Category: አዳማ ከተማ

ሀብታሙ ወልዴ አዳማ ከተማን ተቀላቅሏል

 

በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር በንቃት እየተሳተፈ የገኘው ዳማአ ከተማ የክረምቱ ሥስተኛ ዝውውሩን ሀብታሙ ወልዴን ከድሬዳዋ ከተማ በማስፈረም እጠናቋል።

በድሬዳዋ ከተማ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን ያሳየው ሀብታሙ ወልዴ በያዝነው ውድድር ዓመት በጉዳት የታመሰውን የአዳማን እጥቂ ክፍልን ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።ከዚህ በፊት አዳማዎች የግራ መስመር ተከላካዩን እስናቀ ሞገስን ከባህርዳር ከተማ እንዲሁም ማካኙንአ አማኑኤል ጎበና ከወልዋሎ ማስፈረማቸው አሚታወስ ነው።በተያያዘ ዜና አዳማ ከተማ የነባር ተጨዋቾቹን ተስፋይ በቀለ፣ኤፍሬም ዘካርያስ እና እዲስ ህንፃ ውል ማራዘም ችሏል።

ሪፖርት | መቐለ 70 እንደርታ ወደ ዋንጫ የሚያደርገውን ግስጋሴ ያስቀጠለበት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል

በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ በሜዳው ትግራይ ስታድየም አዳማ ከተማን ያስተናገደው መቐለ 70 እንደርታ በአማኑኤል ገብረሚካኤል እና ያሬድ ከበደ አማካኝነት ባስቆጠርዋቸው ሁለት ግቦች ጣፋጭ ሥስት ነጥቦችን ማሳካት ችልዋል።

በ20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ በባህርዳር ከተማ ከተሸነፈው ቡድን ሥስት ቅያሬዎችን ማለትም ቢያድግልኝ ኤልያስን በስዩም ተስፋዬ፣ሄኖክ ኢሰያስን በአንተነህ ገብረክርስቶስ፣ጅብሪል መሐመድን በዮናስ ገረመው ሲቀይሩ አዳማዎች በኩላቸው በሃዋሳ ከተሸነፈው ቡድን ከንአን ማርክነህን በቡልቻ ሹራ፣ሱሌይማን መሐመድን በሱራፌል ዳንኤል በመቀየር ወደ ጨዋታው ገብተዋል።

ብዙ ሙከራዎች ባልታዩበት የመጀመርያው እጋማሽ በ4-4-2 ዳይመንድ አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት መቐለዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስደው ተጫውተዋል።መሃል ሜዳ ላይ ተደጋጋሚ የኳስ ቅብብሎችን ያደረጉት መቐለዎች ኳሶችን የሜዳው መጨረሻ ክፍል ላይ ማድረስ ሲቸግራቸው ታይቷል።የዚህም ማሳያ መጀመርያው 45 ላይ የፈጠርዋቸው የግብ ዕድሎች የተገኙት ከቆሙ ኳሶች ነበር፤ሚኪኤሌ ደስታ ከማአዘን ምት ያሻማው ኦሰይ ማውሊ በግምባሩ ገጭቶት ወደ ውጭ የወጣው በተመሳሳይ ሃይደር ሸረፋ ከቅጣት ምት በቀጥታ መትቶት ሮበርት ኦዱንካራ የያዘበት ተጠቃሽ የመቐለ ሙከራዎች ናቸው።የጨዋታ ብልጫቸውን ያስቀጠሉት ምዓም እናብሶቹ በ13ኛው ደቂቃ ፍጹም ቅጣት ሳጥን ላይ ምኞት ደበበ በኦሰይ ማውሊ ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት አማኑኤል ገብረሚካኤል እስቆጥሮ መቐለን መሪ ማድረግ ችልዋል።በ4-2-3-1 እሰላለፍ ቡልቻ ሹራን በእጥቂነት ያሰለፋት አዳማዎች የመጀመርያው እጋማሽ መጨረሻ ላይ በበረከት ደስታ እማካኝነት ያደረጓቸው ሙከራዎች በመቐለ 70 እንደርታው በረኛ ፊሊፕ ኦቮኖ ተመልሰዋል።

ድራማዊ ክስተቶችና ተደጋጋሚ ጥፋቶች በታየበት ሁለተኛው እጋማሽ እሁንም በተመሳሳይ መልኩ የመቐለ 70 እንደርታ ብልጫ የታየበት ነበር።በ4 ደቂቃ ልዩነት ውስጥ በተመለከቷቸው ሁለት ቢጫ ካርዶች የግራ መስመር ተመላላሹ ሱሌይማን ሰሚድን በ74ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ሊሰናበት ችሏል።ከቀይ ካርዱ ክስተት ሁለት ደቂቃዎች በኃላ ከግራ መስመር በኩል የተገኘውን ቅጣት ምት ወደ መቐለ የፍጹም ቅጣት ሳጥን ውስጥ አዳማዎች በአዲስ ህንጻ አማካኝነት እስቆጥረው አቻ መሆን ችለዋል።ከግቡ መቆጠር በኃላ ሙሉ ሀይላቸውን ማጥቃት ላይ ያሰማሩት መቐለ 70 እንደርታዎች በኦሰይ ማውሊ እና ያሬድ ከበደ እማካኝነት ሙከራዎችን ቢያደርጉም የአዳማን መረብ መድፈር አልቻሉም።

