Category: የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የሐሙሱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ውዝግብ እንዳይነሳበት ተሰግቷል�

በዮሴፍ ከፈለኝ

በኢመርጀንሲ ኮሚቴና በተቀሩት
የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት
መሀል የነበረው አለመግባባት በረድ ቢልም
ልዩነቶችን ሊያሰፋ የሚችል ምክንያት
መፈጠሩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የፊታችን
ሀሙስ ሀምሌ 25/2011 የሚደረገው የስራ
አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱ ስብሰባ ሌላ ውዝግብ
እንያስከትል ተሰግቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት
በካፒታል ሆቴል ከግንቦት በኋላ ለመጀመሪያ
ጊዜ የተገገናኙት አመራሮቹ በያዙት አጀንዳ
ላይ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት የስዑልሽረና
ወልዋሎ ጨዋታ ህገ ወጥ ድርጊት
ታይቶበታል በሚል አርቢትሩና ኮሚሸነሩ
ሪፖርት በማድረጋቸው ጉዳዩን ዲሲፒሊን
ኮሚቴ አይቶ ውሳኔ እንዲሰጥ ይግባኝ ሰሚ
ኮሚቴም የቅዱስ ጊዮርጊስን ይግባኝ ባፋጣኝ
አይቶ ከአመራሮቹ የሀሙስ ስብስባ በፊት
ውሳኔያቸውን እንዲያሳውቁ ቢወሰንም
ሀትሪክ የደረሳት መረጃ ግን ጉዳዩን አጠራጣሪ
አድርጎታል፡፡ ከታማኝ ምንጮች በደረሰ መረጃ
ዲሲፕሊን ኮሚቴ በወልዋሎ አዲግራትና
ስሁል ሽረ ጨዋታ ዙሪያ ምንም አይነት
መረጃ እንዳልደረሰው ታውቋል፡፡ ይህ ደግሞ
ለሀሙሱ ስብሰባ የዲስፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ
ላይቀርብ እንደሚችል አመላክቷል፡፡ የቅዲስ
ጊዮርጊስ ይግባኝ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ቢደርስም
እስከዛሬ ድረስ ይግባኙን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው
አለማየቱ ታውቋል፡፡ መደበኛ ስብሰባቸው
ሀሙስ ሃሙስ የሚያደርጉት የይግባኝ ሰሚ
ኮሚቴ አባላት ምናልባት በአቸኳይ ማክሰኞና
ረቡዕ ካልተሰበሰቡ በስተቀር የአመራሮቹ
ስብሰባ ውጤት አልባ ሊሆን እንደሚችል
ተሰግቷል፡፡ ከኮሚቴው ምንጫችን ባገኘነው
መረጃ “ብንሰባሰብ እንኳን የሚቀርበው
ሰነድ ካልተሟላ ውሳኔ ላይሰጥ ይችላል”
ሲል የሁኔታውን አጠራጣሪነት አስረድቷል፡
፡ በተለይ ወልዋሎ አዲግራትና ስሁል ሽረ
ጨዋታ ዙሪያ የተሟላ መረጃ አለኝ ያለው
መከላከያ ጥያቄ ማቅረቡና እስካሁን ምላሽ
አለማግኘቱ ራሱን የቻለ ክርክር እንዳያስነሳም
ተሰግቷል፡፡ በስሁልሽረ ደጋፊዎች ተፈፀመ
የተባለው ድርጊት በፌዴሬሽኑ ህግ ነጥብ
የሚያስቀንስ ቢሆንም አመራሮቹ ይህን
የማድረግ ድፍረት ይኖራቸዋል ወይ?
የሚለው የበርካቶችን ትኩረት ስቧል፡፡

