Category: የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ

የ2012 የተጨዋቾች ዝውውር በኢንተርሚደሪ /ሶስተኛ ወገን/ ብቻ የሚስተናገድ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዓለም አቀፋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን /ፊፋ/ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ተጨዋቾች ዝውውርን አስመልክቶ ባወጣው መመሪያ መሠረት በቀጣይ በ2012 ዓ.ም ፌዴሬሽኑ በመሚመራቸው ውድድሩሮች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ተጨዋቾች በኢንተርሚደሪ /በሶስተኛ ወገን / ብቻ ምዝገባ እንደሚካሄድ አስታወቀ፡፡

ቀደም ሲል ይህንኑ ሥራ ለመስራት የሚያስችለውን የኢንተርሚደሪ /የሶስተኛ ወገን/ ፈቃድ ለሚፈልጉ በሙሉ
በፌዴሬሽኑ መስፈርት መሠረት የፈቃድ መውሰጃ ፈተና በመስጠት 75 የሚሆኑት ተመዝጋቢዎች የመመዘኛ ፈተናውን ማለፋቸውን የአረጋገጡ በመሆናቸው ፈቃዱን ለመውሰድ የፈቃድ ክፍያ እና የኢንሹራንስ ክፍያ በመፈፀም ቅድመ ዝግጅታቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ ፡፡

ከሐምሌ 25 /2011 እስከ ጥቅምት 12 /2012 እና ከጥር 1 እስከ ጥር 30 ቀን 2012 ዓ.ም በአንደኛ እና በሁለተኛ ዙር የሚከናወኑት የ2012 ዓ.ም የተጫዋቾች ምዝገባን አስመልክቶ ለኘሪሚየር ሊግ ክለቦች፣ ለከፍተኛ እና ለአንደኛ ሊግ ክለቦች ዛሬ ሐምሌ 18/ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ከፌዴሬሽኑ ሕጋዊ የሦስተኛ ወገን ፈቃድ በተሰጣቸው ህጋዊ አካላት ብቻ ማስመዝገብ እንደሚገባቸው እና በፌዴሬሽኑ ህጋዊ የሆኑት አካላትም ስም ዝርዝር በደብዳቤ እንደሚላክላቸው የተገለፀ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፀሐፊ የሆኑት አቶ ሚሊዮን መኮንን ገልፀዋል፡፡
አክለውም “ማንኛውም የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ተጫዋች በተገለፁት የምዝገባ ጊዜያት ለመመዝገብ በሚቀርብበት ወቅት ከፌዴሬሽኑ የሶስተኛ ወገን ፈቃድ ባላቸው እና ሕጋዊ በሆኑት አካላት ብቻ መመዝገብ እንደሚገባቸው” አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም “ይህ አይነቱ አሰራር ለአገራችን እግር ኳስ የራሱ የሆነ በጎ ገጽታ ያለው ሲሆን ለክለቦቻችን በወቅቱ የሚፈጠሩትን የተለያዩ የምዝገባ ስህተቶች በአፋጣኝ ለመፍታት፣ ለፌዴሬሽኑ የገቢ ምንጭ እንዲያገኝ የማስቻል እና ለተጨዋቾች በተደጋጋሚ የሚከሰትን ክስ እና እንግልት ለመቀነስ እንዲሁም የሦስተኛ ወገን ፈቃድ ላላቸው የሥራ እድል መፍጠርን የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪም የዓለም አቀፋ የእግር ኳስን አሠራር ሂደት የሚከተለውን ዘመናዊ ሥርዓት በአገራችን መተግበሩ በፊፋ እና በካፍ መልካም ገጽታ ለማግኘት የራሱ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ያደርጋል በማለት” አስረድተዋል ፡፡

Via- theeff official page

የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ የ2010 ግምገማ እና የ2011 የእጣ ማውጣት ስነስርአት ተካሂዷል

የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ የ2010 ግምገማ እና የ2011 የምድብ ድልድል እና የእጣ ማውጣት ስነስርአት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ሆቴል ተካሂዷል።
በ2010 የ1ኛ ሊግ ውድድር በርካታ ችግሮች ቢገጥሙንም ውድድሩን መፈፀም ችለናል ሲሉ የፌዴሬሽኑ አካላት ገልፀዋል።
በሳለፈነው የ1ኛ ሊግ ውድድር 57 ክለቦች ሲካፈሉ 486 ጨዋታዎችን አከናውነዋል።

በ2010 ውድድር ዓመት ከነበሩ ችግሮች ውስጥ :-

¤ በጨዋታ ላይ ዳኞች በደጋፊዎቹ እና በክለብ አባለት መደብደብ
¤ በውድድሩ ከክለቦች የቦታ እርቀት የተነሳ ዳኞችን በበቂ ሁኔታ ለመመደብ መቸገር።
¤ በጨዋታ ሜዳዎች ላይ በቂ የፀጥታ ሀይል አለመኖር።
¤ የዳኞችን የጨዋታ አፈፃፀም በተመለከተ ኮሚሽነሮች የተሟላ ሪፖሪት አለማቅረብ።
¤ በውድድሩ ሜዳዎች ደጋፊ እና ተጫዋቾችን እሚለይ አጥር (ሽቦ) አለመኖሩ።
¤ በአንዳንድ የውድድር ቦታ ሜዳዎች ለውድድር አመቺ ያለሁን ሜዳዎች መኖሩ።