ሆኖም መደበኛው 90 ደቂቃ ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ሲቀሩት በአዳማ የፍፁም ቅጣት ሳጥን በግራ በኩል ዮናስ ገረመው ያሾለከውን ኳስ ኦሰይ ማውሊ መሬት ለመሬት ወደ ውስጥ ሲሻግረው ነጻ አቋቋም ላይ የነበረው የፊት መስመር ጥቂው ያሬድ ከበደ በቀላሉ አስቆጥሮ ሙሉ ስታድየሙን በደስታ አስፈንጥዟል።

ውጤቱን ተከትሎ መቐለ 70 እንደርታ ነጥቡን 45 በማድረስ ከተከታዮቹ ያለውን ነጥብ ልዩነት እስጠብቆ ወጥቷል።


የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 2011

PosClubPWDLFAGDPts
13018574817+2159
23017764329+1658
330151234816+3257
429121072818+1046
530121083336-346
630168104231+1144
730101193427+741
830101192731-441
930109112723+439
1029910101621-537
1130811112727035
1230109112934-5,35
1330713102939-1034
143088133757-2032
153078153437-329
163041252167-4613

የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ዛሬ 7ጨዋታዎች ሲያስተናግድ የተለያዩ ውጤቶች ተመዝግበዋል ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 ሲዳማ ቡና

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሁለት ድል እልባ ጨወታዎች በኃላ ወደ እሸናፊነት የተመለሰበትን ድል አስመዝግቧል።በሜዳው አዲስ እበባ ስታድየም ሲዳማን ያስተናገዱት ጊዮርጊሶች በኢሱፍ ብርሃነ ና እቡበከር ሳኒ ሁለት ግቦች ታግዞ ሙሉ ሥስት ነጥብን እሳክቷል።ድሉን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን 33 ሲያደርስ ሲዳማ ቡና ሁለተኛ ደረጃን ለፋሲል ከነማ እስረክቧል።


ደደቢት 2-3 ድሬዳዋ ከተማ

እምስት ግቦችን ያስተናገደው የደደቢት ና ድሬዳዋ ጨዋታ በእንግዶቹ ድሬዳዋ እሸናፊነት ተጠናቋል።የድሬዳዋ ሥስት የእሸናፊነት ግቦች ዘነበ ከበደ ና ረመዳን ናስር በመጀመርያው እጋማሽ ፍሬድ ሙሺንዲ በሁለተኛው እጋማሽ አስቆጥረዋል።የደደቢት ሁለት ግቦች የእብስራ ተስፋዬ በፍፁም ቅጣት ምት መድሃንየ ታደሰ በጨዋታ እስቆጥረዋል።


ፋሲል ከነማ 1-1 ደቡብ ፖሊስ

በሜዳቸው ፋሲለደስ ስታድየም ደቡብ ፖሊስን ያስተናገዱት ከመሪው መቐለ 70 እንደርታ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድል ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።በሙጂብ ቃሲም ግብ መምራት የቻሉት ፋሲሎች ከ10 ደቂቃ በኃላ በሄኖክ እየለ እማካኝነት ደቡብ ፓሊሶች አስቆጥረው ጣፋጭ እንድ ነጥብ ይዘው ወጥተዋል።


ጅማ እባጅፋር 2-0 ስሑል ሽረ

በሜዳቸው ስሑል ሽረን ያስተናገዱት ጅማ እባጅፋር በኦኪኪ ኦፎላቢና እስቻለው ግርማ ግቦች ማሸነፍ ችሏል።በሁለተኛው ዙር መሻሻልን እያሳዩ ሚገኙት ጅማዎች ድሉን ተከትለው ነጥባቸውን 31 በማድረስ ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል።


አዳማ ከተማ 1-2 ሀዋሳ ከተማ

ከእሰልጣኛቸው ጋር የተለያዩት እዳማዎች በሜዳቸው ሽንፈትን እስተናግደዋል።እንግዶቹ ሃዋሳዎች በምንተስኖት እበራ ደስታ ዮሐሀንስ ግቦች ታግዘው መሉ ሥስት ነጥብን እሳክተዋል።የአዳማን ከባዶ ሽንፈት ያዳነች ግብ ቡልቻ ሹራ አስመዝግቧል።

ደስታ ዮሐንስ ለሀዋሳ ያስቆጠራት ጎል በተንቀሳቃሽ ምስል ይመልከቱ።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


ቡልቻ ሹራ ለአዳማ ያስቆጠረውን ጎል

ጎል በተንቀሳቃሽ ምስል ይመልከቱ።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


ወላይታ ድቻ 2-1 ኢትዮጵያ ቡና

ወላይታ ድቻ በሜዳቸው ቦዲቲ ስታድየም ኢትዮጵያ ቡናን እስተናግደው በፀጋዬ እበራ ሁለት ግቦች ታግዘው ከወራ ቀጠናው እንዲርቁ ያገዛቸውን ድል አስመዝግበዋል።በእልሃሰን ካሉሻ ግብ እቻ መሆን ችለው የነበሩት ቡናዎች ውጤታቸውን ማስጠበቅ ሳይችሉ ቀርተዋል።

በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ክልል ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ጅማ አባጅፋር፣ ሐዋሳ ከተማ ና መቐለ 70 እንደርታ ድል አስመዝግበዋል።

የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ትናንት ጥቅምት 17 2011 ዓ.ም ጅማሬውን ሲያደርግ በዛሬው ውሎ ክልል ላይ 9:00 ላይ 3 ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን 3ቱም ጨዋታዎች በመሸናነፍ ተጠናቀዋል።

አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር

አዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ የተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በእንግዳው ጅማ አባጅፋር 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ለጅማ አባጅፋር ግቦቹን አስቻለው ግርማ 45ኛው ደቂቃ እንዲሁም ከ5 ደቂቃዎች በኋላ 50ኛው ደቂቃ ላይ መስዑድ መሐመድ አስቆጥረው ጅማ አባጅፋርን ከሜዳው ውጪ ጣፋጭ 3ነጥቦች እንዲያስመዘግብ አስችለውታል። ይህንንም ተከትሎ ጅማ አባጅፋር በግብ ክፍያ ተበልጦ 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ሐዋሳ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ

በሌላ የ9:00 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሐዋሳ ላይ ሐዋሳ ከተማ ወልዋሎ አ.ዩ.ን ያስተናገደበት ጨዋታ የሚጠቀስ ነው። በጨዋታውም ባለሜዳው ሐዋሳ ከተማ 3-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። በጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 1ደቂቃ ሲቀረው 44ኛው ደቂቃ ላይ እስራኤል እሸቱ የመጀመሪያውን ግብ በማስቆጠር ክለቡን ቀዳሚ በማድረግ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል። ከመልበሻ ቤት ሲመለሱ 46ኛው ደቂቃ ላይ ደስታ ዮሐንስ ሁለተኛ ግብ አስቆጥሮ የክለቡን መሪነት ከፍ አድርጓል። ጨዋታው በዚህ ውጤት ተጠናቀቀ ተብሎ ሲጠበቅ 94ኛው ደቂቃ ላይ ታፈሰ ሰለሞን ድንቅ ግብ በማስቆጠር ክለቡን የ3-0 ድል እንዲያስመዘግብ አስችሎታል።

መቐለ 70 እንደርታ ከደደቢት

መቐለ ላይ ስሙን ከ መቐለ ከተማ ወደ መቐለ 70 እንደርታ የቀየረው እና ተቀማጭነቱን ከአ.አ ወደ ትግራይ ያዞረውን ደደቢትን ያገናኘው ጨዋታ በባለሜዳው መቐለ 70 እንደርታ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ደደቢት አምና ከነበሩት ተጫዋቾች ሙሉ ለሙሉ ሊያስብል በሚያስደፍር ሁኔታ የለቀቀ ሲሆን መቐለ 70 እንደርታም ወደ 15 ተጫዋቾች ለቆ 11 ተጫዋቾችን አስፈርመው ለዚህ የውድድር አመት መቅረብ ችለዋል። በጨዋታው ላይም 3ኛው ደቂቃ ላይ ዮናስ ገረመው ግብ አስቆጥሮ ቀዳሚ ማድረግ የቻለ ሲሆን 74ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ ሳሙኤል ሳሊሶ ሁለተኛ ግብ በማስቆጠር የመቐለ 70 እንደርታን አሸናፊነት ማረጋገጥ ችሏል።

የመቐለ 70 እንደርታ የጨዋታ ሪፖርት ሊንኩን ይጫኑ

ውጤቶቹን ተከትሎ በመጀመሪያው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሐዋሳ ከተማ ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ጅማ አባጅፋር በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ አዳማ ከተማ፣ ደደቢት እና ወልዋሎ.አ.ዩ. ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ሮበርት ኦዶንካራ አዳማ ከተማን ተቀላቀለ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለሃያ አንድ ተከታታይ ጨዋታዎች ግቡን ሳያስደፍር በመቆየት ባለክብረ ወሰን ከመሆኑ በተጨማሪ ከ2004 ዓ.ም እስከ 2008 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ዓመታት የኮከብ ግብ ጠባቂ ሽልማት ክብርን ለማሳካት ችሏል።

ባሳለፈው ዓመት ከ አዳማ ከተማ ጋር ያሳለፈው ጃኮ ፔንዜ ከ አዲስ ፈራሚው ሮበርት ጋር ብርቱ ፍልሚያ ይጠብቀዋል ተብሎ ይገመታል ።

“ወደ ሰርቢያ ዘግይቼ ሄድኩ እንጂ ቀደም ብዬ የዝግጅት ወቅቱን ብቀላቀል ኖሮ ፕሮፌሽናል ተጨዋችነቱን አሳካው ነበር” ከነዓን ማርክነህ

ከነዓን ማርክነህ በኢትዮጵያ ፕሪምየር
ሊግ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ቆይታው
ጥሩ ብቃቱን በሜዳ ላይ በማሳየት መልካም
የሚባል ጊዜን ከክለቡ አዳማ ከነማ ጋር
አሳልፏል፤ በውድድር ዘመኑም ላይ የወቅታዊ
አቋሙን ጥሩ መሆን ተከትሎም ብዙዎቹ
የስፖርት አፍቃሪዎች ከፍተኛ አድናቆትን
ሰጥተውትም አልፈዋል፤ ይሄ ተጨዋች
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከተመረጡት
ውስጥም አንዱ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ
ከሰርቢያው ክለብ ባገኘው የፕሮፌሽናል
ተጨዋችነት ዕድል ወደ ቤልግሬድ ተጉዞ
የሙከራን ወቅት ቢያሳልፍም ከሄደበት
የአጭር ጊዜ አንፃር ግን የፕሮፌሽናል
ተጨዋች የመሆን ምኞቱ ለጊዜው
እንዳልተሳካለትና በቀጣይ ጊዜ በሚያደርገው
የሙከራ እድል ግን እልሙ እንደሚሳካለት
ከስፍራው በተመለሰበት ወቅት ለሀትሪክ
ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፤
የአዳማ ከነማው ከነዓን በሰርቢያ ቆይታው
ስላደረገው የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
የሙከራ እድልና ተያያዥ በሆኑ ጥያቄዎች
ዙሪያ አጠር ባለ መልኩ አናግረነው የሰጠንን
ምላሽ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

