የሐሙሱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ውዝግብ እንዳይነሳበት ተሰግቷል�

በዮሴፍ ከፈለኝ

በኢመርጀንሲ ኮሚቴና በተቀሩት
የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት
መሀል የነበረው አለመግባባት በረድ ቢልም
ልዩነቶችን ሊያሰፋ የሚችል ምክንያት
መፈጠሩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የፊታችን
ሀሙስ ሀምሌ 25/2011 የሚደረገው የስራ
አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱ ስብሰባ ሌላ ውዝግብ
እንያስከትል ተሰግቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት
በካፒታል ሆቴል ከግንቦት በኋላ ለመጀመሪያ
ጊዜ የተገገናኙት አመራሮቹ በያዙት አጀንዳ
ላይ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት የስዑልሽረና
ወልዋሎ ጨዋታ ህገ ወጥ ድርጊት
ታይቶበታል በሚል አርቢትሩና ኮሚሸነሩ
ሪፖርት በማድረጋቸው ጉዳዩን ዲሲፒሊን
ኮሚቴ አይቶ ውሳኔ እንዲሰጥ ይግባኝ ሰሚ
ኮሚቴም የቅዱስ ጊዮርጊስን ይግባኝ ባፋጣኝ
አይቶ ከአመራሮቹ የሀሙስ ስብስባ በፊት
ውሳኔያቸውን እንዲያሳውቁ ቢወሰንም
ሀትሪክ የደረሳት መረጃ ግን ጉዳዩን አጠራጣሪ
አድርጎታል፡፡ ከታማኝ ምንጮች በደረሰ መረጃ
ዲሲፕሊን ኮሚቴ በወልዋሎ አዲግራትና
ስሁል ሽረ ጨዋታ ዙሪያ ምንም አይነት
መረጃ እንዳልደረሰው ታውቋል፡፡ ይህ ደግሞ
ለሀሙሱ ስብሰባ የዲስፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ
ላይቀርብ እንደሚችል አመላክቷል፡፡ የቅዲስ
ጊዮርጊስ ይግባኝ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ቢደርስም
እስከዛሬ ድረስ ይግባኙን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው
አለማየቱ ታውቋል፡፡ መደበኛ ስብሰባቸው
ሀሙስ ሃሙስ የሚያደርጉት የይግባኝ ሰሚ
ኮሚቴ አባላት ምናልባት በአቸኳይ ማክሰኞና
ረቡዕ ካልተሰበሰቡ በስተቀር የአመራሮቹ
ስብሰባ ውጤት አልባ ሊሆን እንደሚችል
ተሰግቷል፡፡ ከኮሚቴው ምንጫችን ባገኘነው
መረጃ “ብንሰባሰብ እንኳን የሚቀርበው
ሰነድ ካልተሟላ ውሳኔ ላይሰጥ ይችላል”
ሲል የሁኔታውን አጠራጣሪነት አስረድቷል፡
፡ በተለይ ወልዋሎ አዲግራትና ስሁል ሽረ
ጨዋታ ዙሪያ የተሟላ መረጃ አለኝ ያለው
መከላከያ ጥያቄ ማቅረቡና እስካሁን ምላሽ
አለማግኘቱ ራሱን የቻለ ክርክር እንዳያስነሳም
ተሰግቷል፡፡ በስሁልሽረ ደጋፊዎች ተፈፀመ
የተባለው ድርጊት በፌዴሬሽኑ ህግ ነጥብ
የሚያስቀንስ ቢሆንም አመራሮቹ ይህን
የማድረግ ድፍረት ይኖራቸዋል ወይ?
የሚለው የበርካቶችን ትኩረት ስቧል፡፡

hatricksport team

<p>Hatricksport team</p>

Facebook