Category: ስሁል ሽረ

ስሑል ሽረ አክሊሉ ዋለልኝን ከጅማ አባጅፋር አስፈረመ

 

በክረምቱ የዝውውር መስኮት በንቃት መሳተፍ የጀመረው ስሑል ሽረ የጅማ እባጅፋር እማካዩን አክሊሉ ዋለልኝን በእንድ ዓመት ውል እስፈርሟል።በሳምሶን አየለ ሚመሩት ስሑል ሽረዎች እክሊሉን ማስፈራማቸው ተከትሎ የክረምቱ ፈራሚዎቻቸው ቁጥር 4 አድርሰዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከተቀያሪ ወንበር እየተነሳ ለጅማ የተጫወተው አክሊሉ ኳስን መሰረት እድርጎ ለሚጫወተው የስሑል ሽሬ ቡድን ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪ ስሑል ሽረዎች የረመዳን ናስር፣አብዱሰላም አማን፣ዲሜጥሮስ ወልደስላሴ እና ደሳለኝ ደባሽ ውልን ማራዘም ችሏል።

ስሑል ሽረ የሥስት ተጨዋቾች ዝውውር አጠናቋል

 

በ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከወራጅነት ለጥቂት የተረፈው ስሑል ሽረ የቀጣይ ውድድር ዓመት ዝግጅቱን ሥስት ተጨዋቾችን በማስፈረም ጀምሯል።

ባለፈው የውድድር ዓመት የግብ ጠባቂ ችግር የተስተዋለበት ስሑል ሽረ ወንድወሰን እሸናፊን ከኢትዮጵያ ቡና እስፈርሟል።የቀድሞው የወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ ወንድወሰን እሸናፊ ባሳለፍነው ዓመት ከኢትዮጵያ ቡና ተቀያሪ ወንበር እየተነሳ እንዳንድ ጨዋታዎችን እካሂዷል።

በተመሳሳይ የተከላካይ መስመራቸውን ለማጠናከር በረከት ተሰማን ከወልዋሎ እብዲ ማሳላቺን ከጋና እስፈርሟል።የወልዋሎ ተከላካይ ክፍልን ከቢንያም ስራጅ ጋር በመፈራረቅ የመራው በርከት በቀጣይ ዓመት በስሑላውያን ማልያ ምንመለከተው ይሆናል።

በ2010 ለመቐለ 70 እንደርታ ፈርሞ ምንም ጨዋታ ሳያደርግ ወደ ሃገሩ የተመለሰውን የተከላካይ መስመር ተሰላፊው እዳሙ ማሳላቺን እስፈርሟል።

ሶስቱ የትግራይ ክልል ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ዱባይ ላይ የቅድመ ዝግጅት ጊዜ ሊያሳልፋ ነው

ኢትዮ-ነጃሺ ቱር ኤንድ ትራቭል ከትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ይህ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ሻምፒዮኒ መቐለ 70 እንደርታ፣ስሑል ሽረ ና ወልዋሎ ዓድግራት ዩኒቨርሲቲ ተሳታፊ ይሆናሉ።ከኦገስት 26- መስከረም 4 2019 ለ 9 ቀናት በሚቆየው የዝግጅት ጊዜ ሥስቱም ክለቦች በነጃሺ ካፕ ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ያልተለመደው ከሃገር ውጪ የቅድመ ውድድር ዝግጅት በነዚህ ክለቦች መጀመሩ ሊበረታታ ሚገባውና ሌሎች ክለቦችም ሊከተሉት ሚገባ ነው።

“ስሑል ሽሬ የመቐለ 70 አንደርታን ውክልና ይዞ ተጫውቶ ፋሲልን ዋንጫ አሳጥቷል ብለው የሚያወሩ ለእኔ የፖለቲካ ነጋዴዎች ናቸው”አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ (ስሑል ሽሬ)

THE BIG INTERVIEW WITH SAMSON AYELE

 

በይስሐቅ በላይ


 ሀትሪክ፡- …ሳምሶን…አስማተኛ…ነው…
አሰልጣኝ….?

ሳምሶን፡- …(እንደ መሳቅ እያለ)…
የምን አስማት…?…አመጣህ ደግሞ…ሳሚ…
የቀድሞ ተጫዋች… አሁን ደግሞ ሀገሪቱ
ውስጥ ካሉ አሰልጣኞች እንዱ ነው…፤…
ግን ለምን… እንዲህ ብለህ ጠየከኝ….? …
(አሁንም ሳቅ)….

ሀትሪክ፡-…ይሄን ጥያቄ የጠየኩህ ያለ
ምክንያት አይደለም…፤…ከሊጉ ይወርዳሉ
ተብለው ከተገመቱት ውስጥ አንዱ…አሁን
በአንተ አሰልጣኝነት የተረፈው ስኹል ሽሬ
ነው፡፡…ለመሆኑ…አንተ ከመጣህ በኋላ…
በሁለተኛው ዙር አስገራሚ ለውጥ ያመጣው
ስኹል ሽሬ…ከመውረድ የተረፈው…ምን
ሰርተህ… ወይም…ምን ተዓምር ፈጥረህ
ነው… ለማለት…ነው

ሳምሶን፡- …(በጣም ሣቅ)…
እኔ አስማተኛም ተዓምር ፈጣሪም
አይደለሁም…፤…ሱኹል ሽሬ ከመውረድ
የተረፈው በአስማት ወይም በተዓምር ሣይሆን
በስራና በስራ ብቻ ነው…፡፡…በመጀመሪያ
ክለቡን ከፍላጎቱ ጋር ለማገናኘት ኃላፊነቱን
ደፍሬ መውሰድ ነበረብኝ…፤…ኃላፊነቱን
ከመቀበሌ በፊት ቡደኑ ያደረጋቸውን አንድ
ሁለት ጨዋታዎች ለመመልከትም ሞክሬ ነበር፡
፡…እነዛ ሁለት በትኩረት የተከታተልኳቸው
ጨዋታዎች ቡድኑን እንዴት ማቀናጀትና ወደ
ውጤት ማምጣት እንዳለብኝ፣ ተጫዋቾቹ
ያላቸውና የሚጎላቸው ምን እንደሆነ ፍንጭ
ሰጥቶኝ ነበር፡፡ በአብዛኛው የቡደኑ ተጨዋቾች
ወጣቶች መሆናቸው መልካም ነገር ቢሆንም
አሁን ቡድኑ በጥብቅ ለሚፈልገው ነገር
ያላቸውን አቅማቸውን አውጥተው በመጠቀም
ቡደኑን ከችግር ሊያወጡ ይችላሉ ወይ…?…
በሚለው ላይ ሙሉ እምነቱ ስላልነበረኝ
ከአመራሮቹ ጋር በመነጋገር ቡድኑን በአዲስ
መልክ የመገንባት በአጭር ጊዜ ጠንካራ
ተፎካካሪ ሆኖ ከመውረድ ሊያወጡን
የሚችሉ አስፈላጊ ነገሮች ላይ መድከማችን
በመጨረሻ የልፋታችን ፍሬ ጣፋጭ እንዲሆን
አድርጎታል፡፡ እዚህ ላይ ግን በዋናነት ቡድኑን
በማጥቃትና በመከላከል ረገድ ከማነፅና
ከማዘጋጀት ባሻገር በስነ-ልቦናው “…መትረፍ
እንችላለን…፤…አንወርድም…” በሚል
በተጨዋቾቹ አዕምሮ ላይ ከፍተኛ የግንባታ
ሥራ ሠርተን በእኔ አቅም ብቻ ሣይሆን
በአመራሩ፣ በደጋፊውና በተጨዋቾቹ የጋራ
ሥራ የስኹል ሽሬ የፕሪሚየር ሊጉ ቆይታ
በአንድ አመት ብቻ እንዳይገድብ የሚያደርግ
ሥራ ሠርተን አትርፈነዋል፡፡