ለአንድ ሳምንት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተሰጠው የእግር ኳስ አስልጣኞች አሰልጣኝ ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒክ ዲፓርትመንት ከተለያዩ ዩኒቭርስቲዎች ለተውጣጡ 33 የስፖርት ሳይንስ መምህራን ሲሰጥ የነበረው የእግር ኳስ አሰልጠኞች ስልጠና ከ7ቀናት የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና በኋላ በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ፡፡
ይህ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካኝነት የተሰጠው የሀገር ውስጥ ኢንትራክተሮች ስልጠና አላማ ያደረገው በሚሄዱባቸው የሃገራችን ክፍሎች ለእግር ኳስ አሰልጣኞች ከክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ስልጠናዎችን እንዲሰጡ ለማደረግ የታቀደ መሆኑን ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒክ ዳይሬክተር ኢንስትራክተር መኮንን ኩሩ ገልጸውልናል፡፡
ዛሬ በነበረው የመዝጊያ ፕሮግራም የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ባደረጉት ንግግር በቀጣይ በርካታ ስራዎች ከሰልጣኖቹ እንደሚጠበቅ የገለጹ ሲሆን፤ አክለውም የወደፊቱን የተሻለ ብሔራዊ ቡድን ለማግኘት ሁሉም ለሀገሩ የሚጠበቅበትን እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡


ስልጠናውን የተከታተሉት የዩኒቨርስቲ መምህራንም ይህን ሀላፊነት በሚገባ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ስለመወጣታቸው የቴክኒክ ዳይሮክተሬቱ ክትትል እንደሚያደርግ እና ግንኙነታቸውም በጠበቀ መልኩ እንደሚያስቀጥሉ ኢንሰትራክተር መኮንን ኩሩ ገልጸውልናል፡፡ በስተመጨረሻም ለሰልጣኞቹ የምስክር ወረቀት ተሰጧቸዋል፡፡

Via- Eff website

✍ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር “የስፖርት ጨዋነት ምንጮች” በሚል ርዕስ በሸራተን አዲስ ሆቴል ያዘጋጀውን የባለድርሻ አካላት የሁለት ቀናት የውይይት መድረክ: ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ፡፡

በውይይቱ ላይ በስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት መንስኤዎች እና መፍትሔዎቻቸው ዙሪያ ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ሀሳባቸውን ያካፈሉ ሲሆን ይህንኑ ተከትሎ የተዘጋጀው የጉባኤው ሙሉ የአቋም መግለጫ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል፡፡

//////////////////////////////////////////////////////////////////

የአቋም መግለጫ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ ‹‹በኢትዮጵያዊያኖች መካከል ውይይት መባዛት አለበት›› ባሉት መሠረት፤ በሚያዚያ 14 እና 15 2011 ዓ.ም በሼራተን አዲስ ሆቴል ለሁለት ቀን የተካሄደው “የስፖርት ጨዋነት ምንጮች” የውይይት መድረክ፤ የሚቀጥለውን የአቋም መግለጫ ለኢትዮጵያ መንግሥት እንዲቀርብ በጋራ ተስማምቷል፡፡

በቅድሚያም ጉባዔው፡-

የኢትዮጵያ መንግሥት የሰላም ሚኒስቴር እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በውይይቱ ላይ በመካፈላቸው፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም በመተባበሩና ለውጥ ፈላጊ መሆኑን በመግለጹ የተሰማውን ደስታ እየገለጸ፤

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በራስ ተነሳሽነትና የጠቅላይ ሚኒስትሩን መመሪያ በመከተል የውይይቱን መድረክ ስላዘጋጀ ምስጋናውን እያቀረበ፤
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ጨዋታ አካባቢ የሚፈጠረው ረብሻ በጎሣ፣ በብሔር ወይም በቋንቋ ልዩነት ላይ የተመሠረተ እየሆነ መምጣቱን በመረዳት፣ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦች መካከል የፖለቲካ አመለካከቶቻቸውን የሚያንጸባርቁ ስሞች፣አርማዎችና ልዩ ልዩ ምልክቶች ያሏቸው መኖራቸውን በመገንዘብ፣

