Category: የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

የ2012 የተጨዋቾች ዝውውር በኢንተርሚደሪ /ሶስተኛ ወገን/ ብቻ የሚስተናገድ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዓለም አቀፋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን /ፊፋ/ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ተጨዋቾች ዝውውርን አስመልክቶ ባወጣው መመሪያ መሠረት በቀጣይ በ2012 ዓ.ም ፌዴሬሽኑ በመሚመራቸው ውድድሩሮች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ተጨዋቾች በኢንተርሚደሪ /በሶስተኛ ወገን / ብቻ ምዝገባ እንደሚካሄድ አስታወቀ፡፡

ቀደም ሲል ይህንኑ ሥራ ለመስራት የሚያስችለውን የኢንተርሚደሪ /የሶስተኛ ወገን/ ፈቃድ ለሚፈልጉ በሙሉ
በፌዴሬሽኑ መስፈርት መሠረት የፈቃድ መውሰጃ ፈተና በመስጠት 75 የሚሆኑት ተመዝጋቢዎች የመመዘኛ ፈተናውን ማለፋቸውን የአረጋገጡ በመሆናቸው ፈቃዱን ለመውሰድ የፈቃድ ክፍያ እና የኢንሹራንስ ክፍያ በመፈፀም ቅድመ ዝግጅታቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ ፡፡

ከሐምሌ 25 /2011 እስከ ጥቅምት 12 /2012 እና ከጥር 1 እስከ ጥር 30 ቀን 2012 ዓ.ም በአንደኛ እና በሁለተኛ ዙር የሚከናወኑት የ2012 ዓ.ም የተጫዋቾች ምዝገባን አስመልክቶ ለኘሪሚየር ሊግ ክለቦች፣ ለከፍተኛ እና ለአንደኛ ሊግ ክለቦች ዛሬ ሐምሌ 18/ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ከፌዴሬሽኑ ሕጋዊ የሦስተኛ ወገን ፈቃድ በተሰጣቸው ህጋዊ አካላት ብቻ ማስመዝገብ እንደሚገባቸው እና በፌዴሬሽኑ ህጋዊ የሆኑት አካላትም ስም ዝርዝር በደብዳቤ እንደሚላክላቸው የተገለፀ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፀሐፊ የሆኑት አቶ ሚሊዮን መኮንን ገልፀዋል፡፡
አክለውም “ማንኛውም የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ተጫዋች በተገለፁት የምዝገባ ጊዜያት ለመመዝገብ በሚቀርብበት ወቅት ከፌዴሬሽኑ የሶስተኛ ወገን ፈቃድ ባላቸው እና ሕጋዊ በሆኑት አካላት ብቻ መመዝገብ እንደሚገባቸው” አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም “ይህ አይነቱ አሰራር ለአገራችን እግር ኳስ የራሱ የሆነ በጎ ገጽታ ያለው ሲሆን ለክለቦቻችን በወቅቱ የሚፈጠሩትን የተለያዩ የምዝገባ ስህተቶች በአፋጣኝ ለመፍታት፣ ለፌዴሬሽኑ የገቢ ምንጭ እንዲያገኝ የማስቻል እና ለተጨዋቾች በተደጋጋሚ የሚከሰትን ክስ እና እንግልት ለመቀነስ እንዲሁም የሦስተኛ ወገን ፈቃድ ላላቸው የሥራ እድል መፍጠርን የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪም የዓለም አቀፋ የእግር ኳስን አሠራር ሂደት የሚከተለውን ዘመናዊ ሥርዓት በአገራችን መተግበሩ በፊፋ እና በካፍ መልካም ገጽታ ለማግኘት የራሱ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ያደርጋል በማለት” አስረድተዋል ፡፡

Via- theeff official page

ሀምበሪቾ ዱራሜ አሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህ (አሌኮ ) በኃላፊነት ቀጥሯል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን በምድብ ለ በ19 ነጥብ በ4ኛ ደረጃ ይዞ የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቀው ሀምበሪቾ ዱራሜ ዋና አሰልጣኙን ያሬድ አበጀን በማሰናበት በምትኩ አለማየሁ አባይነህ (አሌኮ) ቀጥሯል።

አሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህ (አሌኮ) ከ45 የፕርሚየር ሊግ ጨዋታ በሁዋላ ከ10 ወራት በፊት ከሲዳማ ቡና ጋር መለያየቱ ይታወሳል ፡፡

ሀላባ ከነማ በፌዴሬሽኑ ጠንከር ያለ ቅጣት ተላለፈበት

ታህሳስ 28 ቀን 2011 ዓ.ም በሀላባ ስታዲየም በሀላባ ከነማ እና በኢትዮጵያ መድን መካከል ሲካሄድ የነበረው የከፍተኛ ሊግ የ1ኛው ዙር የ6ኛው ሳምንት ጨዋታ በዕለቱ በተፈጠረየስፖርታዊ ጨዋነት ችግር በ76ኛው ደቂቃ መቋረጡ ይታወሳል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የመቋረጥ ዕጣ የገጠመው የዕለቱ አርቢትር ከተመልካች በተወረወረ ድንጋይ በመፈንከታቸውና ይሄንንም ተከትሎ አርቢትሩ “ደም እየፈሰሰኝ ነው፤በዚህ ሁኔታ ጨዋታውን መምራት አልችልም”በማለታቸው ጨዋታው መቋረጡ ይታወሳል።
በዕለቱ ጨዋታ የተፈጠረውን ችግር ሲመረምር የነበረው የፌዴሬሽኑ የዲሲፒሊን ኮሚቴ የቀረቀለትን ሪፖርት ከመረመረ በሃላ ከዚህ በታች ያለውን ውሳኔ ማስተላለፋን በኢሜይል ከተላከልን መረጃ ለማወቅ ተችላል።
ፌዴሬሽኑ በሀላባ ከነማ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ዋና ዋና ነጥቦች

1.150ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት
2.0 ነጥብና 3የግብ ዕዳ እንዲሁም ለተጋጣሚው የኢትዮጵያ መድን 3 ነጥብና 3 ንፁህ ጎል
3.በቀጣይ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች ከ200ኪ.ሜ ያላነሰ ከሜዳው ውጪ እንዲጫወት
4.ጉዳት የደረሰባቸውን የዕለቱ አርቢትር ኤፍሬም ደበሌ በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት ያወጡትን የህክምና ወጪ በደንቡ መሠረት እንዲተኩ
5.በአንቀጽ 80 ተ.ቁ 16 መሠረት የሀላባ ደጋፊዎችን በ30 ቀናት ስፖርታዊ ጨዋነትን እንዲያስተምሩ የወሰነ ሲሆን ከዚህ ውጪ የዕለቱ ኮሚሽነርና ዋና ዳኛ ያቀረቡትን ሪፖርት አስመልክቶ በሊግና በዳኞች ኮሚቴ በኩል እንዲታይ መወሰኑን ፌዴሬሽኑ በኢሜይል ከላከልን መረጃ ለማወቅ ተችላል።

ይሄንን የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ተከትሎ የሀላባ ከተማ ምላሽን ለማወቅ ያደረግነው ጥረት በበዓሉ ምክንያትና የክለቡ ሀላፊዎች ስልክ ሊሠራልን ባለመቻሉ ሃሳባቸውን በዘገባው ማካተት አልቻልንም።

” የውጭ ዜግነት ያለው ተጨዋች እንዳስፈረምን ተደርጎ በተወሰኑ የመገናኛ ብዙሃን የሚሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ ነው” የካ ክ/ከተማ እግርኳስ ቡድን አሰልጣኝ ባንቲ ጌታቸው

 

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ “ለ” ላይ የሚሳተፈው የካ ክፍለ ከተማ እግርኳስ ቡድን ሰሞኑን በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን የውጭ ተጨዋች አስፈረሙ በሚል የሚሰራጨውን ዜና የቡድኑ አሰልጣኝ አስተባብለዋል፡፡