በውድድሩ ለነበሩ ችግሩች የተሰጡ መፍትሔዎች :-
¤ በውድድሩ ወቅት የዳኞች ስም እየተጠቀሱ እንዳይመደቡ እሚጠየቁ ጥያቄዎችን ያለመቀበል።
¤ የጨዋታዎቹ ክብደት እየታየ ሲኒየር ዳኞችን መመደብ።
¤ ከጨዋታ ታዛቢዎች በተጨማሪ በየጨዋታው የኮሚቴ አባላትን በታዛቢነት እንዲገኙ ማድረግን::
¤ በየውድድሩች ላይ ከፀጥታ አካላት ጋር በመነጋገር ችግሮች ሳይፈጠሩ መፍትሔ እንዲወሰድ ማድረግ።

በመጨረሻም 63 ክለቦች በ6 ምድብ እሚሳተፉ ክለቦች ምድቦቻቸውን ይፋ ሆኗል።

የ2011 የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ ክለቦች የጨዋታ መርሐ ግብራቸውን በቀጣይ ቀናት በድህረ-ገፃችን ላይ እምናሳውቅ መሆናችንን እንገልፃለን።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኞች አቋርጠውት የነበረውን የመዳኘት ስራ በኘሪሜየር ሊጉ ተስተካካይና በሌሎች ውድድሮች ከነገ ጀምሮ ለመጀመር መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር በዳኞች ላይ የሚፈጸመው ጉዳት እየተባባሰ መጥቷል በሚል ቅሬታ ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ለሶስት ሳምንታት የትኛውንም ውድድር እንደማያጫዉቱ ባወጡት ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አስታውቀው ነበር።

ይሁን እንጂ ማህበሩ ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ባደረገው ውይይት “በማህበሩ አቋም መግለጫ የተነሱት ጥያቄዎች ከሞላ ጎደል ምላሽ በማግኘታቸው” ዳኞች ነገ ስራቸውን ለመጀመር መወሰናቸውን ገልጿል።

“ሁሉም የዳኞች ጥያቄ ባይመለሱም በውይይቱ ላይ በማህበሩ የቀረቡ ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ሳይሆን በጊዜ ሂደት በፌደሬሽኑ የሚመለሱ መሆናቸው ከመግባባት ላይ መደረሱን” ማህበሩ አስታውቋል።

ዳኞች ውድድር እንደማያካሄዱ በመግለጻቸው ምክንያት የ23 ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አልተካሄደም።

የዳኞች ማህበር ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ወደ ውድድር ለመመለስ 10 ቅድመ ሁኔታዎች እንዲተገበሩ አስቀምጦ ነበር። እነዚህም ከዚህ በታች የተጠቀሱት ናቸው።

በ2010 ዓ.ም የውድድር ዘመን የተጎዱ ዳኞች ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸው፣ ውድድሩን ከመጀመራችን በፊት በውድድር ደንቡ መሰረት የመድህን ዋስትና (ኢንሹራንስ) እንዲገባልን፣ ረዳት ዳኛ ሙስጠፋ መኪ በሃገር ውስጥም ሆነ ውጭ ሃገር ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ፤

ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመግባባት የዳኞች ጥበቃ እንዲደረግ፣ በወንዶች እና በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ለመዳኘት በሚደረግ ጉዞ አውሮፕላን የሚደርስበት ቦታ ሁሉ የአውሮፕላን ትራንስፓርት እንዲመቻች፣ የአልቢትር እያሱ ፈንቴን ጉዳይ ጨምሮ ፖሊስ ያወቃቸው የስርዓት አልበኝነትና የመብት ጥሰቶች ተገቢውን የህግ ፍርድ እንዲያገኙ እንዲደረግ፤

ፌዴሬሽኑ ለዳኞች እና ለታዛቢዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያመቻች፣ ማህበሩ ያለአግባብ ለጠቅላላ ጉባኤ ያወጣው ወጪ በፌዴሬሽኑ በህጋዊ ደረሰኝ አማካኝነት እንዲመለስ፣ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴዎቹ አሰራር በግልፅ እንዲጠየቅ እና ተገቢው የህግ ከለላ በሌለባቸው ስታዲየሞች ውድድር እንዳይካሄድ የሚሉ ናቸው።

” ስሜታችንን ለተጋሩ የስፖርት ቤተሠብ፣ ክለቦች ሚዲያው፣ የማህበራችን አባላትን አመሰግናለሁ። ውድድሩ ከነገ ጀምሮ መካሄድ እንደሚጀምር አረጋግጣለሁ”
አቶ ትግል ግዛው