ሀትሪክ፡-ቡድኑን ለመረከብ ድርድር
ስታደርጉ “አሁን ያለው ውጤት ምንም
ደካማ ይሁን…ይሄንን ቡድን ከመውረድ
አተርፈዋለሁ…፤…አትጠራጠሩ…
አይወርድም…”…ብለህ ቀድመህ ቃል
ገብተህ ነው ክለቡን የተረከብከው…ሲባል
ሰምቻለሁና…ከምን ተነስተህ…በዚህ ደረጃ
ቃል ልትገባና…እርግጠኛ ልትሆን ቻልክ…?

ሳምሶን፡- …(ሣቅ)…ምናልባት ትንቢተኛ
ወይም ተንባይ ነህ እንዳትለኝ እንጂ…
ቡድኑን ለመረከብ ስንደራደር…ይሄ ቡድን
አይወርድም…አትርፈዋለሁ…ይሄን ካለደረኩ
አባሩኝ…ብዬ ቀድሜ ቃል ገብቼ ነው ቡደኑን
የተረከብኩት…፡፡…ይሄን ያልኩት ደግሞ
ሆዴን ለመሙላት፣የጤፍ መግዣ ገንዘብ
ለማግኘት ወይም ወደ ስልጠና ለመመለስ
ከመጓጓት ሣይሆን ቡድኑ ላይ ሥራ ከሠራሁ
መለወጥ እንደምችል ውስጤ በጣም ስላመነና
ከፍተኛ የሥራ ስሜት በውጤ ስለነበር ነው፡
፡ ከስልጠና ርቄ በተቀመጥኩባቸው ጊዜያት
የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታዎችና የቡደኖችን
አቋም በቅርበት እከታተል እገመግም
ስለነበር…የትኛው አካባቢ ብሰራ…የትኛው
አካባቢ ትኩረት ባደርግ መለወጥ እችላለሁ…
የሚለውን በግንዛቤ ደረጃ ይዤው ስለነበር…
ይሄንን ወደ ውጤት ለመቀየር እንዳልቸገር
ረድቶኛል…፡፡

ሀትሪክ፡- ከስኹል ሽሬ ጋር
ያስመዘገብከው…የስልጠና ህይወትህ ትልቁ
ውጤት ነው…ብሎ መውሰድ ይቻላል…?

ሳምሶን፡- …እ…ምን…መስለህ…!…
በእርግጥ ቀደም ሲል በፕርምዬር ሊግም በብ/
ሊግ ደረጃም ሳሰለጥን በትልቅነት የሚነሱ
ያስመዘገብኳቸው ውጤቶች አሉ…፤…
ያም ቢሆን ግን… የስኹል ሽሬ ውጤት
የተመዘገበው በብዙ ፈተናዎች ውስጥ
በመሆኑ ውጤቱን ይበልጥ በትልቅነት
እንዳነሣው ያስገድደኛል…፤…ምክንያቱም…
እኔ ወደ ስኹል ሽሬ ኃላፊነት ስመጣ
ቡድኑ ከውጤት ጋር የተጣለበት፣ ብዙዎች
የመውረድ እጣ ፈንታው ከፍተኛ እንደሆነ
የተነበዩበት ወቅት ነበር፡፡ ከምንም በላይ
ደግሞ ክለቡ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በመጣበት
አመት ተመልሶ የመውረድና በክለቡ ታሪክ
ላይ መጥፎ የሚባል ውጤት ለማስመዝገብ
የተቃረበበት ወቅት ስለነበር በዚህ አይነት
አጣብቂኝ ውስጥ ያለን ክለብ ማዳን ለእንደ
እኔ አይነቱ ገና ታዳጊ ለሆነ አሰልጣኝ ውጤቱ
ከትልቅነትም በላይ ነው፡፡ በስኹል ሽሬ
ያስመዘገብኩት ውጤት ለእኔ ብቻ ሣይሆን
ለብዙዎች እግር ኳስ በማውራት ብቻ
ሣይሆን ከተሠራ፣ ከተለፋ ለውጥ ማምጣት
እንደሚቻል ያየሁበትና የተማርኩበት ለእኔም
የሥልጠና ህይወቴ ትልቅ የደስታ ስሜትን
የፈጠረልኝና ሁሌም በመልካምነት ሣነሳው
የምኖረው የሥልጠና ህይወቴ አንደኛው
ትልቁ ውጤት ነው፡፡

ሀትሪክ፡- …ሳሚ…አሁን ትንሽ ኮስተር
ወደ አለው…ቃለ-ምልልስ ልንገባ…ነው…
ዝግጁ…ነህ…?

ሳምሶን፡- …(ፊቱን ኮስተር አድርጎ
እንደመገረም እያለ)…ኮስተር ያለ…ቃለ-
ምልልስ…ስትል…? አልገባኝም…?…
ለ ማ ን ኛ ው ም … የ ፈ ለ ከ ው ን … መ ጠ የ ቅ
ትችላለህ…?

ሀትሪክ፡- …ከላይ ምላሽ ስትሰጠኝ…
ስኹል ሽሬ…ከሊጉ ከመውረድ የተረፈው
በስራና በስራ ብቻ እንደሆነ አስረግጠህ ምላሽ
ሰጠኸኛል…፤…ብዙዎች ግን የስኹል ሽሬ
ከሊጉ የመውረድ አደጋ መትረፉን…ከሌላ ነገር
ጋር ያያይዙታል…?…ይሄን….ሰምተሃል…?

ሳምሶን፡- …(ኮስተር ብሎ)…
አልሰማሁም…!…የእኛ ከመውረድ መትረፍ…
ከሰራ ውጪ ደግሞ…ከምን ጋር ተያየዘ…?…
(ሣቅ)…እስቲ ከአንተ ልስማ…?

ሀትሪክ፡- …ስኹል ሽሬ…ከሊጉ
የመውረድ አደጋ የተረፈው በላቡ ባገኘው
ውጤት ሳይሆን…የ28ኛው ሣምንት
ተፋላሚው ከሆነው ከወልዋሎ አዲግራት
ጋር በተደረገው ጨዋታ ደጋፊው በፈጠረው
ተፅዕኖና ረብሻ ምክንያት ባገኘው ነጥብ ነው…
ብለው ሙግት የሚገጥሙ…አሉ ይሄንን
ትቀበለዋለህ…?

ሳምሶን፡- …(ሣቅ)…በፍፁም
አልቀበለውም…!…ሰዎች የፈለጉትን
ሃሳብ የመሰንዘር መብት እንዳላቸው
ባምንም…ይሄንን አባባል ግን በፍፁም
አልቀበለውም…፤…እንደውም እንደዚህ
አይነቱ የተሳሳተ ድምዳሜ…የቡድናችንን
ልፋትና…በድካሙ ያገኘውን ውጤት
ለማጣጣል…የእኔንም ውጤታማ ሥራ
አውቅና ላለመስጠት ተፈልጎ የሚወራ ተራ
ወሬ ነው…፡፡…ከወልዋሎ ጋር በሜዳችን
ያደረግነው ጨዋታ 28ኛው ሣምንት ላይ
ነው…፤…እኛ ግን እንደማንወርድ ፍንጭ
ያገኘነው…ከዚህ ጨዋታ በፊት ነው…፡፡…
ስኹል ሽሬ የተረፈው ወልዋሎን በማሸነፉ
ብቻ ሣይሆን ላለመውረድ በሚደረገው
ትንቅንቅ ውስጥ ያሉና በዚህ ቀጠና ውስጥ
የእኛ ተፎካካሪ የሆኑ ቡድኖችን በሜዳችንም
ከሜዳችንም ውጪ በማሸነፍ የመውረድ
ጭንቀቱንና ስጋቱን ለእነሱ ትተን ልዩነቱን
አስፍተን ርቀን የተቀመጥንበት ሁኔታ
በልፋታችን ከመውረድ እንደተረፍን አንዱ
ማሣያ ነው። ከዚህ ውጪ ቡድኑ በተፅዕኖ ነው
የተረፈው የሚለው እውነታውን ለመቀበል
ካለመፈለግ እንጂ የእኛ መትረፍ ከምንም ነገር
ጋር አይያየዝም፤ እኛ ከመውረድ የተረፍነው
ከወልዋሎ ጨዋታ በፊት ነው፤ እንደዚህ
አይነቱን መሠረተ ቢስ ወሬ ከወሬነት የዘለለ
ፋይዳ ስለሌለው አልቀበለውም፡፡

ሀትሪክ፡- …አንዳንዶች ይሄን
አባባላቸውን በማስረጃ አስደግፈው ለማቅረብ
ሲሞክሩ…፤…ወልዋሎ እስከ 70ኛው ደቂቃ
1ለ0 ሲመራ ቆይቶ ጨዋታው በረብሻ
ምክንያት ለደቂቃዎች ከተቋረጠ በኋላ…
ሁለት ጎል አግብታችሁ ማሸነፋችሁ አሳማኝ
አይደለም በሚል ጉዳዩን ከተፅዕኖና ከሌላ
ነገር ጋር ለማየያዝ ለሚሞክሩ መልስህ
ምንድነው…?

ሳምሶን፡- …አንድ ያለው እውነት
ምንድነው…ጨዋታው አልተረበሸም
አልልህም…የተረበሸበት ሁኔታ ነበር…፤…
ደጋፊዎች ለተወሰኑ ደቂቃዎች…ወደ ሜዳ
በመግባታቸው ምክንያት ተቋርጧል…፡፡…
ግን ደጋፊው ወደ ሜዳ የገባው…ወልዋሎዎች
ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ ሣይሆን…
የእኛንም ተጨዋቾች በመቃወም ጭምር
ነው…፤…ደጋፊው…ተጨዋቾቻችን…
በሜዳ ላይ ሲያሳዩት የነበረው እንቅስቃሴ
አላጠገባቸውም… በዚህ የተነሣ “…ከአቅም
በታች ነው እየተጫወታችሁ ያላችሁት…፤…
እንደምንፈልገውና…ለውጤት የሚረዳ
እንቅስቃሴ አላደረጋችሁም…” ብሎ ደጋፊው
የራሱን ተጨዋች ሣይቀር ሲቃወም ነው
የነበረው…፡፡…ምናልባት ከተፈጠረው ችግር
በኋላ የተቆጠሩትን ሁለት ጎሎች… ከተፅዕኖ
ጋር ለማያያዝ ተሞክሮ ካልሆነ በስተቀር…
ጨዋታው ላይ ተፅዕኖ ስለመኖሩ፣ያሸነፍነው
ከእግር ኳሱ ሕግ ውጪ ነው በሚል በዳኞችም
በኮሚሽነሮችም ወይም በቪዲዮ ተቀርጾ የቀረበ
ምስልም ሆነ ክስ የለም፡፡

ሀትሪክ፡- …አንተን…በግልህ ልጠይቅህ…
ሁለቱ ጎሎች ከተፅዕኖ ውጪ…በትክክለኛው
መንገድ የተቆጠሩ ናቸው ትላለህ…?

ሳምሶን፡- …ነገርኩህ…እኮ…ምን አይነት
ጥያቄ ነው የምትጠይቀኝ…?…ደግሞም እኮ
የምናወራው አማርኛ መሰለኝ…!…(ኮስተር
ብሎ)…ምንም ጥርጥር የለውም…!…ጎሎቹ
የተቆጠሩት በትክክለኛው የጨዋታ ሕግና ሕግ
ብቻ ነው…፡፡…አንድ አንድ ጊዜ…ምን አለ…
መሰለህ…ነገሮችን የማመሳሰል… እውነታውን
ላለመቀበል ከመፈለግ የተፈጠረ ችግር ካልሆነ
በስተቀር የተቆጠሩት ሁለት ጎሎች ላይ
የሚነሳ ጥያቄ አለ ብዬ አላምንም…፤…
ብዙዎች ስለተቆጠሩት ጎሎች ተገረሙ
እንጂ…ያገኘነውን ፔናሊቲ እኮ ሳንጠቀምበት
አመከነው እንጂ የጎሎቹ ቁጥር ከዚህም ከፍ
ሊል ይችል እንደነበር ነው የማምነው…፤…
ይሄንንም…ከአሉባልታ ውጪ…ቁም ነገር
ያለው አስተያየት ነው ብዬ አልቀበለውም…፡፡
ሀትሪክ፡- …ደጋፊው ወደሜዳ በመግባቱ
ከተፈጠረው የጨዋታ መቋረጥ ውጪ…
አንተ የአሰልጣኝነት ኤቲክሱን በጣሰ መልኩ
የወልዋሎ አዲግራት አሰልጣኝ የሆነውን
ዮሐንስ ሣህሌን…በፀያፉ ቃላቶች ከመዝለፍ
በዘለለ እስከመማታትም ደርሰሃል… በሚል
ስምህ በክፉ እየተነሣ ነው…፤…እውነት
ይሄን አድርገሃል…?…እስቲ እውነታውን
ከአንደበትህ ልስማው…?

ሳምሶን፡- …(ሣቅ)…ይሄንን ወሬ እኔም
ሰምቼ በጣም ነው ያዘንኩት…(ድንገት
ኮስተር ብሎ)…እውነቱን ልንገርህ…እንዲህ
በመወራቱም በጣም ነው የማዝነው…?…
እንደዚህ ብለው የሚያወሩ ሰዎች ፍላጎታቸው
ምን እንደሆነም አይገባኝም…፤…እኔ…
ዮሐንስን ለመደብደብ እጄን ልሰነዝር…?…
በጣም…. ነው…የሚያስዝነው…

ሀትሪክ፡- …በዚህ መልኩ…
ሸፋፍነህ እንደትመልስልኝ…ሣይሆን…
አድርገሃል…?…አላደረክ…?… ለሚለው
ትክክለኛውን ምላሽ…እንድትሰጠኝ ነው…
የምፈልገው…?

ሳምሶን፡- …ልነግርህ እኮ ነው…!…
እኔ ዮሐንስን…ልደበድብ…?…መደብደቡን
ተወውና…ሰውን መዝለፉ…ክብር መንካት…
የእኔ መገለጫዎች አይደለም…፤…
የተጨዋችነትም ሆነ የአሰልጣኝነት ታሪኬን
ወደ ኋላ ሄደህ ብትፈትሽ…በዚህ ደረጃ የወረደ
ተግባር ውስጥ አለመገኘቴን ትረዳለህ…፤…
…እንደዚህ አይነቱ ስነ ምግባርም መገለጫዎቼ
አይደሉም…፡፡…በጣም የሚገርምህ ዮሐንስ
ሳህሌን እንኳን ልደበድብ…በሙሉ አይኔ
እንኳን የማላየው…በጣም የማከብረው…
ትልቅ ቦታ የምሰጠው… የቅርብ ወዳጄ
ነው…፤…በዚህ ደረጃ…የማየውን ሰው…
እንዴት ነው የምደበድበው…?…በጣም
የሚገርምህ…ወሬውን እኔ ራሴ ስሰማው
በጣም ተጋኖ ነው የተነገረኝ…፤…ከዮሐንስ
ጋር ከመነጋገር በዘለለ ልንገዳደል እንደነበረ
ነው የሰማሁት…፤…በዚህ በጣም…
በጣም ነው…የማዝነው…፡፡…እኔ ዮሐንስን
የምደበደብ ሣልሆን…ከእሱ ብዙ የምማር ሰው
ነኝ…፡፡…ምናልባት በጨዋታው ስሜታዊ
የሚያደርጉ የጨዋታውን መልክ የሚቀይሩ
ነገሮች በሜዳ ላይ ይታዩ ነበር…እነዚህን
ነገሮች ልቀበላቸው ያልቻልኩበት ሁኔታ
ነበር…፤…ከዚህ ውጪ…በሁለታችንም በኩል
ውጤትን አጥብቆ ከመፈለግ አንፃር በስሜት
የተነጋገርንበት ሁኔታ ተፈጥሮ ካልሆነ
በስተቀር…እስከመደባደብ የደረስንበትን
አላስታውስም…፡፡…ከወንድሜም ጋር
በተቃራኒ ቡድን ብንገናኝ ለውጤት ሠላማዊ
ትንቅንቅ ከማድረግ ወደ ኋላ አልልም…ከዚህ
ውጪ…አሁንም የአሰልጣኝ ዮሐንስ አክባሪና
ወዳጅ እንደሆንኩ…እንዲሁም…በሚነገረው
ደረጃም የተፈጠረ ነገር እንደሌለ…በዚህ
አጋጣሚ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ…፡፡
ሀትሪክ፡- …አሁን ደግሞ ከወልዋሎ
ወጥተን…ወደ ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ…
ከፋሲል ከነማ ጋር ወደ አድረጋችሁት
ጨዋታ እንግባ…፤…ሱኹል ሽሬ ከፋሲል
ከነማ ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ የገባው
የመቐለ 70 አንደርታን የዋንጫ ተስፋ
እውን ለማድረግ ተልዕኮ ወይም ውክልና ይዞ
ነው የገባው በሚል ትታማላችሁ…ሀሜቱን
ትቀበለዋለህ…?

ሳምሶን፡- …(በጣም ሳቅ)…የምን
ተልዕኮ…? የምን ውክልና…እንደሆነ ነው
ግራ የገባኝ…እንጂ ወሬውን እኔም እንደ
አንተ ሰምቼ በዚህም በጣም አዝኛለሁ…፤…
እንደዚህ አይነቱ የደከመ ወሬ እኔንም
ክለቡንም የማይገለፅ ተራ የአሉባልተኞች ወሬ
ነው…፤…ሰዎች ከምን ተነስተው…እንደዚህ
አይነት የክፋት ወሬን እንደሚያወሩ ለእኔ
አይገባኝም…

ሀትሪክ፡- …ሱኹል ሽሬ ከመውረድ
አደጋ ቀድሞ መትረፉን በማረጋገጡ የፋሲል
ከተማን ጨዋታ ቢያሸንፍም ቢሸነፍም ምንም
የሚጠቅመው ነገር የለም…፤…ነገር ግን
መቐለ 70 አንደርታ ዋንጫ እንዲወስድ…
ፋሲልን ከዋንጫ ውጪ ለማድረግና ነጥብ
ለማስጣል ነው ወደ ሜዳ ቆርጦ የገባው
በግል ጉዳዩን ወደ ሌላ ነገር ያያይዙታል…
ጉዳዩ የአደባባይ ወሬ ሆኖ ከመወራቱ የተነሳ
ትክክለኛውን ምላሽ ከአንተ ለማግኘት
ነው ያነሳሁልህ…?…ይሄንን ወቀሳስ
ትቀበለዋለህ…?

ሳምሶን፡- …ለእንደዚህ አይነት ተራ
አሉባልታ መልስ ባልሰጥህ ደስ ይለኛል…፤…
ነገር ግን የስፖርት ቤተሰቡ ጋ ብዥታ
እንዳይኖር ስል ብቻ እመልስልሃለሁ…፤…
ምክንያቱም ወሬው እኔም ጋ ስለደረሰ፡
፡ …በመጀመሪያ ደረጃ…እኔ በእንደዚህ
አይነቱ የረከሰ ተግባር ላይ የተሰማራሁ
አሰልጣኝ አይደሁም…፤… እንደዚህ አይነት
ወንጀል ፈፅሜም…ሙያዬንም የስፖርት
ቤተሰቡንም የምክድ አይነት ሰውም…
አይደለሁም…፡፡…በአጭሩ የእንደዚህ አይነቱ
የወረደ ነገር ተባባሪም አዛዥም አለመሆኔን
እንድታውቅልኝ እፈልጋለሁ…፡፡…ደግሞም
መቐለ 70 አንደርታ ዋንጫ መውሰድ ያለበት
በላቡ በድካሙ እንጂ በሱኹል ሽሬ ድጋፍ
ነው የሚል እምነት የለኝም…፡፡…ፋሲልም
ዋንጫ ለመውሰድ አቅሙን መጠቀም እንጂ
ከሰው በሚደረግለት ድጋፈ ነው ብዬም
አላምንም…፤…እንደውም በጣም የሚገርምህ
ሱኹል ሽሬ ስሙ በወቀሳ መልክ ሳይሆን
በምስጋና ነበር መነሳት የነበረበት…

ሀትሪክ፡- …ማለት…?