አሰልጣኝ ባንቴ ጌታቸው በተለይም ለሀትሪክ ስፖርት እንደተናገሩት የውጭ ዜግነት ያለው ተጨዋች እንዳስፈረምን ተደርጎ በተወሰኑ የመገናኛ ብዙሃን የሚሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ እና ቡድናቸው የውጭ ተጨዋች የማስፈረም ፍላጎትም ሆነ ዕቅድ የሌላቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የካ ክፍለ ከተማ እግርኳስ ቡድን ከታች ያሉ ታዳጊዎች ላይ እየሰራ ያለና መልካም እና አበረታች ውጤቶች እየታዩ በመሆኑ በቀጣይም የማስቀጠል ስራዎች ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ መሆናቸውን ለሀትሪክ ስፖርት የገለፁት አሰልጣኝ ባንቴ ጌታቸው የውጭ ተጨዋቾች አለማስፈረማቸውንና ከቡድናቸው ጋር የውጭ ተጨዋቾች አለመኖሩንም አረጋግጠዋል፡፡

የካ ክ/ከተማ እግርኳስ ቡድን የውጭ ዜግነት ያለው ተጨዋች የማስፈረም ፍላጎትም ሆነ ዕቅድ እንደሌላቸው የገለፁት አሰልጣኝ ባንቴ ይሄን ሀሰተኛ ዜና ያሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን መጠየቅ ስላለባቸው ተጠያቂ የምናደርግበት ሂደት ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የካ ክፍለ ከተማ እግርኳስ ቡድን በከፍተኛ ሊግ ምድብ “ለ” ካደረጓቸው 6 ጨዋታዎች በ5ቱ ተሸንፈው፡በ1ጨዋታ የአቻ ውጤት ሲያስመዘግቡ ምንም ጨዋታ ሳያሸንፉ ፡2ጎል ሲያስቆጥሩ ፡13ጎሎች ተቆጥረውባቸው፡በ11 የግብ ዕዳ 1ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታ ኑሯቸው በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ሊፈርስ ከጫፍ ደርሷል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን በመካከለኛ እና ደቡብ ምዕራብ ምድብ ሐ ተቀላቅሎ የነበረው የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ እግር ኳስ ክለብ በበጀት እጥረት ምክንያት ሊፈርስ ከጫፍ መድረሱ እየተነገረ ይገኛል።
የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ክለብ ለቡድኑ ተጨዋቾች እስካሁን
የ3 ወር ደመወዝ እንዳልከፈላቸው እየተነገረ ሲሆን ክለቡና ተጨዋቾቹ በሚለያዩበት ሁኔታ ላይም ከእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ጋር ሁለቱ አካላቶች መነጋገራቸው እና የ3 ወር ደመወዛቸው ሊሰጣቸው እንደሆነም እየተነገረ ይገኛል።
የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ክለብ መፍረሱ ሙሉ ለሙሉ ከተረጋገጠ በህጉ መሰረት ማን ተክቶት ይወዳደራል የፌዴሬሽኑ ህግ የሚመልሰው ይሆናል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2010 ግምገማ እና በአዲስ ውድድር ፎርማት የሚጀመረው የ2011 እጣ ማውጣት ስነስርአት ተካሂዷል

ላለፋት ሥስት ዓመታት በሁለት ምድብ ተከፍሎ በአዲስ ስያሜና ፎርማት ሲካሄድ የቆየው ከፍተኛ ሊግ በማድረግ በሥስት ምድቦች ተከፍሎ እንደሚካሄድ ዛሬ ፌዴሬሽኑ ባካሄደው የከፍተኛ ሊግ የ2010 ግምገማ እና 2011 እጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ላይ አስታውቋል።

በአዲሱ ፎርማት መሰረት 32 የነበረው የተወዳዳሪ ቡድኖች ቁጥር ወደ 36 ከፍ ብሎ በሥስት ምድብ ማዕከላዊ ምድብ፣መካከለኛ እና ደቡብ ምስራቅ ምድብ እና መካከለኛ ደቡብ ምዕራብ ምድብ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።

የመጨረሻ ዕጣ ድልድሉ ይህ ሆኗል፣ ክለቦቹ በሶስት ምድብ ተከፍለዋል

=>ማዕከላዊ ምድብ

 1. ወልዲያ
 2. አውስኮድ
 3. አክሱም ከተማ
 4. ደሴ ከተማ
 5. ኢትዮ ኤሌክትሪክ
 6. ለገጣፎ ከተማ
 7. ቡራዩ ከተማ
 8. አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ
 9. ገላን ከተማ
 10. ወሎ ኮምቦልቻ
 11. ሰበታ ከተማ
 12. ፌደራል ፖሊስ

የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች

ፌደራል ፖሊስ ከ አማራ ውሃ ስራ
ኤሌክትሪክ ከ አክሱም
ሰበታ ከ ወሎኮምቦልቻ
አቃቂ ከ ወልዲያ
ገላን ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ
ቡራዩ ከተማ ከ ደሴ ከተማ

=>መካከለኛ እና ደቡብ ምስራቅ ምድብ

 1. የካ ክፍለ ከተማ
 2. ኢኮስኮ
 3. ዲላ ከተማ
 4. ሀላባ ከተማ
 5. ናሽናል ሲሚንቶ
 6. ወልቂጤ ከተማ
 7. ሀምበሪቾ ዱራሜ
 8. አርሲ ነጌሌ
 9. አዲስ አበባ ከተማ
 10. ኢትዮጵያ መድን
 11. ወላይታ ሶዶ
 12. ድሬዳዋ ፖሊስ

=>የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች

ኢኮስኮ ከ ሀምበሪቾ
ናሽናል ሲሚንት ከ ሀላባ
ዲላ ከተማ ከ ወላይታ ሶዶ
ድሬደዋ ፖሊስ ከ አዲስ አበባ ከተማ
ወልቂጤ ከ የካ ክፍለ ከተማ
አርሲ ነገሌ ከ ኢ/መድን

=>መካከለኛ እና ደቡብ ምዕራብ ምድብ

 1. ነገሌ ቦረና
 2. ቡታጅራ ከተማ
 3. ጅማ አባ ቡና
 4. ሀዲያ ሆሳዕና
 5. ነቀምት ከተማ
 6. ስልጤ ወራቤ
 7. ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ
 8. ካፋ ቡና
 9. ቤንች ማጂ ቡና
 10. አርባምንጭ ከተማ
 11. ሺንሺቾ ከተማ
 12. ሻሸመኔ ከተማ

=>የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች

ሻሸመኔ ከ ከፋ ቡና
ነገሌ ቦረና ከ ቡታጀራ
ነቀምት ከ ቤንች ማጂ
ሀዲያ ሆሳዕና ከ ስልጤ ወራቤ
ቢሾፍቱ ከተማ ከ ጅማአባቡና
ሼንሺቾ ከ አርባምንጭ ከተማ

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር የሚከናወኑ ውድድሮች እሚጀመሩበት ቀናት ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2011 ዓ.ም ከሚያካሂዳቸው አገር አቀፍ እና ኢንተርናሽናል ውድድሮች መካከል ከዚህ በታች የተገለፁትን ውድድሮች :-

v የኢትዮጵያ ሴቶች ኘሪሚየር ሊግ የ2011 ዓ.ም የሁለቱም ዲቪዚዮኖች ውድድር ህዳር 1 ቀን 2011 ዓ.ም የሚጀመር ይሆናል፡፡

v የኢትዮጵያ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በ2010 ዓ.ም የኘሪሚየር ሊግ ወንዶች አሸናፊ በሆነው በጅማ አባ ጅፋር ክለብ እና በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊ በሚሆነው ክለብ መካከል ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡

v የኢትዮጵያ ወንዶች ኘሪሚየር ሊግ የ2010 ዓ.ም የውድድር አፈፃፀም ግምገማ እና የ2011 ዓ.ም የዕጣ ማውጣት ሥነስርዓት መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

v የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ከኬንያ አቻው ጋር መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም በ10፡00 ሰዓት በባህር ዳር ስታዲየም እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ጨዋታ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የስታዲየም ለውጥ እንደተደረገ የሚገለጸው መረጃ የተሳሳተ ሲሆን ውድድሩ በባህር ዳር ስታዲየም የሚከናወን ይሆናል ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

በ ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር የሚካሄዱ ውድድሮች ቀናት ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2011 ዓ.ም ከሚያካሂዳቸው አገር አቀፍ እና ኢንተርናሽናል ውድድሮች መካከል ከዚህ በታች የተገለፁትን ውድድሮች :-

v የኢትዮጵያ ሴቶች ኘሪሚየር ሊግ የ2011 ዓ.ም የሁለቱም ዲቪዚዮኖች ውድድር ህዳር 1 ቀን 2011 ዓ.ም የሚጀመር ይሆናል፡፡

v የኢትዮጵያ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በ2010 ዓ.ም የኘሪሚየር ሊግ ወንዶች አሸናፊ በሆነው በጅማ አባ ጅፋር ክለብ እና በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊ በሚሆነው ክለብ መካከል ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡

v የኢትዮጵያ ወንዶች ኘሪሚየር ሊግ የ2010 ዓ.ም የውድድር አፈፃፀም ግምገማ እና የ2011 ዓ.ም የዕጣ ማውጣት ሥነስርዓት መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

v የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ከኬንያ አቻው ጋር መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም በ10፡00 ሰዓት በባህር ዳር ስታዲየም እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ጨዋታ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የስታዲየም ለውጥ እንደተደረገ የሚገለጸው መረጃ የተሳሳተ ሲሆን ውድድሩ በባህር ዳር ስታዲየም የሚከናወን ይሆናል ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ አዳዲስ የቦርድ አመራሮችን ሾመ

ኤሌክትሪክ በአዲስ መልክ እየተጠናከረ ነው…..
ኤሌክትሪክ (ኤልፓ) የቀደመው ቦርድ ለአዲሱ አመራር ርክክብ ካደረገ በሁዋላ በአሁን ሰአት በሁለት ካምፓኒ እየተመራ ነው፡፡ ከዩቲሊቲ እና ፓወር የተወጣጡ ስድስት የቦርድ አባላት ተመርጠው ስራቸውን ጀምረዋል፡፡
ከዩቲሊቲ
አቶ ጥላሁን ለገሰ
አቶ ጌቱ ተሾመ
አቶ ኢሳያስ ደንድር
ከፓወር
አቶ ህይወት እሸቱ
አቶ ብዙአየሁ አክሊሉ
አቶ ሰለሞን ሀ / ጊዬርጊስ ተመርጠዋል፡፡ አቶ ኢሳያስ ደንድር የቦርዱ ፕሬዝደንት ናቸው፡፡ ከነገ በስቲያ ሐሙስ ሜክሲኮ በሚገኘው የክለቡ የመሰብሰብያ አዳራሽ ከደጋፊዎች እና ከቀድሞው ተጨዋቾች ጋር የአንድ ቀን ውይይት ይደረጋል፡፡ ግልፅ የሆነ አሰራር እና ለሚዲያ ክፍት የሆነ አካሄድ እንደሚኖር ተገልፅዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኞች አቋርጠውት የነበረውን የመዳኘት ስራ በኘሪሜየር ሊጉ ተስተካካይና በሌሎች ውድድሮች ከነገ ጀምሮ ለመጀመር መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር በዳኞች ላይ የሚፈጸመው ጉዳት እየተባባሰ መጥቷል በሚል ቅሬታ ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ለሶስት ሳምንታት የትኛውንም ውድድር እንደማያጫዉቱ ባወጡት ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አስታውቀው ነበር።