ሀትሪክ፡- የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
ሙከራን በሰርቢያ ካደረግክ በኋላ ወደ ሀገርህ
ተመልሰሃል፤ በቅድሚያ እንኳን ደህና
መጣህ? የሙከራው ቆይታ ምን ይመስላል?

ከነዓን፡– በመጀመሪያ እናንተም እንኳን
ደህና ቆያችሁኝ፤ ወደ ሰርቢያ ተጉዤ
ያደረግኩት የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ሙከራ
ምንም እንኳን የመሞከር እድሉ ተሰጥቶኝ
እዛ ገብቶ ለመጫወት የሚያስችለኝን ደረጃ
ለማግኘት ባልችልም በቆይታዬ ግን ጥሩ
ትምህርትንና ልምድን በማግኘት ለቀጣዩ ጊዜ
የሙከራው ዕድል ብዙ ያወቅኳቸው ነገሮች
ስላሉ ቆይታዬን በጣም ወድጄዋለው፤ በሰርቢያ
የ14 ቀናት ቆይታዬም ከሀገር ስትወጣ እዛ
የምትመለከታቸው ነገሮች አስቸጋሪና ብዙ
ቻሌንጆችንም የሚጠይቁም ስለሆኑ እነዛን
እንዴት መቋቋም እንዳለብኝም ያወቅኩበት
ሁኔታም ስላለ ያንን አይቼ መምጣቱ
እንደጥሩ ነገርም ነው የምመለከተው፡፡

ሀትሪክ፡- በሰርቢያ የሙከራ ዕድሉን
የሰጠ ክለብ ማን ነበር? ወደ እዛ ካመራክ
በኋላስ በሙከራው ጊዜ ለአንተ የፕሮፌሽናል
ተጨዋች እንዳትሆን ያስቸገሩ ሁኔታዎች
ምን ነበሩ?

ከነዓን፡- የሰርቢያ ጉዞዬ ላይ የሙከራ
እድሉን የሰጠኝ ክለብ ኤፍ ኬ ጃርኮቭ
ይባላል፤ ይህንንም እድል ያገኘሁት ቢኒያም
በሚባል ጓደኛዬ ነው፤ ወደ እነሱ ካመራው
በኋላም የውድድር ወቅት ላይ ስለነበሩ
በመጀመሪያ ዝም ብዬ እንዳልቀመጥ በሚል
ኤፍ ኬ ሎኮሞቲቭ ከሚባል ቡድን ጋር
ለሁለት ቀን ያህል ልምምድን ከሰራው
በኋላ ከጃርኮቭ ክለብ ጋር የ4 ቀናት የሙከራ
እድል ተሰጥቶኝ ብቆይም ወደ እዛ አምርቼ
ያደረኩት ሙከራ የአጭር ጊዜና በፕሪ ሲዝን
የዝግጅት ወቅት አለመሆኑ እንደዚሁም
ከዚህ የሄድኩት በጣም ዘግይቼና ስለሆነናውድድር በጀመሩበት ወቅት መሆኑ እና በዚህን
ጊዜ ደግሞ እነሱ ለጨዋታ የሚሆን ልምምድን
የሚሰሩበት ጊዜ ስለነበር በአጭር ጊዜ ውስጥ
በሁሉም ነገር መቀናጀት ስለሚያስቸግር በዚህ
መልኩ የሙከራው ዕድል ሳይሳካልኝ ለሌላ ጊዜ
ተጨማሪ የሙከራ እድል እንደሚሰጠኝ ተነግሮኝ
ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ችያለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- በሰርቢያ ተጨማሪው የሙከራ
ጊዜው መች ነው የሚሰጥህ?

ከነዓን፡- የሰርቢያው ክለብ ለእኔ ሌላኛውን
የሙከራ እድል የሚሰጠኝ የአንደኛው ዙር
ውድድር እንደተጠናቀቀ ነው፡፡ ያኔ በቂ የሙከራ
ጊዜን ስለማገኝ በዛ እድል ለመጠቀም ከወዲሁ
ሰፊ ዝግጅትን አደርጋለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ወደ ሰርቢያ በተጓዝክበትና
የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ሙከራን ባደረግክበት
ወቅት የእነሱን ተጨዋቾች ብቃት ከእኛ ሀገር
ተጨዋቾች ጋር ስታነፃፅረው ያለውን ልዩነት
እንዴት አገኘኸው?