ሳምሶን፡- …ውጤቱ ለሱኹል ሽሬ
ጠቀመው አልጠቀመው ለክለቦቹ ሣይሆን
ለስፖርቱ ሕግ ወገኖ በመጫወቱ በአርአያነት
ልንነሳ ልንመሰገን እንጂ ልንወቀስ ይገባል
ብዬ አላምንም…፤…ከፋሲል ጋር አቻ
መውጣታችን እንደ ትልቅ ውጤት ቆጥሮ
ሌላ ስም ከመስጠት በፊት ሱኹል ሽሬ
በሁለተኛው ዙር በሜዳው ያደረጋቸውን
ጨዋታዎች፣የነበረውን ጥንካሬ መፈተሽ ከዚህ
አይነቱ ሥህተቶች ያድናል፡፡ በለሁተኛው ዙር
ከቅድስ ጊዮርጊስና ከፋሲል ከነማ ጨዋታ
ውጪ በሜዳችን ያደረግናቸውን ጨዋታዎች
በሙሉ አሽንፈናል፤ምናልባት በሜዳው ሲሸነፍ
ነጥብ ሲጥል የነበረ ቡድን ሆኖ ለፋሲል
ጨዋታ እለት የተለየ ጠንክሮ ገብቶ ነጥብ
የተጋራንበት ሁኔታ ቢፈጠር ኖሮ ከተባለው
ጋር ሊቀራረብ ይችላል፡፡ ግን ምንም በሌለበት
በሁለተኛው ዙር በተለይ በሜዳው በጥንካሬና
በአሸናፊነት የሚታወቅን ቡድን አቻ ስለወጣና
ነገሮች ስለተገጣጠሙ ተልዕኮ ይዞ ገብቶ ነው
ብሎ ሌላ ስም መስጠት ለእኔ እግር ኳሳዊ
አይደለም፡፡ ደግሞም ለፋሲል ዋንጫ ማጣት
መወቀስ ያለበት እጁ ላይ ያለውን እድል
በአግባቡ ያልተጠቀመውን እንጂ ነገሮች ወደ
እኛ መምጣት አለባቸው ብዬ አላምንም፡፡
ለማንም ሳንወግን ለእግር ኳሱና ለስፖርታዊ
ጨዋነት ወግነን ንፁህ ጨዋታ ተጫውተን
በመውጣታችን መወቀስ ሣይሆን መመስገን
ነው ያለብን፡፡

ሀትሪክ፡- …ግልፅ ባለ ቋንቋ ስናወራ…
ሱኹል ሽሬ የመቐሌ 70 አንደርታን ውክልናን
ይዞ አልገባም እያልከኝ ነው…?

ሳምሶን፡- …ነገርኩህ እኮ…!…ለምን
ደጋግመህስ…ትጠይቀኛለህ…?…እኔ አሁን
ግራ የገባኝ…በእለቱ ጨዋታ ከእኛ ምን ነበር
የተፈለገው…?…ገና ለገና ክለባችን ከመውረድ
ተርፏል ወይም ነጥቡ አይጠቅመንም ብለን
መልቀቅ ነበረብን…?…የተፈለገው ይሄ…
ነበር…?…ለፋሲል ለቀን ፋሲል ዋንጫ ቢወስድ
ነበር ትክክል የሚሆነው…?…እኔ ነገሮች ሁሉ
ፍፁም አልገቡኝም…፤…ለምን በዚህ ደረጃ
ማሰብና ነገሮችን ማወሳሰብ እንደተፈለገም…
ለእኔ ግልፅ አይደለም፡፡…ለአንተም ይሄን
ወሬ ለሚያራግቡም…ሱኹል ሽሬ በዕለቱ
ጨዋታ ምንም አይነት ተልዕኮ ይዞ ወደ ሜዳ
አልገባም… በሁለተኛው ዙር ከሌሎች ጋር
ሲያደርገው በነበረው አይነት አጨዋወትና
የማሸነፍ ስሜት ወደ ሜዳ እንደገባ ነው
አስረግጬ ልነግራችሁ የምፈልገው፡፡ ስራችንን
ከመሰረት ውጪ ማንንም ለመጥቀምም
ለመጉዳትም አለመጫወታችንን የስፖርት
ቤተሰቡ እንዲያውቅልን እፈልጋለሁ፡፡
የቡድኑን፣ የአልጣኞችና የተጨዋቾች ልፋት
ጥላሸት ለመቀባት…የፖለቲካ ንግድ ነግደው
ማትረፍ የሚፈልጉ ሰዎች የሚያስወሩት
ተራ ወሬ ነው…፤…አሁን እግር ኳሳችን
ለከፋ አደጋ እየተጋለጠ የመጣው ከሜዳ
ውጪ በሚፈጠሩ የግለሰቦች ፍላጎትና
ውዥንብሮችም ነው፡፡ የእግር ኳሱን ሠላም
የመንናፍቅ ከሆነ እንደዚህ አይነት የበሬ ወለደ
ዘመቻዎችን መዋጋቱ ነው የሚጠቅመን፡፡
ሀትሪክ፡- በዕለቱ ጨዋታ 1ለ0 ስትመሩ
ቆይታችሁ በተሰጣችሁ የፍፁመ ቅጣት
ምት ነው አቻ የወጣችሁት፤ ፔናሊቲውን
የተጠራጠሩ አሉና በአንተ እይታ ፔናሊቲው
የሚያሰጥ ነው?

ሳምሶን፡- …በጣም ያሰጣል…!…
ራሣቸው ፋሲሎችም ፔናሊቲውን አስመልክቶ
ያቀረቡት ተቋውሞ የለም…፤…ይሄንን
ደግሞ በቦታው የነበሩ ሚዲያዎች፣የዕለቱ
ኮሚሽነሮችም አይተው የተባለ ነገር የለም፡፡
ሌላውን ተወውና የፌዴሬሽኑን ፕሬዝዳንትም
እኮ በክብር እንግድነት ተገኝተው ጨዋታውን
ታድመዋል…፤…ከስፖርቱ ሕግ ውጪ
የተፈፀመ ነገር ቢኖር…ለእግር ኳሱ
ሲሉ ዝምታን አይመርጡም ነበር…፤…
ፔናሊቲውን አስመልክቶ አንድም የተነሣ
ተቃውሞ አላየሁም…፡፡…በትክክልም
የሚያሰጥ ነው፤…ፔናሊቲውን ተወው
በሁለተኛው 45 እኮ ፋሲሎች በጣም
ወርደው በመምጣታቸው በጣም
ተጭነናቸው ነው የተጫወትነው…እነሱ
በ3ኛው ደቂቃ በጠዋት ግብ አስቆጥረው
ያንን አስጠብቀው ባለመውጣታቸው…
ለምን እኛ እንደምንወቀስ አይገባኝም…፡፡

ሀትሪክ፡- …የሁለታችሁ ጨዋታ
ከተጠናቀቀ በኋላ የአሰልጣኝ ቡድን
አባላትና ተጨዋቾች በጣም ጨፍራችኋል
ደንሳችኋል ተብሏል…፤…መደሰት
መብታችሁ ቢሆንም…ውጤቱ ለእናንተ
የሚፈይደው ነገር አለመኖሩ እየታወቀ
እንደዛ በደስታ የቦረቁት መቐለ 70
አንደርታ ዋንጫ በመውሰዱ ነው ብለው
ጉዳዩን ከሌላ ጋር የሚያያይዙ አሉ…
በዚህ ዙሪያስ ምን ትላለህ…?

