሙ የተቀበለውን በቀጥታ ወደ ጎል ያሻማውን ኳስ የምንተስኖት አሎ ስህተት ተጠቅሞ ሙጅብ ቃሲም በቴስታ መረብ ላይ አሳርፏታል።ከጎሉ መቆጠር በሁዋላ ፋሲሎች በተደጋጋሚ ወደ ጎል ሲሞክሩ ተመልክተናል ሙከራቸውም ተሳክቶላቸው በ 31ደኛው ደቂቃ በእለቱ አስደናቂ ብቃቱን ሲያሳይ የነበርው እና የጨዋታው ኮኮብ ኢዙ አዙካ ከ መሀል ሜዳ የተቀበለውን ኳስ በሚገርም ሁኔታ 5 የጣና ሞገድ ተከላካዮች አታሎ በማለፍ ለፋሲል ሶስተኛዋን ጎል በሚገርም አጨራረስ እና ብቃት አስቆጥሩዋል።በፋሲል መሪነት የመጀመሪያ አጋማሽ ተጠናቁዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ባህርዳር ከተማ ተጫዋቾችን በመቀየር ወደ ጭዋታ ለመመለስ እና ተጭነው ለመጫወት ሞክረዋል፡፡ 69ኛው ደቂቃ ሚካኤል ቬራ ጃኮ አራፋት ከሳጥን ውጭ ያሻገረለትን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ አክርሮ ወደ ጎል የመታው እና ሚካኤል ሳማኪ በ ግሩም ሁኔታ ያወጣበት በጭዋታው ለጣና ሞገድ ብቸኛ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ነበር፡፡ፋሲሎች በአንጻሩ ኳስ ይዘው ለመጫወት ሙከራ ሲያደርጉ አስተውለናል።73ተኛው ደቂቃ ላይ ሙጅብ ቃሲም ከዮሴፍ ዳሙየ ጋር አንድ ሁለት ተጫውቶ በጭዋታው ለእራሱ ሁለተኛውን ለቡድኑ ፋሲል አራተኛውን እንዲሁም በውድድር አመቱ 14 ተኛውን ጎሉን አስቆጥሮ ጭዋታው ተጠናቁዋል።

ጭዋታው ፍጹም ጭዋነት የተሞላበት እና የደጋፊዎች ድባብ በጣም የሚያምር እና ታሪካዊ ጭዋታ ነበር፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 52 በማሳደግ መሪነቱን አጠናካሩዋል በአንጻሩ እንግዳው ቡድን ባህርዳር ከነማ 37 ነጥብ በመያዝ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጡዋል።

ሪፖርተር:ከድር ጀማል
ከ ባህርዳር