ከነዓን፡- የሰርቢያ የአጭር ቀናት ቆይታዬ ላይ
የሙከራን ጊዜ ሳደርግ በእኛና በእነሱ ተጨዋቾች
መካከል የተመለከትኩት ነገር ቢኖር ቴክኒኩ ላይ
እኛ ጥሩ ነገር ያለን ቢሆንም ታክቲካል ዲስፕሊን
ሆኖ በመጫወቱ፣ በአካል ብቃቱ እና በፍጥነቱ
በኩል ግን ከእነሱ ጋር ልዩነት አለን፤ የእግር
ኳሱ ላይ የእነሱ ተጨዋቾች ሁሌም ጠንካራ
ሰራተኛ እንደሆኑ ተመልክቼያለውና እነዚህን
ስራዎቻቸውን ወደ እኛ ሀገር ላይ ማምጣት
ከተቻለና ከሰራንበት ቴክኒኩ ስላለን ከሀገራችን
ውስጥ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾችን ማፍራት
እንችላለን፡፡

ሀትሪክ፡- በመጨረሻ

ከነዓን፡- የሰርቢያው ጉዞዬ ላይ የፕሮፌሽናል
ተጨዋችነት ሕልሜን ለማሳካት የምችልበት
ዕድሉ ቢኖረኝም ወደ ሰርቢያ ዘግይቼ በመሄዴና
ቀደም ብዬም የፕሪ ሲዝን ዝግጅቱን ባለመቀላቀሌ
በሙከራ ዕድሉ የፕሮፌሽናል ተጨዋች ሳልሆን
ቀርቼያለሁ፡፡ በቀጣይ ጊዜ ሙከራው ግን
ፕሮፌሽናል የመሆን ሕልሜን አሳካለሁ፡፡

በፕሪምየር ሊጉ ለዋንጫ የሚፎካከሩት ጅማ አባጅፋርና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ሲጥሉ ኢትዮጵያ ቡና ለዋንጫ ከሚያደርገው ፍክክር ተገትቷል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው እለት በክልል ከተሞች ስታዲየሞች ቀጥለው ተካሂደዋል።

ጎንደር ፋሲለደስ ስታዲየም ላይ በተደረገ ጨዋታም ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና የተገናኙ ሲሆን፥ ፋሲል ከነማ ጨዋታውን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

 

የፋሲል ከተማን የማሸነፊያ ጎልም ሀሚዝ ኪዛ በ7ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

በሀዋሳ ስታዲየም የተካሄደው የሀዋሳ ከተማ እና የወልዋሎ አዲግራት ጨዋታም ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

አዳማ አበበ ቢቂላ ላይ የተደረገው የአዳማ ከተማ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታም ያለምንም ግብ 0ለ0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

 

በተመሳሳይ በሶዶ ስታዲየም የተደረገው የወላይታ ድቻ እና የጅማ አባጅፋር ጨዋታም 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል።

ድሬድዋ ላይ ደግሞ ድሬደዋ ከተማ እና አርባ ምንጭ ከተማ የተገናኙ ሲሆን፥ ጨዋታውም 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።

በጨዋታው ላይም እንዳለ ከበደ በ16ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ጎል አርባ ምንጭን መሪ አድርጋ የነበረ ቢሆንም፤ በረከት ይስሀቅ በ90+3ኛው ደቂቃ ላይ ለድሬዳዋ ያስቆጠራት ጎል ጨዋታው በአቻ ውጤት እንዲጠናቀቅ አድርጓል።

የጅማ አባጅፋር እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ መጣልም የፕሪምየርሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳል የሚለው አሁንም የመጨረሻው 30ኛ ሳምንት እንዲጠበቅ አድርጓል።

ፕሪየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ጅማ አባ ጅፋር በእኩል 52 ነጥብ እና 19 ጎል 1ኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ/ አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ 

ኣዳማ ላይ የሚካሄደው የኣዳማ እና ኣርባምንጭ ጨዋታ ዳሰሳን በክፍል ሁለት ዝግጅታችን እንመለከታለን።
ኣዳማዎች የዋንጫ ተስፋቸውን ለማለምለም ኣርባምንጮች ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በ ኣዳማው ኣበበ በቂላ ስታድየም ይካሄዳል።ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ቡና የተሸነፋት ኣዳማ የዛሬውን ጨዋታ በማሸነፍ የዋንጫ ተፎካካሪ መሆናቸውን ማሳየት ይፈልጋሉ።ኣርባምንጭም ከወላይታ ድቻ የጣሉትን 2 ነጥብ ለማካካስ ወደ ሜዳ ይገባሉ ግን ከሜዳቸው ሲወጡ የሚያሳዩት ደካማ ኣቋም ለወራጅ ስጋት ያጋለጣቸው ዋና ምክንያት ነው።
4-2-3-1 የጨዋታ ስልት ሚከተሉት ኣዳማ የዳዋ ሆቴሳ እና የከንኣን ማርክነህ ጥምረት ከሜዳው ሲወጣ ለሚቸገረው የኣርባምንጭ ተከላካይ ፈተና ይሆንባቸዋል።በተለይ ኣጥቂው ዳዋ ሆቴሳ ወደ መስመር እየወጣ ሚየደርጋቸው እንቅስቃሴ ለሌሎች የቡድን ኣጋሮቹ ክፍተትን ይፈጥራል።
ኣርባምንጭም በ 4-1-4-1 ጨዋታ ስልት በግራ መስመር በሚጫወተው እንዳለ ከበደ በሚነሱ ኳሶች የጎል ዕድል ሚፈጥሩት ኣርባምንጭ ኣጥቂ ስፍራ ሚጫወተው ተመስገን ካስትሮም የቡድኑ ሌላ የማጥቃት ኣማራጭ ነው። 
አዳማ ከተማ በዛሬው ጨዋታ ጃኮ ፔንዜ እና በረከት ደስታበቅጣት አይሰለፉም።በአርባምንጭ በኩሉ የጉዳት እና የቅጣት ዜና የለም።

ጨዋታው ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ በመሃል ዳኝነት ይመራዋል።

ሪፖርት | ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን መሸነፍ ችሏል

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ተኛ ሳምንት ጨዋታ ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን አስተናግዶ በአዲስ ግደይ ብቸኛ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፏል፡፡

በየኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር ታጅቦ በሰአቱ ዘጠኝ ሰአት ሲል በተጀመረው ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ደቂቃዎች ይሄነው የሜዳ ላይ የኳስ ያልታየበት የመጀመሪያው አጋማሽ ነበር።
በእንግዳዎቹ አዳማ ከተማዎች የመጀመሪያው የጨዋታ የመጀመሪያ የጨዋታ ክፍል ግዜ ደቂቃዎች በረጅሙ በሚጣሉ ኳሶች ዳዋ ሆቴሳ ሁለት ያልተሳኩ አጋጣሚዎችን አግኝቶ በቀላሉ ያመከነበት አጋጣሚ ነበር።
በ15ኛ ደቂቃ ላይ እንግዳዎቹ አዳማ ከተማዎች በበረከት ደስታ እና ሱራፌል ዳኛቸው አማካኝነት ሰብሮ ለመግባት ጥረት ሲያደርጉ ቢስተዋልም የሲዳማ ተከላካዮች በተለይ ፈቱዲን ጀማል ጥረት መክነዋል።

በ40ኛው ደቂቃ ላይ ሱራፌል ዳኛቸው በጥሩ የኳስ ቅብብል ከበረከት ጋር አድርጎ በመጨረሻም በረከት ደስታ አክርሮ ወደ ግብ መቷት ግብ ጠባቂው መሳይ አያኖ ሲያድንበት በ42ተኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ አዲስ ግደይ ሁለት የአዳማ ተጫዋቾችን በማለፍም ከሙጂብ ቃሲም እግር ስር ነጥቆ ከግብ ጠባቂው ጃኮ ፔንዜ ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የመታትን ኳስ ጃኮ ፔንዜ አድኖበታል። የመጀመሪያው አጋማሽ በዚሁ ወደ መልበሻ አምርቷል።

ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ መልኩ ሲዳማ ቡናዎች የተሻለ የማጥቃት ሂደት የታየበት ሲሆን በ53ኛው ደቂቃ ላይ ወንድሜነህ አይናለም ከርቀት አክርሮ መቷት ጃኮ ፔንዜ እንደምንም ያዳነበት በተቃራኒው እንግዳዎቹ አዳማ ከተማዎች ደግሞ 56ተኛው ደቂቃ ላይ ከነዓን ማርክነህ በግል ጥረቱ እየገፋ ገብቶ ያገኘውን እድልን በቀላሉ ሳይጠቀምቀት ያመከናት ኳስ እምታስቆጭ ነበረች። በ74ኛ ደቂቃ ላይ በመስመር ላይ በተደጋጋሚ የአዳማን ተከላካይ ሲረብሽ የነበረው አዲስ ግደይ በግራ በኩል እየገፋ ወደ ሳጥን ሲገባ በግብ ክልል ውስጥ በሙጂብ ቃሲም በመጠለፉ ምክንያት የእለቱ ፌዴራል ዳኛ ተካልኝ ለማ የሰጡትን የፍፁም ቅጣት ምት ራሱ አዲስ ግደይ በመምታት አስቆጥሮ የሲዳማን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስጨብጧል።

ከግቡ መቆጠር በኃላም ይገዙ ቦጋለ እና አዲስ ግደይ እንዲሁም በወንድሜነህ አይናለም አማካይነት በርካታ የግብ እድልን ቢያገኙም ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ጫዋታው በሲዳማ ቡና 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል ፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት

ዘርአይ ሙሉ – ሲዳማ ቡና

“የዛሬው ጨዋታው ከባድ ነበር። ምክንያቱም ተጋጣሚያችን ይዞ የመጣሁ አጨዋወት ትንሽ ፈትኖን ነበር። በጨዋታው ባናሸንፍም ከስጋት እንወጣለን ልጆቼ አቅም አላቸው በቀጣይ ቡድናችንን ወደ ተፎካካሪነት እናመጣዋለን”

አሰልጣኝ ተገኔ ነጋሽ ~ አዳማ ከተማ
የጨዋታ ድህረ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል

ሪፖርት | ቅዱስ ጊዮርጊስና አዳማ ከተማ ከሊጉ መሪ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ 3 በማጥበብ ደረጃቸውን አሻሽለዋል

አዳማ ከተማ ከነዓን ማርክነህ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ወላይታ ድቻን 1-0 በመርታት ከሊጉ መሪ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 3 ሲያጠብ በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ 3ኛነት ከፍ ብሏል፡፡

እንደሁልጊዜው በርካታ ተመልካች በስራ ምክንያት ሳይታደምበት 9:00 ሲል የጀመረው ይሄው ጨዋታ ከጨዋታው አስቀድሞ ባለሜዳዎቹ አዳማ ከተማዎች የስፖርታዊ ጨዋነትን በተመለከተ “ቅድሚያ ለስፖርታዊ ጨዋነት” የሚል የተፃበት ባነር ወደ ሜዳ ይዘው በመግባት አሳሳቢ እየሆነ ለመጣው የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጨዋታው በሁለቱም በኩል ተመጣጣኝ የሚባል እንቅስቃሴ የተደረገበት ቢሆንም ያን ያህል በግብ ሙከራዎች የታጀበ አልነበረም፡፡ምናልባትም ገና በጨዋታው መጀመሪያ 4ኛው ደቂቃ ባልተጠበቀ ሰዓት ባለሜዳዎቹ በከነዓን ማርክነህ ድንቅ የጭንቅላት ግብ መሪ የሆኑበትን አጋጣሚ በጊዜ ማግኘታቸው ድቻዎች ላይ መደናገጥን ፈጥሯል፡፡

ያም ሁኖ ከግቧ መቆጠር በሇላ የጦና ንቦቹ የአቻነቷን ግብ ለማግኘት ጫና ፈጥረው ሲጫዎቱ በረጅሙ ወደ ፊት በሚጣሉ ኳሶች ግብ ለማግኘት ተንቀሳቅሰዋል፡፡በዚህ በዳግም በቀለና ያሬድ ዳዊት አማካኝነት ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ባለሜዳዎቹ አዳማዎች የተሰነዘረባቸውን ጥቃት ከመመከት ባለፈም የአጠፋ ምላሽ ለመስጠት በ30ኛው ደቂቃ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ ዳዋ ሆቴሳ በጭንቅላቱ ገጭቶ ወደ ግብ ሞክሮት ለትንሽ ኳሷ በግቡ ቋሚ ታካ ወጥታለች፡፡

በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ የኳስ ቁጥጥር የበላይነትን በመውሰድ ፡በትልቅ ተነሳሽነት ግብ ለማስቆጠር የተጫዎቱት ወላይታ ድቻዎች በ51ኛው ደቂቃ በበዛብህ መለዮ አማካኝነት የአቻነቷን ግብ ቢያስቆጥሩም፡ በዛብህ ኳሷን ከማግኘቱ አስቀድሞ ከጨዋታ ውጭ (Offside )አቋቋም ላይ ስለነበር ግቧ በመስመር ዳኛው ተሽራለች፡፡ባለሜዳዎቹ አዳማዎች ግብ ላለማስተናገድ ወደ ሇላ ተመልሰው በረጅሙ ለዳዋ በሚጣሉ ኳሶች ሌላ ግብ ለማግኘት የተጫዎቱ ቢሆኑም ሌላ ግብ ሳያስቆጥሩ ጨዋታው በዚሁ ተጠናቋል፡፡

አዳማ ከተማ ማሸነፍን ተከትሎ ነጥቡን ወደ 36 በማድረስ በደረጃ ሰንጠሰዡ ወደ 3ኛነት ከፍ ሲል ወላይታ ድቻ በነበረበት 10ኛ ደረጃ በ27ነጥብ ተቀምጧል፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት

አዳማ ከተማ -አሰልጣኝ ተገኔ ነጋሽ
በዛሬው ጨዋታ 3 ነጥብ ማስመዝገባችን ጥሩ ነው፡፡የጨዋታ ብልጫ በወሰድንበት የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ግብ አስቆጥረን ግብ አለማስተናገዳችን መልካም ነበር፡፡

ወላይታ ድቻ -ዘነበ ፍስሀ
በጨዋታው ጥሩ ባልነበርንበት የመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ግብ አስተናግደናል፡፡ነገር ግን እኛ ጥሩ በነበርንበት የሁለተኛው አጋማሽ ግብ ማስቆጠር አለመቻላችን ውጤት እንድናጣ አድርጎናል፡፡ቢሆንም ግን በውጤቱ አንከፋም፡፡


ኤሌክትሪክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ፈረሰኞቹ ዳግም ወደ ለመዱት የሻምፒዮንነት ጉዞ የተሳፈሩበትን ወሳኝ ድል ኢትዬ ኤለክትሪክን 2-1 በማሸነፍ ሲያስመዘግቡ ከመሪው ጅማ አባጅፋር ያለቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ 3 በማጥበብ በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ 2ኛነት ከፍ ብለዋል፡፡

በቅዱስ ጊዬርጊስ የአፍሪካ መድረክ ተሳትፎ በይደር ተይዞ ዛሬ በተስተካካይ መርሃ ግብር የተካሄደው ይሄው ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ኢሊክትሪኮች ወልዲያ ከተማን 1-0 በማሸነፍ ለጊዜውም ቢሆን ከወራጂ ቀጠና ወተው አፋፉ ላይ የተቀመጡበትን ውጤት ካስመዘገቡበት ቋሚ 11 ስብስብ የ3 ተጨዋቾችን ለውጥ በማድረግ ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን ሲሴ ሀሰን፡ጥላሁን ወልዴ እና ሀይሌ እሸቱን በማሳረፍ ግርማ በቀለ፡በሀይሉ ተሻገርና ዲዲዬ ለብሪን ተክተው ገብተዋል፡፡