ይሁን እንጂ ማህበሩ ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ባደረገው ውይይት “በማህበሩ አቋም መግለጫ የተነሱት ጥያቄዎች ከሞላ ጎደል ምላሽ በማግኘታቸው” ዳኞች ነገ ስራቸውን ለመጀመር መወሰናቸውን ገልጿል።

“ሁሉም የዳኞች ጥያቄ ባይመለሱም በውይይቱ ላይ በማህበሩ የቀረቡ ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ሳይሆን በጊዜ ሂደት በፌደሬሽኑ የሚመለሱ መሆናቸው ከመግባባት ላይ መደረሱን” ማህበሩ አስታውቋል።

ዳኞች ውድድር እንደማያካሄዱ በመግለጻቸው ምክንያት የ23 ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አልተካሄደም።

የዳኞች ማህበር ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ወደ ውድድር ለመመለስ 10 ቅድመ ሁኔታዎች እንዲተገበሩ አስቀምጦ ነበር። እነዚህም ከዚህ በታች የተጠቀሱት ናቸው።

በ2010 ዓ.ም የውድድር ዘመን የተጎዱ ዳኞች ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸው፣ ውድድሩን ከመጀመራችን በፊት በውድድር ደንቡ መሰረት የመድህን ዋስትና (ኢንሹራንስ) እንዲገባልን፣ ረዳት ዳኛ ሙስጠፋ መኪ በሃገር ውስጥም ሆነ ውጭ ሃገር ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ፤

ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመግባባት የዳኞች ጥበቃ እንዲደረግ፣ በወንዶች እና በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ለመዳኘት በሚደረግ ጉዞ አውሮፕላን የሚደርስበት ቦታ ሁሉ የአውሮፕላን ትራንስፓርት እንዲመቻች፣ የአልቢትር እያሱ ፈንቴን ጉዳይ ጨምሮ ፖሊስ ያወቃቸው የስርዓት አልበኝነትና የመብት ጥሰቶች ተገቢውን የህግ ፍርድ እንዲያገኙ እንዲደረግ፤

ፌዴሬሽኑ ለዳኞች እና ለታዛቢዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያመቻች፣ ማህበሩ ያለአግባብ ለጠቅላላ ጉባኤ ያወጣው ወጪ በፌዴሬሽኑ በህጋዊ ደረሰኝ አማካኝነት እንዲመለስ፣ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴዎቹ አሰራር በግልፅ እንዲጠየቅ እና ተገቢው የህግ ከለላ በሌለባቸው ስታዲየሞች ውድድር እንዳይካሄድ የሚሉ ናቸው።

” ስሜታችንን ለተጋሩ የስፖርት ቤተሠብ፣ ክለቦች ሚዲያው፣ የማህበራችን አባላትን አመሰግናለሁ። ውድድሩ ከነገ ጀምሮ መካሄድ እንደሚጀምር አረጋግጣለሁ”
አቶ ትግል ግዛው

” ክስተቱ ሁሉም እግር ኳሳዊ ጉዞ በስርአትና በመመርያ መሰረት መካሄድ እንዳለበት አሳይቶናል። እኛም ያቆምነው ሰው እንዳይሞት አስበን ነው።ጸጥታውን በጋራ እንጂ በፖሊስ ብቻ አይጠበቅም። አሁን ግን ማህበሩ ጋር ስምምነት በማድረጋችን ከነገ ጀምሮ ውድድሮች የሚቀጥሉ ይሆናል”
ፕሬዝዳንቱ ጁነይዲ ባሻ


በስብሰባው ላይ ከየክልላቸው ተወከለው ከመጡ ዳኞችና ከፌዴሬሽኑ አካላት የተለያዩ አሳቦች ቀርበዋል ፣ከቀረቡት ሀሳቦች መካከል :-

👉”እናንተ አንድ ብትሆኑ እኛም አንድ እንሆን ነበር።
ከመቶ 25ቱ አልተመለሰም።የፌዴሬሽኑ ሳይሆን የኛ ጉባኤ ነውና እንደፈለኩ እናገራለው።በሰውነታችሁ አከብራለው ሃሳባችሁን ግን አናከብርም።

እድሜ ለአማራ ቲቪ ዳኛውን ሲያሯሩጡ አይተናል እናንተ ባታሳዩኝ። ከከፍተኛ ሊግ ማንን እንደሚያልፍ ተሰርቶ አልቋል። እንደ አዲስ አበባ ተወካይነቴ አልቀበልም”
አርቢትር አሰፋ ደቦጭ


👉”ኮማንድ ፖስቱ የተቋቋመው ለሁላችን ደህንነት ነው
ፌዴሬሽን ደግሞ በአቶ ጁነዲን የሚመራ ዳኛ የሚመድብ ኮማንድ ፖስት አቋቁሟል ይሄ ደግሞ ተገቢ አይደለም ። ቦታ እስኪያገኝ ድረስ ታግሎ ቦታውን ሲይዝ ባለሙያ የሚገድል ሰው አለ ተው
ሊባል ይገባል። ”
የማህበሩ ም/ል ፕሬዝዳንት ሚካኤል አርአያ


👉”የቀይ ካርድ ውሳኔን የሚያሽሩት አቶ አበበ ገላጋይ ናቸው”
ዳኞች ውሳኔ ለመወሰን የተቀመጡላቸው መስፈርቶች አሉ። ለምሳሌ ተጫዋች በጨዋታ ላይ ሲያጠፋ የሚሰጠው የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ ወይም ቀይ ካርድ ዳኛው ሲሰጥ የተቀመጡ መስፈርቶች አሉን።

በዚሁ ቢጫ ካርድ ወይም ቀይ ካርድ እንሰጣለን። ሆኖም ይህ አሰራር እየተሻረ ነው። እንዲያውም አንዳንድ ተጨዋቾች ቀይ ካርድ ስንሰጣቸው ችግር የለውም አንተ ቀይ ካርድ ብትሰጠኝ ነገ የሚያነሳልኝ አካል አለ” እያሉ ያፌዙብናል ይሄ ፌዝ ነው። ”
ኢ/ር አርቢትር ዳዊት አሳምነው


👉 ” አንቺ ከቦክስ ተረፍሽ እንዴ እየተባልኩ ነው ያጫወትኩት ይሄ መታረም አለበት ይሄ የተኩስ ማቆም ስምምነት ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ነው”
አርቢትር ማርቆስ


👉”ፌዴሬሽኑ 1+1=2 ነው እያለ አይደለም 1+1=2 ሊሆን ይችላል እያለን ነው። ይሄ ልክ አይደለም እኛ የምንፈልገው ድርድር አይደለም ጥያቄውን መልሱልን”
ኢ/ር ረዳት ዳኛ ክንዴ ሙሴ


👉 ” ይሄ መንግስታችን ነው ስፖርቱ የልማቱ አንዱ አካል ነው ያለው።መንግስትና ማህበራችን አድማ አይፈልጉም ሴትና ወንድ እኩል ነው እየተባለ መለያየት ተገቢ አይደለም”
የማህበሩ ፕሬዝዳንት ትግል ግዛው


የኢትዮጵያ ዳኞችና ፌዴሬሽኑ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተክትሎ ኘሪሚየር ሊጉ በተስተካካይ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ሲቀጥል ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት መርሐ ግብሮቹ እሚከናወኑ ይሆናል።
 

የ2010 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ተሰተካካይ ጨዋታዎች 

                

 

ሰኞ ግንቦት 6 ቀን 2010

 09:00
ወልዋሎ አዲግራት ዩ.
    ?-?
መቐለ ከተማ

በሽረ ስታዲየም ቀሪ 45 ደቂቃ


 09:00
 አዳማ ከተማ
   ?-?
 ወላይታ ድቻ

 10:00
 ቅዱስ ጊዮርጊስ
    ?-?
ኢትዮ-ኤሌክትሪክ

አርብ ግንቦት 10 ቀን 2010

 09:00
መቐለ ከተማ
   ?-?
ቅዱስ ጊዮርጊስ

 09:00
ደሬዳዋ ከተማ
    ?-?
ወላይታ ድቻ