ሳምሶን፡- …(ከት ብሎ ሳቀ)…
እንዴ…ምን ማለት …ነው?…ላንደሰት
ልንጨፍር ነው እንዴ…? ቡድናችን
በተለይ በሜዳው ከጨዋታ በኃላ
ሲደሰትና ሲጨፍር ይሄ የመጀመሪያ
አይደለም…፤…በሁለተኛው ዙር በተለይ
በሜዳችን ብዙ የደስታና የጭፈራ
ጊዜያትን አሳልፈናል፡፡…ለምን ከፋሲል
ጋር በነበረው ጨዋታ የነበረውን ደስታ
ብቻ መምዘዝ እንዳስፈለገ አልገባኝም…፡
፡…አንዳንዴ የሚባለውና የሚወራው
ነገር የሚያስቅ እየሆነብኝ ነው…
(ሣቅ)…፡፡…ቡድናችን ከወራጅ ቀጠና
የተረፈበት የአመቱን ውድድር የመዝጊያ
ጨዋታ ከጠንካራውና የዋንጫ ትልቅ
ተስፋ ከነበረው ፋሲል ጋር ተጫውቶ
በጥሩ ውጤት በማጠናቀቁ ተጨዋቾቹ
በደስታ ቢጨፍሩ ኃጢአቱ ምንድነው…?
ከሊጉ እንወርዳለን ብለው ሲሰጉ የነበሩ
ተጨዋቾች አመቱን በተሻለ ውጤት
በመዝጋታቸው በመደሰታቸው ሣይሆን
ሊገርመን የሚገባው ባይደሰቱ ነበር፡
፡ የአሰልጣኞች ቡድን አባላትም ስትቦርቁ
ስትጨፍሩ ነው ለተባለው…አልቦረቅንም እንጂ
ሁለተኛውን ዙር ለተሻለ ውጤትና መጥፎ
ታሪክ እንዳይመዘገብ ሲጨነቅ እንቅልፍ
ሲያጣ ለነበረ አሰልጠኝ ከዚህ ቀን የተሻለ
የመጨፈሪያና የመቦረቂያ ቀን አለው ብዬ
አላስብም፡፡ በማይታመን መልኩ የአመራሩ፣
የኮቺንግ ስታፉ፣ የተጨዋቾች፣ የደጋፊው
ህብረትና ርብርቦሽ ክለባችንን ከመውረድ
በማትረፋችን አልጨፈርንም እንጂ ብንጨፍር
እንኳን ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይገባም፡
፡ሻምፒዮን መሆን ግቡ የሆነ ህልሙን
ለማሣካት የሆነን አካል መደገፍ ወይም ካለፈ
በኋላ አሉባልታ መንዛት ሣይሆን ስራ ላይ
ማተኮር ነበር የሚገባው፤ የፈለገ የወሬ ዘመቻ
ቢከፍቱ የአንድ ሰሞን ወሬ ከመሆን የዘለለ
ፋይዳ ስለሌለው…ለሚባለው ነገር ብዙም ቦታ
አልሰጠውም…፤…ዘመቻውን የከፈቱትም
አንድ ቀን ትዝብት ላይ መውደቃቸው
አይቀርም…፡፡

ሀትሪክ፡- …እስቲ ዛሬ ላይ ሆነህ አንድ
ጥያቄ ልጠይቅህ… ለዋንጫ አንድ እጁን
የዘረጋው ፋሲል ከነማ በአንተ አሰልጣኝነት
የሚመራው ቡድን ነጥብ አስጥሎት ዋንጫ
በማጣቱ የሚፀፀትህ…?…የሚሰማህ.. ነገር
አለ…?

ሳምሶን፡- …እንዴ…ለምን እፀፀታለሁ…
?… ለፀፀት የሚያበቃ ምን መጥፎ ነገር
ሰርቼ ነው እስከ መፀፀት የምደርሰው…?…እኔ
እስከሚገባኝ ድረስ ለፀፀት የሚዳርግ አንዳችም
የሠራሁት ሥራ የለም…፡፡ ነጥቡ ጠቀመን
አልጠቀመን…የስፖርቱ ሕግ፣የስፖርታዊ
ጨዋነት መርሀ አጥብቆ የሚጠይቀውን
ነው አድርገን የወጣነው፡፡ በሁለተኛው ዙር
በተለይ በሜዳችን ያደረግናቸውን ጨዋታዎች
የመፈተሽ እድል ያገኘ…የሠራነው
አንዳችም ሥህተትና ወንጀል እንደሌለ ያለ
ነጋሪ ይረዳል…፡፡…ለእግር ኳሱ ለሙያዬ
ታማኝ ሆኜ በመውጣቴ ህሊናዬን ሠላም
የሚነሣ…፣…ለፀፀት የሚዳርገኝ አንዳች ነገር
የለም፡፡ ግን በዚህ አጋጣሚ አንድ ማንሣት
የምፈልገው ነገር እግር ኳሱ ከሜዳ ላይ
ጨዋታ ወጥቶ የፖለቲካ ሹኩቻ ውስጥ ገብቶ
አላስፈላጊ ትርጉም እየተሰጠ እግር ኳሱን
በሚያቀጭጩ ነገር ላይ እየተጠመደን ነው፤
በእግር ኳስ ቋንቋ በግልፅ ስናወራ…እነዚህ
ነገሮች ላይ ብንተራረም መልካም ነው…፤…
ከሜዳ ላይ ጨዋታ ወጥተን ስለ ዘር፣ ስለ
ፖለቲካ፣ ስለመከፋፈል፣ ስለ ጥላቻ እያወራን
የነገ የእግር ኳሱ ተተኪ የሆኑ ወጣቶች
ላይ መጥፎ ዘር ዘርተን እንዳናወርሳቸው፤
ቀጣዩን ትውልድ የዚህ ችግር ሠለባ አድርገን
እንዳንቀርፃቸው ነው የምሰጋው። የሚሻለው
ለአላስፈላጊ ወሬዎች፣ እግር ኳስ… እግር ኳስ
ለማይሸቱ ነገሮች ሳንመቻች ለእድገቱ ብንሰራ
ይሻላል የሚል ነው እምነቴ….

ሀትሪክ፡- …ቀደም ሲል ሐረር ቢራና
ዳሽን ቢራን በፕሪሚየር ሊግ አሰልጥነህ
አልፈሃል…፤…ሱኹል ሽሬን ስታሰለጥን
ምን የተለየ ነገር አይህበት…?…የነበረህ የስራ
ነፃነትስ…?