በፈረሰኞቹ በኩል ከሜዳቸው ውጭ በአርባምንጭ ከተማ ከደረሰባቸው የ3-0 አስደንጋጭ ሽንፈት ከተጠቀሙባቸው ቋሚ 11 ስብስብ የ4 ተጨዋቾችን ለውጥ ሲያደርጉ አስቻለው ታመነ፡ናትናኤል ዘለቀ፡አዳነ ግርማና ሪቻርድ አፒያን በማስገባት ምንተስኖት አዳነ፡ ሙሏለም መስፍን፡ጋዲሳ መብራቴና አሜ መሀመድን በማሳረፍ ገብተዋል፡፡በዚህም የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ አፒያ በፈረሰኞቹ ማለያ በቋሚ አሰላለፍ የመጀመሪያ ተመራጭ ሁኖ ሲጀምር የመጀመሪያው ሁኖ ተመዝግቧል፡፡

በርካታ ደጋፊዎች ታድመውበት 10:00 ሲል በጀመረው የኢሊክትሪክና የቅዱስ ጊዬርጊስ ጨዋታ ገና ከጨዋታው መጀመሪያ ደቂቃ የግብ ሙከራ የተደረገበት ሲሆን በ2ኛው ደቂቃ ኢሊክትሪኮች በመስመር በኩል ለግብ የተቃረበ ሙከራ በስንታየሁ ሰለሞን አማካኝነት ሲያደርጉ የፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዶንካራ ኳሷን ወደ ውጭ አውጥቶ የማዕዘን ምት ቢያገኙም ኢለክትሪኮች አልተጠቀሙበትም፡፡በፈጣን የኳስ ቅብብሎሽ ወደ ግብ ለመድረስ በሚደረግ ፍክክር የቀጠለው ይሄው ጨዋታ በፈረሰኞቹ መለያ በመጀመሪያ አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገባው ስቴቨን አፒያ በ6ኛው ደቂቃ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ ከመረብ ጋር በማገናኘት ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል፡፡

ከጎሏ መቆጠር በሇላ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ግብ ለማግኘት ወደ ፊት ተጠግተው የግብ ሙከራ ቢያደርጉም ኢላማቸውን የጠበቁ አልነበሩም፡፡በ19ኛው ደቂቃ ፈረሰኞቹ በመስመር በኩል ይዘውት የገቡትን ኳስ በሀይሉ አሰፋ በጥሩ ሁኔታ ወደ ግብ ክልል የሰነጠቀውን ኳስ አፒያ ኳሱን ሳይደርስበት የኢለክትሪኩ ግብ ጠባቂ ሱሌማን አቡ ኳሷን በያዘበት እንቅሰስቃሴ ከአፒያ ጋር ተጋጭተው ግብ ጠባቂው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ጨዋታው ለ6ደቂቃዎች ያህል ቆሞ ኤሌክትሪኮች በሱሌማን አቡ ቦታ፡ ዮሃንስ በዛብህን ቀይረው በማስገባት ጨዋታው ቀጥሏል፡፡

ፈረሰኞቹ ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በማጥቃት እንቀቅስቃሴ ትተዋቸው የሚሄዷቸውን ክፍተቶች በመጠቀም ግብ ለማስቆጠር ሲጫዎቱ በ37ኛው ደቂቃ በመሀሪ መና እና በበሀይሉ አማካኝነት ያደረጓቸው ለግብ የተቃረቡ ሙከራዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በኢለክትሪክ በኩል በ38ኛው እና 49ኛው ደቂቃ ለግብ የቀረበ ሙከራ ሲያደርጉ በ51ኛው ደቂቃ ዲዲዬ ለብሪ በጥሩ አጨራረስ ኳስና መረብን አገናኝቶ ቡድኑን ወደ አቻነት መልሷል፡፡በ60ኛው ደቂቃ ካሉሿ አልሀሰን ጣጣውን የጨረሰ ኳስ ለታፈሰ ተስፋዬ አመቻችቶ አቀብሎት አገባው ሲባል ሮበርት ኦዶንካራ የመለሰበት ኢሊክትሪክን ወደ መሪነት የሚመልስ ወርቃማ አጋጣሚ መክኗል፡፡

ፈረሰኞቹ በ70ኛው ደቂቃ ያገኙትን የማዕዘን ምት በአፒያ ተቀይሮ የገባው አማራ ማሌ በግንባሩ ገጭቶ ባስቆጠረው ግብ በድጋሚ መሪ መሆን ችለዋል፡፡ኢሊክትሪኮች በድጋሚ የአቻነቷን ግብ ለማግኘት በጨዋታው ማገባደጃ በቀኝ መስመር በኩል ዲዲዬ ለብሪ ሰብሮ ለመግባት ሲሞክር
አቡበከር ሳኒ ጥፋት በመስራቱ በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡ጨዋታው በዚሁ ሲጠናቀቅ ኢለክትሪክ በነበረበት በ21 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ሲረጉ፡ ፈረሰኞቹ በ36 ነጥብ ወደ 2ኛነት ከፍ ብለዋለል፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት

ኢትዮ ኤሌክትሪክ – ም/አሰልጣኝ ቦጋለ ዘውዴ
በጥቃቅን ስህተቶች ተሸንፈናል፡፡የአጨራረስ ችግራችን ዋጋ አስከፍሎናል፡፡በቀጣይ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክረን እንሰራለን፡፡

ቅ/ጊዮርጊስ – ቫስ ፒንቶ
ዛሬ ማሸነፋችን ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ወደ ዋንጫው በምናደርገው ጉዞ የማሸነፍ ስነ ልቦና ጥንካሪያችን ለማጎልበት ውጤቱ ትልቅ ሚና አለው፡፡