ክልሎችም ሆኑ ከተሞች እግር ኳስንየፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ መሣሪያ ማድረጋቸውን በማስተዋል፣ በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳም፣ በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ጨዋታ አስጊና አሳዛኝ ሁኔታ ላይ በመገኘቱ፣ ዘርን የተመለከቱ የኦሊምፒክ ቻርተርና የኢንተርናሽናል ፌዴሬሽኖች ደንቦች እየተጣሱ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ አስተዳዳሪዎች በሙያና በችሎታ ሳይሆን በብሔር ተዋፅዖ የሚመረጡበት አሠራር በመኖሩ፣

የትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች ስፖርት እንቅስቃሴ መዳከም በመጉላቱ፣ ያም ሆኖ፣ የእግር ኳስ ክለቦችን አቅም በመመዘንና ያገሪቱን ኢኮኖሚ በማገናዘብ፣ የኢትዮጵያ አንድነት የሚጠነክርበትና ሕዝቡም የሚዋሐድበት የስፖርት እንቅስቃሴው መሆኑን በማመን፣

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የስፖርት እንቅስቃሴውን ችግሮች በመረዳትና ዓለማቀፍ የስፖርቶቹን ሕጎች እና ደንቦች ለማክበር ይቻል ዘንድ ተገቢውን እርምጃዎች ለመውሰድ እንዲረዳ የውይይቱ መድረክ በሚከተሉት አቋሞች ላይ በጋራ ተስማምቷል፡-

1) የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ የዘር ልዩነት እንዲጠፋና የኦሊምፒክ ቻርተርና የኢንተርናሽናል ስፖርት ፌዴሬሽኖች ደንቦች እንዲከበሩ እንዲደረግ፤

2) ዘራቸውን ወይም ብሔራቸውን መሠረት አድርገው የተቋቋሙት የእግር ኳስ ክለቦች ስማቸውን እንዲቀይሩ፤

3) የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የልዩ ልዩ ስፖርት ፌዴሬሽኖች መሪዎችና አባሎች በዘራቸው ሳይሆን በሞያቸውና በችሎታቸው ብቻ እንዲመረጡ፤

4) የትምህርት ሚኒስቴር ስፖርት በትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች እንዲስፋፋ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ፤

5) የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ አገልጋዮች በጎ ፈቃደኞች መሆናቸውን በመገንዘብ የወጣቱ ትውልድ በበጎ ፈቃደኝነት እንዲሰለፍ እንዲበረታታ፤

6) የኢትዮጵያን ስፖርት ድርጅቶች ለማገልገል የሚመኙ ሁሉ በስነ-ምግባር ኮሚቴዎችና በመንግሥት ፀጥታና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም በፖሊስና በፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዲመረመሩ፤

7) ኢትዮጵያን በዓለም ስፖርት ጉባኤዎች የሚወክሉት መልዕክተኞች ቢያንስ አንድ የውጭ አገር ቋንቋ አጣርተው የሚያውቁና ውይይቱን መከታተል የሚችሉ መሆናቸውእንዲረጋገጥ፤

8. የፖሊስና የደህንነት ድርጅቶች የስፖርት ውድድሮችን በተለይ እግር ኳስ ጨዋታን በፀጥታና በጥበቃ መስክ ከፌዴሬሽኖቹ ጋር በመተባበር የሚሠሩ ቋሚ ኃላፊዎች በየከተሞቹ እንዲመደቡ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ፤

9) በኢትዮጵያ ያሉት የስፖርት ስታዲዮሞችና መጫወቻ ስፍራዎች ተገቢ የእሳት አደጋ መከላከያ እንዲሁም የሕክምናና የአምቡላንስ አገልግሎትና በቂ የመፀዳጃ ስፍራዎች እንዲኖራቸው፤

10) የአልኮል መጠጥ ከስታዲዮሞች ውስጥ እንዳይሸጥና ሲጃራ ማጨስ ክልክል መሆኑን እንዲታወጅ፤

11) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚዘጋጁት ውድድሮች ፎርማት ለክለቦች ተስማሚና ለስፖርት ዕድገት የሚጠቅም እንዲሆን እንዲደረግ፤

