Day: August 7, 2019

32ቱ ህጋዊ የተጨዋች (የክለብ) ወኪሎች ተለይተው ታወቁ

32ቱ ህጋዊ የተጨዋች (የክለብ) ወኪሎች ተለይተው ታወቁ

ከ2012 ዓ.ም የውድድር ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመሚመራቸው ውድድሩሮች ላይ ተሳታፊ ለሚሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ተጨዋቾች ዝውውርን ለማካሄድ የዓለም አቀፋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን /ፊፋ/ ባወጣው መመሪያ መሠረት ቅድመ ሁኔታዎችን ላሟሉ 32 ኢንተርሚደሪዎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህጋዊ ፈቃድ ተሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢንተርሚደሪ /የሶስተኛ ወገን/ ፈቃድ ለሚፈልጉ በሙሉ በፌዴሬሽኑ መስፈርት መሠረት የፈቃድ መውሰጃ ፈተና በመስጠት 75 የሚሆኑት ተመዝጋቢዎች በመመዘኛ መሠረት ፈተናውን ወስደው ማለፋቸውን የአረጋገጡ በመሆናቸው ከፈለፋት ውስጥ 32 የሚሆኑት የፈቃድ መውሰጃ /የላይሰንስ/ እና የኢንሹራንስ ክፍያ በመፈፀም አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች በማጠናቀቃቸው ሐምሌ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ህጋዊ ፍቃዳቸውን ወስደዋል፡፡

ሕጋዊ ፈቃዱ ለሁለት ዓመታት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን እና ይህንን ፈቃድ ያገኙ ብቻ ዝውውሩን እንደሚሰሩ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚደረጉ ዝውውሮች ህገወጥ መሆናቸውን እና በፌዴሬሽኑም ሆነ በፊፋ ተቀባይነት የማይኖራቸው መሆኑን ፌዴሬሽኑ ገልጿል፡፡

ፈቃዱን የወሰዱ ዝርዝር

1 ጢሞቲዮስ ባዬ
2 ኤርሚያስ ተክሌ
3 ብሩክ ኢስራኤል
4 ደረጄ መኮንን
5 ዘርአይ ኢያሱ
6 በያን ሁሴን
7 ኤፍሬም ተሰማ
8 አፈወርቅ አሳለ
9 መነን መላኩ
10 እስክንድር ገመዳ
11 ሙሉጌታ ወልደሚካኤል
12 ተስፋአብ ህሉፍ
13 ተሾመ ፋንታሁን
14 ለአለም ሲሳይ
15 ፍቃዱ ተፈራ
16 ሞገስ በሪሁን
17 ብርሃኑ በጋሻው
18 ከበረ አስማረ
19 ስለሺ ብሩ
20 ቴዎድሮስ ፋና
21 ዳግማዊ ረታ
22 ዱሬሳ ሳሙና
23 ጌትነት ኃይለማርያም
24 ወንድማገኝ መኮንን
25 አብዱልወሃብ ፋሪስ
26 አሰግድ ከተማ
27 ሄኖክ ታምሩ
28 ጋሮ ገረመው
29 ፈድሉ ዳርሰቦ
30 መሀቡባ ሳሙና
31 ቢኒያም ወርቁ
32 በረከት ደረጄ

Via – EFF

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኖቹ መቐለ 70 እንደርታ ወደ ማላቦ ኢኳቶሪያል ጊኒ ሚያደርጉትን ጉዞ ጀምረዋል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኖቹ መቐለ 70 እንደርታ ወደ ማላቦ ኢኳቶሪያል ጊኒ ሚያደርጉትን ጉዞ ጀምረዋል

በታሪካቸው ለመጀመርያ ጊዜ በእፍሪካው ትልቁ መድረክ ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ሚሳተፋት መቐለ 70 እንደርታ የቅድመ ማጣሪያው የመጀመርያ ዙር ጨዋታቸውን ለማከናወን ወደ ማላቡ እቅንተዋል።

19 ተጨዋቾችን በመያዝ ወደ ማላቡ ያቀናው መቐለ 70 እንደርታ ቅዳሜ ነሐሴ 4 ከቀኑ 11 ሰዓት የኢኳቶሪያል ሊግ ሻምፒዮን የሆነውን ካኖ ስፖርትን ይገጥማል።

ወደ ማላቦ ያቀኑ ተጨዋች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች፦ ፊሊፕ ኦቮኖ፣ ሶፎንያስ ሰይፈ

ተከላካዮች ፦ እሌክስ ተሰማ፣ እሚን ነስሩ፣ ታፈሰ ሰርካ፣ ኣንተነህ ገ/ክርስቶስ፣ ሄኖክ ኢሳይያስ፣ ስዩም ተስፋዬ

እማካዮች፦ ሚካኤል ደስታ፣ ጋብርኤል ኣሕመድ፣ ሃይደር ሸረፋ፣ ዮናስ ገረመው፣ ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ፣ ኤፍሬም እሻሞ፣ያሬድ ብርሃነ

እጥቂዎች፦ ኦሴይ ማውሊ፣ እማኑኤል ገ/ሚካኤል፣ያሬድ ከበደ

ኢትዮጵያ ሁለት ስታድየሙዎቻ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን እንዲያስተናግዱ በካፍ ፍቃድ ተሰጣቸው

ኢትዮጵያ ሁለት ስታድየሙዎቻ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን እንዲያስተናግዱ በካፍ ፍቃድ ተሰጣቸው

ከቀናት በፊት እንጋፋውን የእዲስ እበባ ስታድየም ምንም እይነት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች እንዳያስተናግድ የከለከለው ካፍ፤ለሁለቱም ትግራይና ባህርዳር ስታድየም ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን እንዲያስተናግዱ ገድብ ያለው ፍቃድ ሰጠ።

ዛሬ ካፍ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው በፈረንጆች እቆጣጠር እስከ ጥቅምት 8 ድረስ ገደብ ያለው ፍቃድ እንደተሰጣቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚደንት ኢሳያስ ጅራ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።ፕሬዝዳንቱ እያይዘውም
ምንም እንካን ፈቃዱ ቢሰጥም አሁንም ግን መሰራት ያለባቸው ስራዋች እንዳሉ እስገንዝበዋል።በተጨማሪም አቶ ኢሳያስ ጂራ የሚመለከታቸው የክልልና የፌደራል የመንግስት አካላት ድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በዚህም መሰረት በእፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን ሚወክሉት መቐለ 70 እንደርታና ፋሲል ከተማ ጨዋታቸውን በትግራይና በባህርዳር ስታድየም ያደርጋሉ።