” ክስተቱ ሁሉም እግር ኳሳዊ ጉዞ በስርአትና በመመርያ መሰረት መካሄድ እንዳለበት አሳይቶናል። እኛም ያቆምነው ሰው እንዳይሞት አስበን ነው።ጸጥታውን በጋራ እንጂ በፖሊስ ብቻ አይጠበቅም። አሁን ግን ማህበሩ ጋር ስምምነት በማድረጋችን ከነገ ጀምሮ ውድድሮች የሚቀጥሉ ይሆናል”
ፕሬዝዳንቱ ጁነይዲ ባሻ


በስብሰባው ላይ ከየክልላቸው ተወከለው ከመጡ ዳኞችና ከፌዴሬሽኑ አካላት የተለያዩ አሳቦች ቀርበዋል ፣ከቀረቡት ሀሳቦች መካከል :-

👉”እናንተ አንድ ብትሆኑ እኛም አንድ እንሆን ነበር።
ከመቶ 25ቱ አልተመለሰም።የፌዴሬሽኑ ሳይሆን የኛ ጉባኤ ነውና እንደፈለኩ እናገራለው።በሰውነታችሁ አከብራለው ሃሳባችሁን ግን አናከብርም።

እድሜ ለአማራ ቲቪ ዳኛውን ሲያሯሩጡ አይተናል እናንተ ባታሳዩኝ። ከከፍተኛ ሊግ ማንን እንደሚያልፍ ተሰርቶ አልቋል። እንደ አዲስ አበባ ተወካይነቴ አልቀበልም”
አርቢትር አሰፋ ደቦጭ


👉”ኮማንድ ፖስቱ የተቋቋመው ለሁላችን ደህንነት ነው
ፌዴሬሽን ደግሞ በአቶ ጁነዲን የሚመራ ዳኛ የሚመድብ ኮማንድ ፖስት አቋቁሟል ይሄ ደግሞ ተገቢ አይደለም ። ቦታ እስኪያገኝ ድረስ ታግሎ ቦታውን ሲይዝ ባለሙያ የሚገድል ሰው አለ ተው
ሊባል ይገባል። ”
የማህበሩ ም/ል ፕሬዝዳንት ሚካኤል አርአያ


👉”የቀይ ካርድ ውሳኔን የሚያሽሩት አቶ አበበ ገላጋይ ናቸው”
ዳኞች ውሳኔ ለመወሰን የተቀመጡላቸው መስፈርቶች አሉ። ለምሳሌ ተጫዋች በጨዋታ ላይ ሲያጠፋ የሚሰጠው የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ ወይም ቀይ ካርድ ዳኛው ሲሰጥ የተቀመጡ መስፈርቶች አሉን።

በዚሁ ቢጫ ካርድ ወይም ቀይ ካርድ እንሰጣለን። ሆኖም ይህ አሰራር እየተሻረ ነው። እንዲያውም አንዳንድ ተጨዋቾች ቀይ ካርድ ስንሰጣቸው ችግር የለውም አንተ ቀይ ካርድ ብትሰጠኝ ነገ የሚያነሳልኝ አካል አለ” እያሉ ያፌዙብናል ይሄ ፌዝ ነው። ”
ኢ/ር አርቢትር ዳዊት አሳምነው


👉 ” አንቺ ከቦክስ ተረፍሽ እንዴ እየተባልኩ ነው ያጫወትኩት ይሄ መታረም አለበት ይሄ የተኩስ ማቆም ስምምነት ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ነው”
አርቢትር ማርቆስ


👉”ፌዴሬሽኑ 1+1=2 ነው እያለ አይደለም 1+1=2 ሊሆን ይችላል እያለን ነው። ይሄ ልክ አይደለም እኛ የምንፈልገው ድርድር አይደለም ጥያቄውን መልሱልን”
ኢ/ር ረዳት ዳኛ ክንዴ ሙሴ


👉 ” ይሄ መንግስታችን ነው ስፖርቱ የልማቱ አንዱ አካል ነው ያለው።መንግስትና ማህበራችን አድማ አይፈልጉም ሴትና ወንድ እኩል ነው እየተባለ መለያየት ተገቢ አይደለም”
የማህበሩ ፕሬዝዳንት ትግል ግዛው


የኢትዮጵያ ዳኞችና ፌዴሬሽኑ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተክትሎ ኘሪሚየር ሊጉ በተስተካካይ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ሲቀጥል ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት መርሐ ግብሮቹ እሚከናወኑ ይሆናል።
 

የ2010 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ተሰተካካይ ጨዋታዎች 

                

 

ሰኞ ግንቦት 6 ቀን 2010

 09:00
ወልዋሎ አዲግራት ዩ.
    ?-?
መቐለ ከተማ

በሽረ ስታዲየም ቀሪ 45 ደቂቃ


 09:00
 አዳማ ከተማ
   ?-?
 ወላይታ ድቻ

 10:00
 ቅዱስ ጊዮርጊስ
    ?-?
ኢትዮ-ኤሌክትሪክ

አርብ ግንቦት 10 ቀን 2010

 09:00
መቐለ ከተማ
   ?-?
ቅዱስ ጊዮርጊስ

 09:00
ደሬዳዋ ከተማ
    ?-?
ወላይታ ድቻ


 
 


ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሊበተን ነው:: ዳኞችና ኮሚሽነሮች ከመግለጫ እንዲቆጠቡ ታዟል!!