ሳምሶን፡- …በሱኹል ሽሬ የነበረኝ የሥራ
ነፃነት ምን ይመስል እንደነበር በመናገር
ቃላቶችን ማባከን ያለብኝ አይመስለኝም…
(ሳቅ)…፤…ምክንያቱም የተመዘገበው ውጤት
በራሱ ጥሩ የሥራ ነፃነት እንደነበረኝ አፍ
አውጥቶ ይመሰክራልና፡፡…ሙሉ የሥራ
ነፃነት…ሙሉ መብት ስለነበረኝ ነው በነፃነት
ሠርቼ ይሄ ውጤት የተመዘገበው፤የክለቡ
ኃላፊዎችም ዋንጫ ከማግኘት በራቀ
የሀገር እግር ኳስ እድገት የሚያሳስባቸውና
የሚያስጨንቃቸው ፍፁም ተባባሪና አጋዥ
ሆነው ነው ያገኘኋቸው…፤…ውጤት ሲኖርም
ሳይኖርም…በአቅማቸው አለሁ ሲሉህ ነው
የምታየው…፡፡…ሌላው በዚህ አጋጣሚ
ሳላነሳው የማላልፈው ነገር ስለአካባቢው
ህዝብና ስለደጋፊው ነው፤እውነት ለመናገር
ያለምንም ማጋነን የሱኹል ሽሬ ህዝብ
ስፖርት ወዳድና ለእግር ኳስ ራሱን የሰጠ
እውነተኛ ደጋፊ መሆኑን ከዚህ በፊት እሠማ
ነበር ወደ ክለቡ ከመጣሁ በኋላ ያየሁትና
ያረጋገጥኩት ቀደም ሲል የሰማሁት ሁሉ
አለመጋነኑንና እውነት መሆኑን ነው፡፡በድል
ጊዜ ብቻ ሣይሆን ውጤት ሲጠፋም አብረውህ
ሲሆኑ ስለምታያቸው ክለብ መደገፍና ክለብ
መውደድ ምን እንደሚመስል በእነሱ ላይ
ታያለህ፡፡አሁን ቡደኑ ከመውረድ በመትረፉ
በከተማው መነቃቃት ተፈጥሯል… ለዚህ
ደጋፊ የበለጠ ነገር ለመስጠት ከአሁኑ
በመማር ለቀጣይ ብዙ የመስራት ግዴታ
ውስጥ ገብተን ከወዲሁ የተለያዩ የማጠናከር
ሥራዎችን መስራት ጀምረናል፡፡

ሀትሪክ፡- …ቀጣይ… ዕቅድህ ምንድ
ነው…?

ሳምሶን፡- …እንግዲህ የአመቱን ውድድር
ገና መጨረሻችን ነው… ያም ቢሆን ግን
ስለቀጣይ ማሰባችን አላቋረጥንም…፤…
በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከገጠሙን
ድክመቶች ተምረን…ጥንካሬያችንን ይበልጥ
አጎልብተን ብዙ ሰርተን በ2012 የውድድር
ዘመን ወራጅ ቀጠና ከሚለው የደካማነት
መገለጫ ወጥተን ጠንካራና ተፎካካሪ
የሚያስብለንን ጥሩ ቡድን በሜዳችንም
ከሜዳችንም ውጭ ገንብተን ለመቅረብ
እንዲሁም በተለይ በሜዳችን ላይ የገነባነውን
አሸናፊነት የሚያስቀጥል ቡድን ለመገንባት
ቀጠሮ ሳንሰጥ ከወዲሁ ሥራ ጀምረናል፡፡

ሀትሪክ፡- …የሱኹል ሽሬን ቡድን
በሁለተኛው ዙር ተረክበህ ያመጣኸውን
ውጤት የተመለከቱ… እንደዚህ አይነት
ውጤታማ ሥራ የሚሠራ ከሆነ…እስከዛሬ
እንዴት ከስልጠና ርቆ ሊቀመጥ ቻለ…?…
በማለት በግርምት ጥያቄ የሚያነሱ አሉ…
ለጥያቄው ምን ትላለህ…?

ሳምሶን፡- …(እንደ መሳቅ እያለ)…ይሄ
የብዙዎች ጥያቄ ነው…፤…እኔ ከስልጠና
ርቄ የተቀመጥኩት የአቅም ችግር ኖሮብኝ
አይደለም…፡፡…የአቅም ችግር እንደሌለብኝ
በፕሪሚር ሊግ ደረጃ በሐረርና ዳሽን ቢራን
ሳሰለጥን የገነባኋቸውን ቡድኖች የስፖርት
ቤተሰቡና ሜዲያው ጭምር የሚያውቀው
የሚመሰክረው ጉዳይ ነው…፡፡…ግን
እንደምታውቀው አሁን አሁን በሀገራችን ክለብ
ለማሠልጠን መመዘኛውና መስፈርቱ አቅም
አለው…?…ውጤቱስ…ምን ይመስላል…?…
ከሚለው ይልቅ ማንን ታውቃለህ…?…ምን
ትለቃለህ…? በሚል መጥፎ
ቅኝት የተቃኘ በመሆኑና…
እኔም በዚህ የተጨማለቀ
መስመር ውስጥ መግባትን
በመጠየፌ መስራት እየቻልኩ
ከምወደው ስልጠና ርቄ
ለመቀመጥ ተገድጃለሁ…፡
፡…በሽሬ በሁለተኛው ዙር
ያስመዘገብኩትን ውጤት
አይተው ብዙዎች ሲገረሙ
አያለሁ… ይህ ውጤት ግን…
ትናንት ከትናንት ወዲያ…
በሐረር ቢራና በዳሽን ቢራ
ቡድን ውስጥ ሳደርገው
የነበረው ነው…።…ሐረር
ቢራን በታሪክ ለመጀመሪያ
ጊዜ በፕርምዬር ሊጉ
ሳሰለጥን በመጀመሪያ አመት
በተለይ በአንደኛው ዙር
ለሻምፒዮናነት ከሚፎካከሩ
ክለቦች ተርታ አድርጌ ነው
የጨ ረ ስ ኩ ት … ፤ … በ ዳ ሽ ን
ቢራም በነበረኝ ቆይታ
ጥሩ የኳስ ፍሰት ያለው…
ማራኪ ጨወታን የሚጫወት
ውጤታማና ጠንካራ ተፎካካሪ
ቡድን ነው የነበረኝ።…እነዛ
ተሞክሮዎቼ ናቸው በሱኹል
ሽሬ ጎልተው የታዩት፤…
ከዚህ ውጪ የብቃት ጥያቄ
በየትኛውም ክለብ ተነስቶብኝ
አያውቅም…፤…እንዳልኩህ
ግን ከስልጠናው እንድርቅ
ያደረገኝ ግልፅ ባለ ቋንቋ…
ስፖርቱ አካባቢ ያለ የቆሸሸ
አ ሠ ራ ር ና … ያ ል ተ ፈ ለ ጉ
ግንኙነቶች ሠለባ መሆኔ
ያመጣብኝ ጣጣ እንጂ…የአቅም ጥያቄ
ተነስቶብኝ አይደለም…፡፡…እኔ እንደውም
ራሴን ለእግር ኳሱ የተፈጠርኩ ሰው የሆንኩ
ያህል ነው የማስበው፡፡

ሀትሪክ፡- …የኢትዮጵያ እግር ኳስ
በዘር፣በፖለቲካ፣በጎሣ በተከፋፈሉ ወገኖች
ለከፋ ስቃይ መዳረጉን እንዴት ነው
የታዘብከው…?

