Category: ሉሲዎቹ

የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለካሜሮን ጨዋታ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ አደረገች

አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ የኢትዮጵያ ሴቶች የኦሎምፒክ እግር ኳስ ቡድን ከካሜሩን ጋር ላለበት ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርጋለች፡፡

የኢትዮጵያ ሴት ኦሎምፒክ እግር ኳስ ቡድን ከካሜሩን አቻው ጋር የኦሎምፒክ ማጣሪያ ጨዋታውን ነሃሴ 20/2011ዓ.ም በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ያካሂዳል፡፡ ለዚህም እንዲረዳት አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድጋለች፡፡

ጥሪ የተደረገላው ተጫዋቾች በነገው ዕለት ነሃሴ 1/2011ዓ.ም አዲስ አበባ ስታዲየም ቴክኒክ እና ልማት ዳይሬክቶሬት ከጠዋቱ 4 ሰዓት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፎላቸዋል፡፡

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች

ግብ ጠባቂዎች

ታሪኳ በርገና (ጥረት ኮርፖሬት)
አባይነሽ ኤርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ)
ማርታ በቀለ (መከላከያ)

ተከላካዮች

መስከረም ኮንካ ( አዳማ ከተማ)
ገነሜ ወርቁ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
መሰሉ አበራ (መከላከያ)
ቅድስት ዘለቀ (ሐዋሳ ከተማ)
ብዙዓየሁ ታደሰ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ናርዶስ ጌትነት (አዳማ ከተማ)
አለምነሽ ገረመው (ኢትዮ ኤሌክተሪክ)
ነጻነት ጸጋዬ (አዳማ ከነማ)

አማካኞች

እጸገነት ብዙነህ (አዳማ ከነማ)
ሕይወት ደንጌሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
እመቤት አዲሱ(መከላከያ)
ብርቱካን ገ/ክርስቶስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ሰናይት ቦጋለ (አዳማ ከተማ)
አረጋሽ ካልሳ (መከላከያ)

አጥቂዎች

ምርቃት ፈለቀ(ሐዋሳ ከተማ)
ሎዛ አበራ(አዳማ ከተማ)
መዲና ጀማል( ሀዋሳ ከተማ)
ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ)
ሰርካዲስ ጉታ (አዳማ ከነማ)
ሔለን እሸቱ

ምንጭ – የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ውድድር የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ

በሩዋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው ሶስተኛው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ውድድር የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አዘጋጇን ሩዋንዳን 3ለ0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሉን አጣጥሟል።

ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓ.ም የተጀመረው ውድድር ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል።

ትናንት በስታድ ደ ኪጋሊ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመሰሉ አበራ፣ ምርቃት ፈለቀና ሴናፍ ዋቁማ ጎሎች የሩዋንዳ አቻውን ማሸነፍ ችሏል።

ሉሲዎቹ ጨዋታውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ወደ ዋንጫው ፉክክር የተመለሱ ሲሆን ሶስት ነጥብና ሁለት የግብ ክፍያ በመያዝ ከነበሩበት አምስተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ ማለት ችለዋል።

ሉሲዎቹ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ከኡጋንዳ አቻቸው ጋር ባደረጉት ጨዋታ ሁለት ለአንድ መሸነፋቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ጨዋታውን ነገ በስታድ ደ ኪጋሊ ነገ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ያደርጋል።

ትናንት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ታንዛኒያ ኡጋንዳን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። በዚሁ መሰረት ታንዛንያ ነጥቧን ወደ አራት ከፍ በማድረግ ወደ ሁለተኛ ደረጃ መምጣት ችላለች።

ኡጋንዳ በስድስት ነጥብ የመሪነቱን ደረጃ የያዘች ሲሆን ቀጣይ ጨዋታዋን ነገ ከቀኑ 11 ሰአት ከ15 ደቂቃ ከአዘጋጇ ሩዋንዳ ጋር ታደርጋለች።

በአጠቃላይ አምስቱ አገሮች እርስ በእርስ በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የተሻለ ነጥብ ያስመዘገበ ቡድን የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል።

ውድድሩ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2010 ዓ.ም ይቆያል።

​በሴካፋ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የሁለተኛ ቀን ልምምዱን ትናንትና በሩዋንዳ አድርጓል

በሩዋንዳ የሚካሄደው ሶስተኛው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) የሴቶች እግር ኳስ ውድድር ትናንት ተጀምሯል ።
በአገሪቷ ርዕሰ መዲና ኪጋሊ በሚካሄደው ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ አዘጋጇ ሩዋንዳ ፣ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያና ኬንያ ይሳተፋሉ።

በውድድሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 20 ተጫዋቾችና ሌሎች 10 ልዑካንን በመያዝ ከትናንት ወዲያ ወደ ሩዋንዳ በማምራት ማምሻውን የአገሪቷ ርዕሰ መዲና ኪጋሊ መድረሱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በሰላም ዘርአይ አሰልጣኝነት የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ትናንትና የሁለተኛ ቀን ልምምዱን ማድረጉም ተገልጿል።

ሉሲዎቹ ከሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለውድድሩ ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን የውድድሩን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ቅዳሜ ሐምሌ 14 ቀን 2010 ዓ.ም ከኡጋንዳ ጋር በሩዋንዳ ብሔራዊ ስታዲየም ከቀኑ 8 ሰዓት ከኡጋንዳ አቻው ጋር ያደርጋል።

በአጠቃላይ አምስቱ አገራት እርስ በእርስ በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የተሻለ ነጥብ ያስመዘገበ ቡድን የውድድሩ አሸናፊ እንደሚሆን የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ የክለቦች ማህበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) አስታውቋል።

የሴካፋ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2010 ዓ.ም ይቆያል።

የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ የክለቦች ማህበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) ውድድሩን ለማዘጋጀት የሚያስፈልገውን ወጪ በተቀመጠለት ጊዜ ለአዘጋጇ ሩዋንዳ ባለመላኩ ውድድሩ ከግንቦት ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ በተደጋጋሚ  ሲራዘም ቆይቷል።