በቅርብ ጊዜያት ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜያት
ስማቸው ሲጠራ ከከረሙት ኮሚቴዎች አንዱ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ነው። ዲሲፕሊን ኮሚቴ ወልዲያ ላይ ከጣለው ቅጣት ጋር በተያያዘ የአንድ አመት የሜዳ ዕገዳን ወደ 3 ጨዋታ በመቀነስ የውዝግቡ መነሻ ሆኗል በሚል የስራ አስፈጻሚው በአቶ ገደቡ መርዕድ የሚመራውን ይህንን ኮሚቴ እንዲበተን መወሰኑ ታውቋል። አመራሮቹ በአስቸኳይ በአዳዲስ አባላት ኮሚቴውን የማጠናከር ስራ ይሰራልም ተብሏል።
በሌላ በኩል ከዚህ ምሽት ጀምሮ ማንኛውም ዳኛና ኮሚሽነር ስላጫወተው ጨዋታ ለሚዲያ መግለጫ እንዳይሰጥ ተከልክሏል።በዚህ መሰሉ ድርጊቱ የተገኘ
ዳኛና ኮሚሽነር ላይም ርምጃ እወስዳለሁ ብሏል
የአርቢትር ኮሚቴው።

አንዳንድ አርቢትሮችምአላስፈላጊና ሃላፊነት የጎደለውን ጸብጫሪ አስተያየታቸውን ማቆም አለባቸው ሲል አርቢትር ኮሚቴው አስጠንቅቋል።
ዳኞችና ኮሚሽነሮች የፊታችን እሁድ ሊጉ ስለሚቀጥል እንዲዘጋጁ ለዚህ ደግሞ ከማህበሩ አመራሮች ጋር ጠንካራ ውይይት እንደሚደረግና ረቡዕ
ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት ስራ አስፈጻሚው እንደሚጥር ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

“በዳኞች ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት እንቃወማለን፡ዳኞች ላነሱት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት አለበት፡ኘሪሚዬር ሊጉ ግን መቋረጥ የለበትም ክለቦች እና አቶ ጁነዲን ባሻ”

የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያና በተለይም በዳኞች ላይ እየደረሰ ባለው ድብደባ ዙሪያ ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ምክክር ሲያደርጉ በዳኞች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ተቀባይነት የሌለውና የምንቃወመው ነው፡ ዳኞች ላነሱት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት አለበት፡ኘሪሚዬር ሊጉ ግን መቋረጥ የለበትም በሚሉትና ሌሎች ጉዳዬች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በምክክሩም በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ለተነሱ ችግሮች ክለቦች እና ፌዴሬሽኑ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር የተደረገ ቢሆንም ትናንት የዳኞች እና ኮሚሽነሮች ማህበር ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በቀጣይ 3ሳምንታት የትኛውንም ጨዋታ ላለመዳኘት እና በቀጣይም ጨዋታውን ለመዳኘት ማህበሩ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ስላሉ የኘሪሚዬር ሊጉ መቋረጥ ክለቦች ከበጀትና ከሌሎችም ጉዳዬች አንፃር እንዳሳሰባቸው ገልፀው ማህበሩ ጉዳዩን በድጋሚ እንዲያየው ጠይቀዋል፡፡

ክለቦች ትኩረት ሰተው ካነሷቸውና የጋራ መግባባት የተደረሰባቸው ዋና ዋና ነጥቦች

✍በዳኞች ላይ የደረሰውን ድብደባ ኢ-ሰብዓዊ የሆነና በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑና እንደሚያወግዙት፡፡

✍ፌዴሬሽኑ የሚወስናቸው የቅጣት ውሳኔዎች አስተማሪ አለመሆናቸውና ቅጣቶች በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የሚሻሩበት ሁኔታ ፍትሀዊ አለመሆኑ፡፡

✍አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች አዘጋገብ በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴም ሆነ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ላይ ቀድመው ጫና እያሳደሩ መሆናቸው፡፡

✍የአማራና የትግራይ ክለቦች ሲገናኙ ፡ችግሩን በመሰረታዊነት ከመፍታት ይልቅ በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫዎቱ መደረጉ ትክክል አለመሆኑ

✍አንዳንድ ክለቦች ዳኛ የሚያስመድቡበትና የሚያስቀይሩበት አካሄድ ትክክል አለመሆኑ

✍ጥቂት ዳኞችና ኮሚሽነሮች የሙያቸውን ስነ ምግባር በመጣስ ጨዋታዎች በሁከት ተጠናቀው በሪፖርታቸው በሰላም ተጠናቋል በማለት ይልካሉ፡፡

