Day: August 12, 2019

ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ የሚወዷት፤ በጉጉት የሚጠብቋት ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም እናንተን በንባብ ልታገኝ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡

ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ
የሚወዷት፤ በጉጉት የሚጠብቋት ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም እናንተን በንባብ ልታገኝ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡
ሀትሪክ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
በሀገር ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የሀትሪክ ስፖርት ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተርና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሀቅ በላይ ላለፉት በርካታ ዓመታት በክለብና በብሄራዊ ቡድን የእግር ኳስ ተጨዋችነትም ሆነ የአሰልጣኝነት ሙያ ላይ በመሰማራት አብዛኛው ህይወቱን ያሰለፈውንና በአሁን ሰዓት ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ክለብን ለማሰልጠን በመስማማት ፊርማውን ላኖረው አመለ ሸጋው ፋሲል ተካልኝ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቦለት የሰጠውን ምላሽ ጋዜጣዋ ታቀርብሎታለች፡፡ ፋሲል ምን ብሎ ይሆን ሀትሪክን ያንብቧት።
ሀትሪክ ስፖርት በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋም በአፍሪክ ክለቦች የኢንተርናሽናል የውድድር መድረክ ሀገራችንን በመወከል ስለተሳተፉት መቐለ 70 እንደርታና ፋሲል ከነማም መረጃ አላት፤ ከእነዚህ መካከል ፋሲል ከነማ የታንዛኒያውን አዛም ክለብ ባሸነፈበት ጨዋታ ዙሪያ ለቡድኑ የድሉን ጎል ያስቆጠረው በዛብህ መላዮ የሚለው አለው። ተከታተሉት፤ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች የደሞዝ ክፍያ ዙሪያም የተጨዋቾች ደሞዝ ከ50 ሺ ብር መብለጥ የለበትም ተብሎ በተወሰነው ውሳኔ ዙሪያም እየተፈጠሩ ባሉት ጉዳዮች ላይም ሀትሪክ መረጃን ትሰጦታለች፤ ሀትሪክ አታምልጦት፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዋም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በይፋ መጀመርን አስመልክቶ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ስለተካሄዱት ታላላቅ ጨዋታዎች ዙሪያ በተለይ ማንቸስተር ዩናይትድ ቼልሲን እንደዚሁም አርሰናል ኒውካስትልን ባሸነፉበት እና ሌሎች ግጥሚያዎችን አስመልክተን የሚወዱትን ዘገባ አቅርበንሎታል።
የሀትሪክ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል።

ፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ስዮም ከበደን በኃላፊነት ሾመ

ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ትናንት የታንዛኒያውን አዛም 1-0 አሸንፈው ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ይፋ ሁኗል ።
ፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ስዩም ከበደን በይፋ የቀጣዩ የአፄዎቹ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል ። አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የትናንትናውን የፋሲልና የአዛም ጨዋታ በባህርዳር ስታዲየም ተገኝተው የተመለከቱ ሲሆን ከ15 ቀናት በኋላ በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከተማ ለሚካሄደው የመልስ ጨዋታ የአፄዎቹን የሚያዘጋጁ ይሆናል ።


አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ከዚህ ቀደም ሰበታ ከተማ ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አዲስ አበባ ከተማና መከላከያን ያሰለጠኑ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋሊያዎቹንና ሉሲዎቹን በምክትልና በዋና አሰልጣኝነት አሰልጥኗል ።

ፋሲል ከነማ በበዛብህ መለዮ ብቸኛ ግብ እዛምን እሸነፈ

 

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ዙር ጨዋታ  በሜዳው እዛምን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በመጀመርያ እጋማሽ በበዛብህ መለዮ እማካኝነት በተቆጠረች ግብ እሸንፈዋል።