12) ይህን የአቋም መግለጫ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያቀርቡልንና መንግሥትም ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ የኦሊምፒክ ቻርተር አክባሪ እንዲሆን ተገቢውን ውሳኔ እንዲያስተላልፉ ክብርት የሰላም ሚኒስትርንና ክብርት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

አዲስ አበባ
ሚያዚያ 15 ቀን 2011 ዓ.ም
የስፖርት ጨዋነት ምንጮች የውይይት መድረክ

via- Liyu sport

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለምርጥ 10 ተጫዋቾች ምርጫ 32 ዕጩዎች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2011 ዓ.ም የ1ኛው ዙር ውድድር መርሃ ግብርን መሠረት የአደረገ ምርጥ አስር ተጨዋቾች ምርጫ ኘሮጀክት ከገምጃ የህትመትና ማስታወቂያ ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር ለመሥራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል ፡፡
በምርጥ 10 ዕጩነት በምርጫው የሚካተቱ 32 ተጨዋቾችን የመምረጡን ሥራ ከፌዴሬሽኑ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት ተሠርቶ ተጠናቋል፡፡
32ቱ እጩ ተጫዋቾቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1 አማኑኤል ገ/ሚካኤል መቐለ 70 እንድርታ አጥቂ

2 ሐይደር ሸረፋ መቐለ 70 እንድርታ አማካይ

3 አዲስ ግደይ ሲዳማ ቡና አጥቂ

4 ፊቶዲን ጀማል ሲዳማ ቡና ተከላካይ

5 አቤል ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ

6 ሳላዲን ሰይድ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ

7 ታፈሰ ሰሎሞን ሐዋሳ ከተማ አማካይ

8 ደስታ ዮሃንስ ሐዋሳ ከተማ የመስመር ተከላካይ

9 ያሬድ ባዬ ፋሲል ከነማ ተከላካይ

10 ሱራፌል ዳኛቸው ፋሲል ከነማ አማካይ

11 ኤልያስ አህመድ ባህር ዳር ከተማ አማካይ

12 ወሰኑ ዓሊ ባህር ዳር ከተማ አጥቂ

13 ዳዋ ሆቴሳ አዳማ ከተማ አጥቂ

14 ከነዓን ማርክነህ አዳማ ከተማ አጥቂ

15 አቡበከር ነስሩ ኢትዮጵያ ቡና አጥቂ

16 አማኑኤል ዮሃንስ ኢትዮጵያ ቡና አማካይ

17 ደስታ ደሙ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተከላካይ

18 አፍወርቅ ሀይሉ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተከላካይ/ተመላላሽ

19 ምኒሉ ወንድሙ መከላከያ አጥቂ

20 ዳዊት እስጢፋኖስ መከላከያ አማካይ

21 ባዬ ገዛኸኝ ወላይታ ዲቻ አጥቂ

22 ቸርነት ጉግሳ ወላይታ ዲቻ አማካይ

23 ሳሙኤል ዮሃንስ ድሬዳዋ ከተማ ተከላካይ/ተመላላሽ

24 ያሬድ ሙሸንዲ ድሬዳዋ ከተማ አማካይ

25 አስቻለው ግርማ ጅማ አባ ጅፋር አጥቂ

26 ይሁን እንዳሻው ጅማ አባጅፋር አማካይ

27 ሄኖክ አየለ ደቡብ ፖሊስ አጥቂ

28 ዮናስ በርታ ደቡብ ፖሊስ አማካይ

29 ጅላሉ ሻፊ ስሑል ሽረ አማካይ

30 ልደቱ ለማ ስሑል ሽረ አጥቂ

31 የአብስራ ተስፋዬ ደደቢት አማካይ

32 አቤል ጥላሁን ደደቢት አማካይ

በቀጣይ የተጫዋቾች መምረጫ የጽሁፍ ቁጥሩን እና የተጫዋቾቹን ኮድ በይፋ በቀጣይ ቀናት እንደሚያሳውቁ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ፍሰሃ ገልጸውልናል፡፡