✍የፌዴሬሽኑ አመራሮች ከአንድ በላይ በሆኑና በተለያዩ በውሳኔ ላይ በሚጣረሱ ስራዎች መወከላቸው አግባብ አለመሆኑ እና ሌሎችም በርካታ ነጥቦች ተነስተው ውይይቱ ሲቀጥል

ክለቦች የኘሪምየር ሊጉ ውድድር መቋረጥ የለበትም ብለው ላነሱት ሀሳብ ፡የዳኞችና ኮሚሽነሮች ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ “ትግል” ማህበሩ የኔ የግል ድርጅት አይደለም
ውሳኔው የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ነው፡፡ ነገር ግን ማህበሩ ጨለምተኛ አይደለም፡፡ስለዚህ ይህን መሻር እና ማፅደቅ ያለበት ጉባኤው ነው ሲሉ ምላሽ ሰተዋል፡፡

ክለቦች በበኩላቸው ጨዋታዎች የሚቋረጡ ከሆነ በዚህ አመት ሻምፒዬንም፡ ወራጂም ክለብ መኖር የለበትም ሁሉም ክለቦች የቀጣዩን ዓመት ውድድር መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡ካልሆነ ግን ዳኞችን ከውጭ ሀገር እናስመጣለን እንጂ ውድድሩ አይቋረጥም፡፡ብዙ ወጭዎች አሉብን ውድድሮች ቀድመው ሊጠናቀቁ ይገባል በማለት ጠንከር ያለ ሀሳብ ሰንዝረዋል፡፡

በመጨረሻም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ በማጠቃለያ ንግግራቸው ውድድሮች መቋረጥ የለባቸውም፡ዳኞች ያነሷቸውን ጥያቄዎች የተወሰኑትን መልሰናል፡ያልተመለሱትን ጥያቄዎችም በሂደት ምላሽ የሚያገኙ ይሆናል፡፡በቀጣይም የዳኞችና ኮሚሽነሮች ማህበር ጋር ውይይት እናደርጋለን ከዚህ ባሻገር የፊታችን እሁድ ከፀጥታ አካላት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ገልፀው፡፡
“ኢትዮጵያን እናክብር የራሳችንን ዜጋንም እናክብር» ብለው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኞች ለሶስት ሳምንት ምንም አይነት የዳኝነት አገልግሎት አንሰጥም አሉ

የኢትዮጵያ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር በዳኞች ላይ እየተከሰተ በመጣው የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል፡፡

በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር በሴቶችና ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ፣በከፍተኛ ሊግ፣በአንደኛ ሊግ እና ሌሎች ማንኛውም ፌድሬሽኑ በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ጨዋታዎችን ላለመዳኘት መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከሶስት ሳምንት በኋላ ወደ እግር ኳስ ዳኝነት ለመመለስም በርከት ያሉ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል በ2010 ዓ.ም በእግር ኳስ ጨዋታዎች በስፖርታዊ ጨዋነት የተጎዱ ዳኞች ካሳ እንዲከፈላቸው እና ለሚደርስባቸው ጉዳት የህይወት መድህን ኢንሹራንስ እንዲገባላቸው ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል፡፡

በክልል በሚደረጉ ውድድሮችም ለዳኞችና ታዛቢዎች የክልል ጸጥታ ሀይሎች ጥበቃ የሚያደርጉበትን መንገድ ፌድሬሽኑ እንዲፈጥርም ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም በክልል የሚካሄዱ የእግር ኳስ ውድድሮችን ለመዳኘት አውሮፕላን በሚያርፍባቸው ቦታዎች ላይ የአውሮፕላን መጓጓዣ እንዲመቻችላቸውና ሌሎች ተያያዥ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉላቸው ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የዕጣ ማውጣት እና ዓመታዊ ግምገማ ተካሄደ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሚያወዳድራቸው ውድድሮች መካከል አንደኛው የሆነው በቀድሞ ስያሜው ‹‹ብሄራዊ ሊግ ›› በአሁኑ መጠሪያው ‹‹አንደኛ ሊግ›› የደንብ ውይይት እና እጣአወጣጥ ስነስርአት ዛሬ ተከናውኗል።
በፕሬዝዳንቱ አቶ ጁነዲን ባሻ መክፈቻ ንግግር የተጀመረው ውይይት ፣ ። የ2009 ዓ.ም ውድድር አመት ሪፖርት ቀርቧል።
ከዚህ ሪፖርት መጠናቀቅ በኋላ የዳኞች ኮሚቴ ተወካይ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በአመቱ ለምን ያህል ዳኞች የአካል ብቃት ምዘና ፈተና እንደተሰጠ በሪፖርቱ ውስጥ ተጠቅሷል። በዚህም መሰረት ለ215 ዳኞች የአካል ብቃት ምዘና ፈተና ተሰጥቷል።
በተጨማሪም በውድድር አመቱ አንድ ዳኛ ከፍተኛ 12 ጨዋታዎችን እንዲሁም ዝቅተኛ 7 ጨዋታዎችንአጫውቷል። ከዚም በማስከተል የዳኞች ሪፖርት ተጠናቆ ወደ ፀጥታ ኮሚቴ ሪፖርት አምርቷል።
ከዚህ በማስቀጠልም የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ሪፖርት ማሰማት የጀመረ ሲሆን በስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት የጎፋ ባሪንቼ 6 ነጥብ እና 100 ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎበት እንደነበር እና ነጥብ መቀነስ ክለቡ ላይ ብቻ ሳይሆን አካባቢው ላይ የሚያመጠውን ተፅዕኖ ከግምት በማስገባት 50 ሺህ ብር እንዲሆን ተደርጎ የነጥብ ቅነሳውን ሽረናል ሲሉ አብራርተዋል።
የደንቡ ክፍተት ችግር እያመጣብን ነው፤ ስለዚህም የጥፋት ዝርዝር እና ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ጥፋቶች በግልፅ መቀመጥ አለበት ሲሉ ተወያዮቹ ሀሳባቸውን አንፀባርቀዋል።
ለ3 የውድድር አመታት የሚያገለግል ደንብ የወጣ ሲሆን ክለቦቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል። የሚዲያ ትኩረት፣ ዳኝነት እና ስፖርታዊ ጨዋነት ትልቅ የመወያያ ርዕስ ሆነው ተነስተዋል።
በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ የተቀጡ ቡድኖች የተሻለ ነጥብ ተሰጥቷቸዋል ምክንያቱ ምንድነው, ኮከብ ግብ አግቢ እና ተጫዋች የተሰጣቸው ነገር ምንድነው? እንደ ተቋም የሰጣቸው እውቅና ምንድነው ግልፅ ቢሆን ተብሏል።
ከሰአት በኋላ በነበረው የውይይት ጊዜ
13ቱ ተሰብሳቢዎች ሀሳባቸውን ገልፀው ምላሾች የተሰጡ ሲሆን በስብሰባው ድርጊቱ ሲፈፀም ቦታው ላይ ሁሉ ያልነበሩ ተጫዋቾች ተቀጥተውብናል የሚል ቅሬታ ተነስቶ የነበረ ሲሆን የዲሲፒሊን ኮሚቴ ተወካዪ በቀረበልን ሪፖርት መሰረት ነው ሲል ሲሉ መልሰዋል።
የውድድሩ መጀመሪያ ቀን ላይ ሀሳብ ተነስቶ የመጀመሪያው ቀን ጥቅምት 18 የነበር ሲሆን ህዳር 3 ለመጀመር ሀሳብ ቀርቦ በመጨረሻም ህዳር 25/2010 እንዲጀመር ተወስኗል።
በመጨረሻም ስለ ወራጅ እና አላፊ ቡድኖች ሀሳብ የተነሳ ሲሆን ቀደም ሲል ከየምድቡ አንደኛ አንደኛ የሚወጡት ቡድኖች በቀጥታ አልፈው አንድ ቡድን የተሻለ ነጥብ ያመጣው ተደምሮ ለከፍተኛ ሊግ ያልፉ ነበር በአሁኑ የውድድር አመት ግን ከየምድቡ ከ1~3 የወጡት በቀጥታ አልፈው የተሻለው አራተኛ ተቀላቅሎ የማጠቃለያ ውድድር ይደረጋል ተብሏል። የቀኑ ውሎም የምድብ ድልድይ በማውጣት ተጠናቋል፡፡
ምድብ -ሀ
1. አራዳ ክ/ከተማ
2. አምቦ ከተማ
3. ወሊሶ ከተማ
4. አሶሳ ከተማ
5. ንስር
6. ጋምቤላ ዩኒቲ
7. አ/አ ፖሊስ
8. ዱከም ከተማ
9. ቱሉ ቦሎ
10. መቱ ከተማ
11. ነቀምት ከተማ
12. ሆለታ ከተማ
13. ጋምቤላ ከተማ

ምድብ -ለ
1.ቢሾፍቱ ከተማ
2.ሞጆ ከተማ
3.ባቱ ከተማ
4.ወንጂ ስኳር
5.ካሊ ጅጅጋ
6.ድሬዳዋ ጨርቃጨርቅ
7.ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ
8.መተሃራ ስኳር
9.ኢትዮ-ሶማሌ ልዩ ፖሊስ
10.ሀረር ከተማ
11.ካዳባ አፋር
12.ሀረር አባድር
13.ገላን ከተማ