በባለሜዳው የፋሲል ደጋፊዎች ደማቅ የሞዛይክ ትርኢት ታጅቦ በተካሄደው የመጀመርያ እጋማሽ የፋሲሎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ እና ሙከራ የታየበት ነበር።በመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች እፄዎቹ ከሁለቱም መስመር በሚነሱ ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ቢሞክሩም እንደ ያዙት የኳስ ብልጫ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ እልቻሉም። ናይጀርያዊው ኢዙ እዙካ ከግራ መስመር ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ሰብሮ በመግባት ለሙጂብ እቀብሎት በእዛም ተከላካዮች በተመለሰ ኳስ እድሎችን መፍጠር የጀመሩት ፋሲሎች በተደጋጋሚ የእዛም ፍፁም ቅጣት ሳጥንን ቢጎበኙም የጠሩ እድሎችን መፍጠር ተስንዋቸው ታይቷል።የፋሲሎች ሊጠሩ ሚችሉ ሙከራዎችን ከቆሙ ኳሶች በተሻለ ሁኔታ ፈጥረዋል የዚህ ማሳያ ሚሆኑት በ6ኛው ደቂቃ ቀኝ መስመር ላይ የተገኝውን ቅጣት ምት ሱራፋኤል ዳኛቸው እሻምቶት በእዛም ተካላካዮች ተመልሶ የተገኘውን ኳስ ቅርብ የነበረው ሙጂብ ቢመታውም የግቡ የጎን መርበብ ገጭቶ ወጥቷል።በተመሳሳይ ሱራፌል ዳኛቸው ከፋሲል ሜዳ ቀኝ መስመር በረጅሙ የላከው ኳስ እጥቂው ሙጂብ ቃሲም የእዛም ተከላካይና በረኛ አለመግባባት በመጠቀም ያገኘውን ኳስ በጨረፍታ ቢመታውም ለትንሽ ወደ ውጭ ሊወጣ ችሏል።እንግዶቹ እዛም በበኩላቸው በ3-5-2 እሰላለፍ ወደ ኃላ ማፈግፈግን ምርጫቸው በማድረግ ከመስመር በሚነሱ የመልሶ ማጥቃት ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ቢሞክሩም ሚካኤል ሳማኬን እና ተቀይሮ የገባውን ጀማል ጣሰው ሚፈትኑ እልነበሩም።

መስመር ላይ ትኩረት ያደረገው የፋሲል እጨዋወት መደበኛው የመጀመርያ 45 ተጠናቆ ዳኛው በጨመረው 2 ደቂቃዎች ላይ ፍሬ ማፍራት ችሏል።ሽመክት ጉግሳ ከግራ መስመር ያሻማው ኳስ በፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን በቀኝ በኩል የነበረው ሙጂብ ወደ ውስጥ መልሶት በዛብህ መለዮ በጥሩ እጨራረስ አፄወቹን በመሪነት ወደ ዕረፍት እንዲወጡ እድርጓል።

በሁለተኛው እጋማሽ ተሽለው የቀረቡት እዛሞች እሁንም መስመር ላይ ትኩረት እድርገው እድሎችን ፈጥረዋል።በተለይ ፊት ላይ የነበረው የእብርይ ቼርሞ ና ኤዲ ሱሌማን ጥምረት የፋሲል ተከላካይ ክፍልን በሚገባ መፈተን ችሏል።የሁለተኛው እጋማሽ የመጀመርያ ሙከራ ከቀኝ መስመር ኤዲ ሱሌማን ያሻገረው ኳስ አብሬይ ቼርሞ በግምባሩ ቢገጨውም ከግቡ ጎን ለጥቂት ወጥቷል።

በተመሳሳይ ቦታዎች ጥፋቶች ሲሰሩ የነበሩት ፋሲሎች ሁለተኛው እጋማሽ ላይ በእካል ብቃት ተዳክመው ታይቷል።በመጀመርያው እጋማሽ የኳስ ብልጫ ወስደው የተጫወቱት ፋሲሎች ሁለተኛ እጋማሽ ላይ ኳሱን ለእዛሞች በመስጠት መከላከልን ምርጫቸውን እድርገዋል።በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ በእዞሞች ጥቃት ደርሶባቸዋል፤በተለይ ተቀይሮ የገባው ሙዩ ኩሪ በተቀራራቢ ደቂቃዎች ከተመሳሳይ ቦታ የመታቸው ሁለት ኳሶች እንደኛው ለትንሽ ወደ ውጭ ሲወጣ ሁለተኛው የግቡ እግዳሚ ሊመልሰው ችሏል።መሃል ሜዳ ላይ ብልጫ የተወሰደበት ውበቱ እባተ በሁለተኛው እጋማሽ ላይ ተዷክሞ የታየውን ሃብታሙ ተኸስተን በሰለሞን ሃብቴ በመቀየር በተሻለ ሁኔታ ተከላካይ ክፍሉ ሽፋን እንዲያገኝ በማድረግ ጨዋታው በፋሲል እሸናፊነት እንዲጠናቀቅ እድርጓል።

በዚህም መሰረት ፋሲል ከነማ የመጀመርያው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታውን በማሸነፍ ጀምሯል።የመልሱ ጨዋታ ከ15 ቀናት በኃላ ታንዛንያ ላይ ይካሄዳል።