ሳምሶን፡- …ስለዚህ ነገር ሳስብ በጣም
ነው የማዝነው ብቻ ሳይሆን በጣምም ነው
የሚያሰጋኝም…፤… በራሳችንም በሌሎች
የአለማችን ሀገሮች እንደምናየው…ከታሪክም
እንደምንረዳው ስፖርት በተለይ እግር ኳስ
የጦርነቶች ማቆሚያ፣የፀቦች ማብረጃና
ማስታረቂያ፣የተራራቁትን ማቀራረቢያ
የሆነ…የሠላምና የፍቅር መድረክ እንደሆነ
ነው…፡፡…ደግሞም የስፖርት እውነተኛው
ትርጉሙ ለወዳጅነት፣ ለሠላም ስለሆነ
በየትኛውም ሁኔታ በዚህ በኩል ያለው
ድርሻ የላቀ ነው…፤…ነገር ግን አሁን አሁን
በሀገራችን እየታየ ያለው አዝማሚያ…
እግር ኳሱን ብቻ ሣይሆን ይህቺን ትልቅ
ታሪክ ያላትን ሀገር ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ
የሚመራ ነው…፡፡…አሁን እግር ኳሱ ላይ
እየፈሰሰ ያለው ሀብት ሀገሪቷ ካላት አቅም፣
ሀገሪቷ ካለባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች አንፃር
ሲታይ ስፖርቱ አተረፈ…፣…ለሀገር አመጣ
የምንለው ነገር ኢሚንት ነው…፡፡…ስፖርቱ
አንድነታችንን የሚበታትን…በዘር፣ በሠፈር፣
በመንደር እየተከፋፈልን ለከፋ ችግር እየዳረገን
ከመሆኑ አንፃር በጣም ያሳስበኛል…፡፡
…አሁን እኛ ካደረግነው የ30ኛ ሣምንት
ጨዋታ በኋላ…ከሌላው ጊዜ በተለየ እንቅልፍ
እየነሣኝ ያለው ነገር… ሰዎች በተሰጣቸው
ኃላፊነት ትኩረት ሰጥተው ከመስራትና
የሚፈልጉትን ከማግኘት ይልቅ የፖለቲካ
ትርፉ ወደሚያገኙበት አቅጣጫ በማዞር
ከዘር፣ከአካብቢ ጋር መነሻ እያደረጉ እግር ኳሱ
ለሀገር አንድነት ችግር እንዲሆን በሚያሳፍር
ሁኔታ ሲተጉ እያየሁ ያለሁበት ሁኔታ
መጪው ጊዜ በሥጋት እንዳስብ…ይሄ ነገር
ወዴት ነው የሚወስደን የሚል ፍራቻ እንደ
ሀገር እየፈጠረብኝ ነው፡፡…የያዝነው ዓመት
የፕርምዬር ሊግ ውድድር ከእነ ዘርፈ ብዙ
ችግሮቹ አልቋል…፤…በቀጣይ እግር ኳሱን
ከእነዚህ የኋላ ቀርነት አስተሳሰብ ውጤቶችና
ስልጣኔ የጎደላቸው ችግሮች ነፃ አውጥቶ
ማስቀጠል ካስፈለገ በቅን ልቦና፣ለላቀ ሃሳብ
በመገዛት፣ከሠፈር፣ከዘር፣ በፖለቲካ ከተቃኘ
ጠባብ አመለካከት በመውጣት መወያየት
መመካከር የግድ ይመስለኛል፡፡ አሁን በእግር
ኳሱ በደረሰው ሰው ሠራሽ ችግሮች ተምረን
እስካልተወያየን፣ በግልፅ ሳንመካከር ሸፋፍነው
የምንጓዝ ከሆነ ከሌላው ፖለቲካዊ ችግሮች
በተጨማሪ እግር ኳሱም ሀገር እንዲበታተን
ተጨማሪ ምክንያት እንዳይሆን ስጋቱ ስላለኝ
ጥንቃቄ ቢደረግ የሚል አቋም ነው ያለኝ…፡፡
…እግር ኳሱን የሚጫወቱትና የሚከታተሉት
በአብዛኛዎቹ የወጣቱ ክፍል በመሆኑ
ልዩ ትኩረት ይሻል…፤…አሁን አሁን
ስፖርቱን የፖለቲካ መጠቀሚያ የሚያደርጉ
አዝማሚያዎች እየታዩ ነው…፤…እግር ኳሱ
የፖለቲካ መፈንጫ፣ መናኸሪያ ለመሆን
እየተቃረበ ነው…፤…ስለዚህ የ2012
የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት መንግሥት
መግለጫ ከመስጠት በዘለለ የተለየ ትኩረት
ሊሰጠው ይገባል የሚል እምነት አለኝ…“…
ምነው…በእንቁላሉ…”እንደሚባለው ይሄ ክፉ
አዝማሚያ በቶሎ ካልተቀጨ እግር ኳሱ
ለሀገር አንድነት ሣይሆን ለሀገር መበታተን
ምክንያት እንዳይሆን የሚል ስጋት አለኝና
በደንብ ሊታሰብበት እንደሚገባ ነው አስረግጬ
መናገር የምፈልገው፡፡

ሀትሪክ፡-.. ለነበረን ጊዜ…፣…በድፍረት
ላነሳሁት አሉባልታ የሚመስሉ…ግን…
የብዙዎች መነጋገሪያ ለሆኑ ጉዳዮች…አንተም
በድፍረት መልስ ሰጥተህ ስላስተናገድከኝ…
በራሴና በአንባቢዎቼ ስም… አመስግኜ
ከመለየቴ በፊት…በመጨረሻ ቀረ የምትለው
ካለ ዕድሉን ሰጥቼህ…እንለያይ…?

ሳምሶን፡- …እውነት ለመናገር…
ቀረ የምለው እንኳን የለም…፤…
እኔም በአሉባልታ፣በወሬ ደረጃ ሰምቼ
ያዘንኩባቸውን…እኔንና ክለባችንን
የማይገልፁ ወሬዎችን አንስተህ ስለጠየቀኝ…
የስፖርትቤተሰቡጋ ጋር ያለው ብዥታ
እንዲጠፋ የራሱን ፍርድ እንዲፈርድ መድረክ
ስለፈጠርክ አንተንም ከልብ አመሰግናለሁ፤
እግዚአብሔር ያክብርልኝም እላለሁ…፡
፡…ሌላው የሚናፈሱትን አሉባልታዎች
በመስማት በማዘንና በመቆርቆር ስሜት
ስልክ በመደወል አጋርነታቸውን ያሳዩኝ
ወዳጆቼን…፤…ከስልጠናው በግፍ መገፋቴን
አይተው በቁጭት ሲብሰለሰሉ የነበሩና ይሄንን
ቀን ሲናፍቁ የነበሩ የስፖርት ቤተሰቦችና
ወዳጆቼ በሥራዬ ተደስተው ለሰጡኝ ድጋፍና
የሞራል ስንቅ…አነሱንም በዚህ አጋጣሚ
ላመሰግናቸው… እግዚአብሔር ይስጥልኝ
ልላቸው እወዳለሁ…፡፡