ምድብ -ሐ
1. ላስታ ላሊበላ
2. ዳሞት ከተማ
3. ትግራይ ዋልታ ፖሊስ
4. አማራ ፖሊስ
5. ትግራይ ውሀ ስራ
6. ራያ አዘቦ
7. ሶሎዳ አድዋ
8. አምባ ጊዮርጊስ
9. ደባት ከተማ
10. ደባርቅ ከተማ
11. መርሳ ከተማ
12. ሰሜን ሸዋ ደ/ብርሃን
13. አዊ አምፒልታቅ
14. የጁፍሬ ወልድያ

ምድብ-መ
1.ጉለሌ ክፍለ ከተማ
2.አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ
3.ጨፌ ዶንሳ
4.ቂርቆስ ክፍለ ከተማ
5.ቦሌ ክፈፍለ ከተማ
6.ቦሌ ገርጂ ዩኒየን
7.ጎጃም ደብረማርቆስ
8.ናኖ ሁርቡ
9.ሰንዳፋ በኬ
10.አቃቂ ክፍለከተማ
11.ንፋስ ስልክ ክፍለከተማ
12.ለገጣፎ 01
13.ልደታ ክፍለከተማ

ምድብ -ሠ
1.ሀዲያ ሌሞ
2.አርሲ ነገሌ
3.ሺንሺቾ ከተማ
4.ጋርዷላ
5.ኮንሶ ኒዮርክ
6.ሮቤ ከተማ
7.ቡሌ ሆራ ከተማ
8.ወላይታ ሶዶ
9.ጪንቻ ከተማ
10.ጎፋ ባሬንቼ
11.ጂንካ ከተማ
12.ጎባ ከተማ

ሃገር አቀፍ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር የእጣ ማወውጣት ፕሮግራም ተካሄደ!!

ሃገር አቀፍ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር የእጣ ማወውጣት ፕሮግራም ተካሄደ!!
ወልድያ ከተማ ላይ የሚካሄደው የሃገር አቀፍ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከ ሐምሌ 22-ነሐሴ 9 ድረስ በወልድያ ከተማ በ34 የክልል ክለቦች መሃከል የሚካሄድ ሲሆን የእጣ ማውጣት ስነስርአቱ ዛሬ አርብ ሐምሌ 21 ቀን የእጣማውጣቱ ስነስርአት በወልድያ ባህል አዳራሽ ተካሂዷል!!
በዚህ ፕሮግራም መሰረት 34ቱ ክለቦች በ 8 ምድቦች ተከፍለው የሚጫወቱ ሲሆን ከየ ምድቡ ሁለት ሁለት ቡድኖች ባጠቃላይ 16 ቡድኖች ወደ ጥሎ ማለፉ ያልፋሉ!!
በጥሎማለፍ ካለፉት 16 ክለቦች ውስጥ በጥሎማለፍ ጨዋታው ወደ እሩብ ፍጻሜው የሚቀላቀሉ 8 ክለቦች ወደ ብሄራዊ ሊግ (አንደኛ ሊግ) ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ!!
በዚህ ውድድር በውድድር ደንቡ አንቀጽ 13 ተ.ቁ 2 በአንድ ጨዋታ መቀየር የሚቻለው የተጨዋች ብዛት 3 የነበረው ወደ 4 ከፍ ብሏል ይህም በዋናነት ለወጣቶቹ እድል ለመስጠት ታስቦ ነው!!
ምድቡም
ምድብ አንድ (ሀ)
1. የጁ ፍሬ ወልድያ (አማራ)
2. ሽረ እንደስላሰ ቢ (ትግራይ)
3. ያሶ ወረዳ (ቤኒሻንጉል)
4. ሾኔ ከተማ (ደቡብ)
5. ኢተያ ከተማ (ኦሮሚያ)
.
ምድብ ሁለት (ለ)
1. ድሬዳዋ ኮተን (ድሬዳዋ)
2. ቡሬ ከተማ (አማራ)
3. መርካቶ አካባቢ (አ/አ)
4. ቤንች ማጂ ፖሊስ (ደቡብ)
5. መተከል ፖሊስ (ቤኒሻንጉል)
.
ምድብ ሶስት (ሐ)
1. አሳሳ ከተማ (ኦሮሚያ)
2. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ
3. ደጋን ከተማ (አማራ)
4. ናኖ ሁርቡ (አ/አ)
.
ምድብ አራት (መ)
1. ነስር ክለብ (ቤኒሻንጉል)
2. ሰንዳፋ በኬ (ኦሮሚያ)
3. አረካ ከተማ (ደቡብ)
4. ዋልያ ክለብ (ድሬዳዋ)
.
ምድብ አምስት (ሠ)
1. ሀረማያ ዩንቨርስቲ (ሐረር)
2. ሻሾጎ ወረዳ (ደቡብ)
3. አላማጣ ከተማ (ትግራይ)
4. መርሳ ከተማ (አማራ)
.
ምድብ ስድስት (ረ)
1. አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ (አ/አ)
2. ሐረር ፖሊስ ኮሚሽን (ሐረር)
3. ኦሮሚያ ፖሊስ (ኦሮሚያ)
4. ገንዳ ውሃ ከተማ (አማራ)
.
ምድብ ሰባት (ሰ)
1. ገንፈል ውቅሮ (ትግራይ)
2. ጉለሌ ክ/ከተማ (አ/አ)
3. 07 ቀበሌ (ድሬዳዋ)
4. ካማሺ ከተማ (ቤኒሻንጉል)
.
ምድብ ስምንት (ሸ)
1. ሺንሺቾ ከተማ ( ደቡብ)
2. 06 ሕብረት (ድሬዳዋ)
3. ጫንጮ ከተማ (ኦሮሚያ)
4. አቃቂ ማዞሪያ (አ/አ)
………..
ነገ የሚካሄድ ጨዋታ
የጁፍሬ ወልድያ ከ ሾኔ ከተማ
በ8:00 ሰአት በወልድያ ሙሃመድ ሁሴን አላሙዲ ስታዲየም
እንደ ስላሴ ከ ያሶ ከተማ
በ10:00 ሰአት
በሸህ ሙሃመድ ሁሴን አላሙዲ ስታዲየም
የመክፈቻ ስነስርአቱ ከ 6:30 ይጀምራል!!
መልካቆሌ ላይ ጧት 2 ጨዋታወች ይካሄዳሉ!!

በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የምድቡ አሸናፊ እንዲሁም በማጠቃለያ ውድድር ላይ 2ኛ ደረጃን ይዞ ላጠናቀቀው የደሴ ከነማ እግር ኳስ ክለብ የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ

በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የምድቡ አሸናፊ እንዲሁም በማጠቃለያ ውድድር ላይ 2ኛ ደረጃን ይዞ ላጠናቀቀው የደሴ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ልኡካን ቡድን፤ተጋባዥ እንግዶችና ደጋፊዎችን ጨምሮ የእራት ግብዣ ኘሮግራም ትናንት ምሽት ተዘጋጅቶ ነበር፡፡
በዚሁ ዝግጅት ላይ ቃል የተገባላቸዉን 600ሺ ብር ወጭ በማድረግ ለክለቡ ውጤት አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካላት ለእያንዳንዳቸው የገንዘብ ሽልማት ተሠጥቷል፡፡
1.ለክለቡ ዋና አሠልጣኝ  30ሺ ብር
2.ለክለቡ ምክትል አሠልጣኝ 20ሺ ብር
3.ለ1ኛ ደረጃ ተጨዋቾች  20ሺ ብር
4.ለ2ኛ ደረጃ ተጨዋቾች  15 ሺ ብር
5.ለ3ኛ ደረጃ ተጨዋቾች  10 ሺ ብር
6.ለ4ኛ ደረጃ ተጨዋቾች  8 ሺ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ከዚህ በተማሪም ለተጨዋቾች ምግብ የሚያበስሉ፤የፅዳት አገልግሎት የሚሠጡ፤ሾፌር፤ወጌሻ ገንዘብ ያዥን ጨምሮ ለበርካቶች ሽልማት ተበርክቷል፡፡
አመቱን ሙሉ ክለቡን በተለያዬ መንገድ ሲያበረታቱ ለነበሩ ቀንደኛ የክለቡ ደጋፊዎችም የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል ፡፡
በቀጣይ የከፍተኛ ሊጉን ዉድድር በድል ከተወጡ ዳጎስ ያለ ሽልማት እንደሚጠብቃቸው ቃል ተገብቷል፡፡

source-dessie kenema official fb page

በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ደባርቅ ከ ራያ ያደረጉት ጨዋታ በውዝግብ ተቋረጠ 

ራያ ቀድሞ ባስቆጠረው ጎል 1 ለ ምንም እየመራ፤  90ኛው  ደቂቃ ላይ ደባርቅ የአቻነቱን ጎል እንዳገባ፤ ወዲያውኑ የራያ አዘቦ ደጋፊ ወደ ሜዳ በመግባት በተጨዋቾቹ ላይ ጉዳት አደርሰዋል


ከተጎዱት የደባርቅ ተጨዋቾች መካከል፤ ቻላቸው አሰፋ፣ ፋሲል ፋንታሁን፣ሸጋው አስማረ፣ አቤል ፋንታሁን፣ ዮሃንስ ኪሮስ፣ ፍስሃ ረዲ እና አሰልጣኝ ስጦታው ይገኙበታል።

 የተጎዱትን ወደ ሆስፒታል ከአመሩ በኋላ ፥የጨዋታው ኮሚሽነር የባከነውን 5 ደቂቃ እንዲጨርሱ ሁለቱንም ቡድን ያዘዙ ሲሆን የደባርቅ ተጨዋቾቹ አቋርጠው ወጥተዋል። 

ደባርቅ በብሄራዊ ሊጉ 8ኛ ደረጃ ላይ ሲሆን ፥ ራያ አዘቦ 6ኛ ነው። ሁለቱም ቡድኖች ወደ ልዕለ ደራጃው የማደግ እድል የላቸውም።

source-TBM