source -Eff

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዋሊያ ቢራ ጋር የስፖነሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማህበር ጋር የብቸኛ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ዛሬ መጋቢት 11/2011ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተፈራረመ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ላለፉት አራት ዓመታት 56ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ አጋርነቱን በተግባር ያረጋገጠው ዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማህበር መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ዋሊያዎቹ ሲነሱ ዋሊያ ቢራ፤ ዋሊያ ቢራ ሲነሳ ዋሊያዎቹ ይታወሳሉ፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማህበር ለቀጣዮቹ አራት አመታት የሀምሳ ስድሰት ሚሊዮን ብር ብቸኛ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ይህ አዲስ ስምምነት የኢትዮጵያ የወንድ እና የሴት ዋና ብሔራዊ ቡድኖችን ላይ የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ በተጨመሪም ከዚህ በፊት ከነበረው ስምምነት በተለየ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቢራ እና ማልት መጠጦች ውጪ ከሌሎች የመጠጥ ተቋማት ጋር የስፖነሰር ሺፕ ስምምነት እንዲፈራረም ስምምነቱ ይፈቅድለታል፡፡

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ”የእኛ እና የዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማህበር የብቸኛ ስፖንሰር ሺፕ ስምምነት በዋናነት የምግብና መጠጥን አስመልክቶ የወጣውን አዋጅ መሰረት አድርጎ ለመስራት እና በተመሳሳይ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ለማስጠበቅ ግዴታ እና መብትን በግልጽ የሚያሳይ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ስምምነት ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህ ስምምነት ከ2019 እስከ 2022 እ.ኤ.አ ለተከታታይ 4ዓመታት የሚቆይ ሲሆን የስፖንሰር ሺፑ ስምምነቱም 56ሚሊዮን ብር ነው፡፡

Source – eff

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በ95 ሚሊየን ብር አዲስ ህንጻ ገዝቷል

ከወሎ ሰፈር ወደ ቄራ ሲያቀኑ የኢትዮጲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ
ዋና ጽ/ቤት ወይም የሳውዲአረቢያ ኤምባሲ ጋር ሳይደርሱ የሚያገኙት ባለ 8 ፎቅ ህንፃ በተለይ ከሰኔ በዃላ
የኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል::

ከፊፋ በተገኘ ድጋፍ እስከ 120 ሚሊየን ብር የሚያወጣው
ህንጻ. በ95 ሚሊየን ብር. ለመግዛት የተስማሙት. አመራሮቹ
ወደ 7. የሚጠጉ ህንጻዎችን ከተመለከቱ በዃላ መሆኑ ታውቋል::

ፌዴሬሽኑ ወደ 13 ሚሊየን ብር ለሻጩ የቅድሚያ ክፍያ የሰጠ ሲሆን የርክክብ ሂደቱ በ3ወር ጊዜ ውስጥ የሚያልቅ እንደሆነ መረጃዎች ያስረዳሉ::

አመራሮቹ በቅርቡ በዚህ ህንጻ ግዢ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል

ዶ/ር እያሱ መርሀፅድቅ አዲሱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ ሆነው ተሹመዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ በአዲሱ የሪፎርም አደረጃጀት መሠረት ሁለት ሹመቶችን መስጠቱን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በስብሰባው ፌዴሬሽኑ በአዲስ መልክ ባዘጋጀው የአደረጃጀት ሪፎርም ጥናት መሠረት የሰው ሃብት አደረጃጀት ምደባው በአዲስ መልክ በአስቸኳይ እንዲጠናቀቅ ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጿል።

ይሄንኑ ተግባራዊ ለማድረግ ሁለት ሹመቶችን የሰጠ ሲሆን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊነት ዶክተር ኢያሱ መርሃፅድቅን መሾሙን አመልክቷል።

ስራ አስፈጻሚው አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴን በፌዴሬሽኑ ምክትል ዋና ፀሐፊነት እና በእግር ኳስ ልማት ኃላፊነት መመደቡንም ገልጿል።

አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ ዶክተር ኢያሱ ከመሾማቸው በፊት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ዋና ጸሐፊ ሆነው አገልግለዋል።

ደደቢት እግርኳስ ክለብ ቅሬታውን አሰመልክቶ ለፌዴሬሽኑ በደብዳቤ አስገብቷል

የ2011 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ የ2ኛ ሳምንት ጨዋታ ደደቢት እግርኳስ ክለብ ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ 2-0 በሆነ ውጤት መረታቱ በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ እለት እሚታወስ ነው። በእለቱ ከአዲስአበባ መገናኛ ብዙሀን ኤፍ ኤም 96.3 በቀጥታ ስርጭት አዲስአበባ እና አካባቢው ላይ ማስተላለፍ ችሏል።

በእለቱ ጣቢያው የደደቢት እግርኳስ ክለብን ፍቃድ ሳያገኝ ማስተላለፉ በክለቡ የሜዳ ገቢ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ማሳደሩን ክለቡ ለፌዴሬሽኑ የላከው ደብዳቤ ያስረዳል። የደብዳቤው ሙሉ ይዘት ከታች ይመልከቱ

የ2011 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ እጣ ማውጣት ስነስርዓት ተካሂዷል።

የ2010 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ግምገማ እና የ2011 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ የእጣ ማውጣት ስነስርዓት ተካሂዷል ። የመጀመሪያው ዙር የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ተፋላሚዎች ታውቀዋል


ጥቅምት 17 ቀን 2011

1ኛ ሳምንት

አዳማከተማ ከ ጅማ አባጅፋር
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ባህርዳር ከተማ
ሽረ እንዳስላሴከ ወላይታ ድቻ
ሲዳማ ከፋሲል ከተማ
ሀዋሳ ከተማከ ወልዋሎአዲግራት
መቐለ ከተማ ከ ደደቢት
ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬደዋ ከተማ
ደቡብ ፖሊስ ከ መከላከያ


የ2011 የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ድልድል ታውቋል

ወላይታ ድቻ ከ ጅማአባጅፋር
ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት
ሽረ እንዳስላስ ከ ሲዳማ ቡና
ድሬደዋ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
አዳማ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ
ወልዋሎ አዲግራት ከ ፋሲል ከተማ
መቐለ ከ ደቡብ ፖሊስ
መከላከያ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ


*በጉባኤው ላይ የተነሱ አንኳር አንኳር ሁነቶች አስመልክቶ አመሻሹ ላይ በድህረ ገፃችነሰ ላይ እምናስነብብ ይሆናል።

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር የሚከናወኑ ውድድሮች እሚጀመሩበት ቀናት ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2011 ዓ.ም ከሚያካሂዳቸው አገር አቀፍ እና ኢንተርናሽናል ውድድሮች መካከል ከዚህ በታች የተገለፁትን ውድድሮች :-

v የኢትዮጵያ ሴቶች ኘሪሚየር ሊግ የ2011 ዓ.ም የሁለቱም ዲቪዚዮኖች ውድድር ህዳር 1 ቀን 2011 ዓ.ም የሚጀመር ይሆናል፡፡

v የኢትዮጵያ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በ2010 ዓ.ም የኘሪሚየር ሊግ ወንዶች አሸናፊ በሆነው በጅማ አባ ጅፋር ክለብ እና በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊ በሚሆነው ክለብ መካከል ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡

v የኢትዮጵያ ወንዶች ኘሪሚየር ሊግ የ2010 ዓ.ም የውድድር አፈፃፀም ግምገማ እና የ2011 ዓ.ም የዕጣ ማውጣት ሥነስርዓት መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

v የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ከኬንያ አቻው ጋር መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም በ10፡00 ሰዓት በባህር ዳር ስታዲየም እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ጨዋታ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የስታዲየም ለውጥ እንደተደረገ የሚገለጸው መረጃ የተሳሳተ ሲሆን ውድድሩ በባህር ዳር ስታዲየም የሚከናወን ይሆናል ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን