Category: የዝውውር ዜናዎች

ጋቶች ፓኖም እና ኤልጉና ተለያዩ

ባለፈው ዓመት መቐለ 70 እንደርታን በመልቀቅ የግብፁ አዲስ ያደገውን ኤልጉናን የተቀላቀለው ጋቶች ፓኖም ከአንድ ዓመት ቆይታ በኃላ ከክለቡ ጋር ተለያይቷል።

ኤልጉና ላለመውረድ ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ የራሱን ድርሻ የተጫወተው ግዙፋ አማካይ ጋቶች ከክለቡ ጋር ቀሪ የሁለት ዓመት ኮንትራት እያለለው ክለቡን በስምምነት ሊለቅ ችሏል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣መቐለ 70 እንደርታ፣አንዚ ማካቻካላ እና ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እማካይ ጋቶች ፓኖም በተጠናቀቀው የግብፅ ሊግ እንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል።የጋቶች ቀጣይ ማረፍያ ክለብ ከኢትዮጵያ ውጪ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

ስሑል ሽረ አክሊሉ ዋለልኝን ከጅማ አባጅፋር አስፈረመ

 

በክረምቱ የዝውውር መስኮት በንቃት መሳተፍ የጀመረው ስሑል ሽረ የጅማ እባጅፋር እማካዩን አክሊሉ ዋለልኝን በእንድ ዓመት ውል እስፈርሟል።በሳምሶን አየለ ሚመሩት ስሑል ሽረዎች እክሊሉን ማስፈራማቸው ተከትሎ የክረምቱ ፈራሚዎቻቸው ቁጥር 4 አድርሰዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከተቀያሪ ወንበር እየተነሳ ለጅማ የተጫወተው አክሊሉ ኳስን መሰረት እድርጎ ለሚጫወተው የስሑል ሽሬ ቡድን ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪ ስሑል ሽረዎች የረመዳን ናስር፣አብዱሰላም አማን፣ዲሜጥሮስ ወልደስላሴ እና ደሳለኝ ደባሽ ውልን ማራዘም ችሏል።

ኢትዮጵያ ቡና የሁለት ወሳኝ ተጨዋቾቹን ውል እራዝሟል

 

 

ካሳዬ እራጌን በእሰልጣኝነት የቀጠሩት ኢትዮጵያ ቡና የሁለት ወሳኝ ተጨዋቾቻቸውን ውል እራዝመዋል።ባሳለፍነው የውድድር ዓመት 11 ጎሎችን ያስቆጠረው ተስፈኛው ወጣት እቡበከር ነስሩ ከእናት ክለቡ ጋር ለቀጣይ ዓመት ለመቀጠል ተስማምቷል።

በተመሳሳይ በተለያዩ ቦታዎች በመጫወት ሚታወቀው እያሱ ታምሩ ሌላው ውሉን ያራዘመ ተጨዋች ነው።በፓፓዲች እና በጎሜዝ ስር በተለያዩ ቦታዎች በመጫወት ጥሩ ብቃቱን ያሳየው እያሱ በቀጣይ ዓመት በካሳዬ እራጌ ቡድን ቁልፍ ቦታ ሊሰጠው እንደሚችል ይገመታል።

ኢትዮጵያ ቡና በሚቀጥሉት ቀናቶች ውስጥ የነባር ተጨዋቾቹ ውል ማራዘም በተጨማሪም የእዳዲስ ተጨዋች ዝውውር ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የ2012 የተጨዋቾች ዝውውር በኢንተርሚደሪ /ሶስተኛ ወገን/ ብቻ የሚስተናገድ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዓለም አቀፋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን /ፊፋ/ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ተጨዋቾች ዝውውርን አስመልክቶ ባወጣው መመሪያ መሠረት በቀጣይ በ2012 ዓ.ም ፌዴሬሽኑ በመሚመራቸው ውድድሩሮች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ተጨዋቾች በኢንተርሚደሪ /በሶስተኛ ወገን / ብቻ ምዝገባ እንደሚካሄድ አስታወቀ፡፡

ቀደም ሲል ይህንኑ ሥራ ለመስራት የሚያስችለውን የኢንተርሚደሪ /የሶስተኛ ወገን/ ፈቃድ ለሚፈልጉ በሙሉ
በፌዴሬሽኑ መስፈርት መሠረት የፈቃድ መውሰጃ ፈተና በመስጠት 75 የሚሆኑት ተመዝጋቢዎች የመመዘኛ ፈተናውን ማለፋቸውን የአረጋገጡ በመሆናቸው ፈቃዱን ለመውሰድ የፈቃድ ክፍያ እና የኢንሹራንስ ክፍያ በመፈፀም ቅድመ ዝግጅታቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ ፡፡

ከሐምሌ 25 /2011 እስከ ጥቅምት 12 /2012 እና ከጥር 1 እስከ ጥር 30 ቀን 2012 ዓ.ም በአንደኛ እና በሁለተኛ ዙር የሚከናወኑት የ2012 ዓ.ም የተጫዋቾች ምዝገባን አስመልክቶ ለኘሪሚየር ሊግ ክለቦች፣ ለከፍተኛ እና ለአንደኛ ሊግ ክለቦች ዛሬ ሐምሌ 18/ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ከፌዴሬሽኑ ሕጋዊ የሦስተኛ ወገን ፈቃድ በተሰጣቸው ህጋዊ አካላት ብቻ ማስመዝገብ እንደሚገባቸው እና በፌዴሬሽኑ ህጋዊ የሆኑት አካላትም ስም ዝርዝር በደብዳቤ እንደሚላክላቸው የተገለፀ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፀሐፊ የሆኑት አቶ ሚሊዮን መኮንን ገልፀዋል፡፡
አክለውም “ማንኛውም የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ተጫዋች በተገለፁት የምዝገባ ጊዜያት ለመመዝገብ በሚቀርብበት ወቅት ከፌዴሬሽኑ የሶስተኛ ወገን ፈቃድ ባላቸው እና ሕጋዊ በሆኑት አካላት ብቻ መመዝገብ እንደሚገባቸው” አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም “ይህ አይነቱ አሰራር ለአገራችን እግር ኳስ የራሱ የሆነ በጎ ገጽታ ያለው ሲሆን ለክለቦቻችን በወቅቱ የሚፈጠሩትን የተለያዩ የምዝገባ ስህተቶች በአፋጣኝ ለመፍታት፣ ለፌዴሬሽኑ የገቢ ምንጭ እንዲያገኝ የማስቻል እና ለተጨዋቾች በተደጋጋሚ የሚከሰትን ክስ እና እንግልት ለመቀነስ እንዲሁም የሦስተኛ ወገን ፈቃድ ላላቸው የሥራ እድል መፍጠርን የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪም የዓለም አቀፋ የእግር ኳስን አሠራር ሂደት የሚከተለውን ዘመናዊ ሥርዓት በአገራችን መተግበሩ በፊፋ እና በካፍ መልካም ገጽታ ለማግኘት የራሱ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ያደርጋል በማለት” አስረድተዋል ፡፡

Via- theeff official page

ፈረሰኞቹ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ቀጠሩ

ከፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ማኑኤል ቫዝ ፒንቶ ጋር የአንድ ዓመት ቀሪ ግዜ እያላቸው የተለያዩት ፈረሰኞቹ የ62 ዓመቱን ስቴዋርት ጆን ሀል ማስፈረማቸው የክለቡ የፋዊ ገፅ አስታውቋል ::

“አሰልጣኙ በቀደመው ጊዜ የበርሚንግሃም ሲቲ እግር ኳስ አካዳሚ ዳይሬክተር እና የተተኪ ቡድኑ እና ከ18 ዓመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ የነበሩ ሲሆን በርሚግንሐምን ለቀው የህንዱን ፑኔ ሲቲን ከ2007-09 እ.ኤ.አ አሰልጥነዋል፡፡ በ2009 መጨረሻ ሴንት ቪንሰንት እና ግሬናዲያንስ ዋናውን እና ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት በመያዝ ከ20 ዓመት በታች ቡድኑን በኮንካካፍ ማጣሪያ ቡድኑን ከምድቡ አንደኛ በማድረግ ማሰለፍ ችለዋል፡፡”

አሰልጣኙ ከክለቡ ገፅ ጋር ቆይታ አድርገዋል

“በባንግላዴሽ ቆይታዬ ጥሩ ተከፋይ አሰልጣኝ ነበርኩ በሊጉም ዛሬ እዚህ አስክመጣ ድረስ በ18 ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈትን አላስተናገድኩም፡፡ ነገር ግን ለ8 ዓመታት በምስራቅ አፍሪካ በተለያዩ ክለብና ብሔራዊ ቡድኖች ስቆይ ቅዱስ ጊዮርጊስን ማሰልጠን እፈልግ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ከክለቡ ጥያቄ ሲቀርብልኝ ባሳልፈው የምፀፀትበት ውሳኔ ይሆናል ብዬ የልቀቁን ጥያቄ ለክለቤ አቀረብኩኝ እነርሱም መልቀቅ ባይፈልጉም ጥያቄን ተቀብለውኛል፡፡

አዛም (ታንዛኒያ) እያለሁ ብዙ ድሎችን እና ውጤቶችም ማሳካት ብችልም ቡድኔ ደጋፊ አልነበረውም፡፡ አሁን ግን ወደ በርካታ ደጋፊዎች ባለቤት ወደሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ መጥቻለሁ በዚህም ደስተኛ ነኝ”፡፡

ከሴንት ቪንሰንት እና ግሬናዲያንስ ወደ ቀድሞ ቡድናቸው ተመልሰው የህንዱ ፑኔ ሲቲ በውድድር ዓመቱ ምንም ግብ ሳይቆጠርበት ቡድኑን ወደ ዋናው ፕሪሚየር ሊግ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሳደግ ችለዋል፡፡ በ2010 እ.ኤ.አ የዘንዚባር ብሄራዊ ቡድን አለቃ ሆነው ተሾሙ፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ታንዛኒያ ላይ ለተካሄደው ለምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ውድድር ይዞ በመቅረብ በግማሽ ፍፃሜ በኡጋንዳ በመለያ ምት ተሸንፈው ከውድድር ወጥተዋል፡፡ አሰልጣኙ ዛንዚባርን ለቀው የታንዛኒያውን አዛምን በመያዝ ቡድኑን በቮዳኮም ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሆኖ እንዲያጠናቅቅና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የማፓንዱዚ ዋንጫን እንዲያሸኝፍ አድረገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአዛም ቆይታቸው የፍንድሺፕ ዋንጫ ፍፃሜ ተፋላሚ እንዲሆንና በሴካፋ የክለቦች ውድድር ቡድኑ በመጀመሪያ ተሳትፎው ለፍፃሜ እንዲደርስ አድርገውታል፡፡

ከ2 ዓመት ቆይታ በኋላ ከቦርዱ ጋር ባለመስማማታቸው አዛምን ለቀው በ12 መስከረም 2012 እ.ኤ.አ የኬንያውን የተስካር ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለብ ሶፋፓካን ተቀላቅለዋል፡፡ ነገር ግን የሶፋፓካ ቆይታቸው ከ7 ሳምንታት አልዘለለም ተመልሰው አዛምን መያዝ ችለዋል፡፡ አሰልጣኙ አዲስ ቡድን በመገንባት ቡድኑ በሊጉ ቀዳሚና እስከ ግማሽ የውድድር ዓመት ምንም ሽንፈት ያላጋጠመው ቡድን መስራት ችለው የነበረ ቢሆንም በ8/ጠቅምት/2013 እ.ኤ.አ ሌላኛውን የታንዛኒያ ክለብ ሲምቢዮን ፓውርን (ዳሬ ሰላም የሚገኘውን የሰንድርላንድ አካዳሚን መቀላቀል ችለዋል፡፡ ልክ እንደ አንድ የስራ ድርሻ የታንዛኒያን ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖችን አሰልጥነዋል፡፡

በድጋሚ ወደ አዛም ተመልሰው የሴካፋን የክለቦች ዋንጫ (ካጋሚ ካፕ) ማሸነፍ ችለዋል፡፡ ከአዛም በ2016 ወደ ኬንያው ኤ.ሲ ሌዎፓርድ ለ2 ዓመት በሚቆ የውል ስምምነት ቢቀላቀሉም ከ1 ዓመት በላይ መቆት አልቻሉም፡፡ ከ2018 ጀምሮ የባንግላዴሹን ሳይፍ ስፖርቲንግ ክለብ በማሰልጠን ለ18 ተከታታይ ጨዋታዎች ያለሽንፈት መጓዝ ችለዋል፡፡
አሰልጣኙ የዩኤፋ የአሰልጣኛነትና የአሰልጣኞች አሰልጣኝነት ላይሰንስ ያላቸው ናቸው።

አሰልጣኙ በነገው ዕለት ስራ የሚጀምሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ዋና ፀሀፊ፣ የቡድን መሪ እና ኮቺንግ ስታፍ ጋር ትውውቅ የክለቡ የፋዊ ገፅ አስታውቋል ።”

source -saint Georg AS

ብሩክ አየለ ወደ ደቡብ ፓሊስ አምርቷል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ቆይታው ላይ ለሀዋሳ ከተማ ለሲዳማ ቡና ለኤሌክትሪክ እና ለወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ እንደዚሁም ደግሞ ለባህር ዳር እና በታዳጊ እና ወጣትነት ዕድሜው ደግሞ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድኖች ተጫውቶ ያሳለፈው የአማካይ ስፍራ ተጨዋቹ ብሩክ አየለ የፕሪሚየር ሊጉን ከዓመታት በኃላ ዘንድሮ በድጋሚ ለተቀላቀለው ደቡብ ፖሊስ ለመጫወት ለአንድ ዓመት ፊርማውን አኑሯል።

ባሳለፈው የእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኑ የመሀል ሜዳው ላይ በሚያሳየው አበረታች ብቃት እና አጨዋወት የብዙዎችን ትኩረት ይስብ የነበረው ይኸው ተጨዋች ለደቡብ ፖሊስ መፈረሙ ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ቡና አሰልጥኖት ካለፈው የቀድሞ አሰልጣኙ ዘላለም ሽፈራው /ሞውሪኖ/ ጋር ዳግም እንዲገናኝ ያስቻለው ሲሆን ተጨዋቹ በወልዋሎ ሳለ ደርሶበት ከነበረው ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ድኖ በመምጣቱ ለአዲሱ ክለቡ በሙከራ ከታየ በኋላ እንደፈረመም ታውቋል።
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ዘንድሮ የተቀላቀለው ደቡብ ፖሊስ ከብሩክ ውጪ ሰሞኑን ሙልዓለም ረጋሳ እና አበባው ቡታቆን ማስፈረሙ ይታወሳል።

ደደቢት አራት ተጨዋቾችን አስፈረመ

ወጣት ተጨዋቾች ላይ ትኩረት አድርገው እየተንቀሳቀሱ ሚገኙት ደደቢቶች የአራት ተጨዋቾችን ፊርማ አጠናቀዋል።በክረምቱ 8 ተጨዋቾችን ያስፈረመው ደደቢት አሌክሳንደር ዓወት፣ሐዱሽ በርሀ፣ረሺድ ማታውሲ ና ሙሉጌታ ብርሃነ(ሻኩር) አስፈርሟል።

በትግራይ ዋንጫ የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሽልማትን ያገኘው ረሺድ ማታውሲ ከክለቡ ጋር የተሳካ ሙከራ ጊዜ ማሳለፋን ተከትሎ ሰመያዊዮቹን በቀዋሚነት መቀላቀል ችሏል።በተጨማሪ የደደቢት ተስፋ ቡድን ውጤት የሆነው ግብ ጠባቂው ሐዱሽ በርሄ ከትግራይ ውሃ ስራዎች ደደቢትን በመቀላቀል የረሺድ ጥሩ ምትክ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

በ2009 ከሃዋሳ ከተማ 20 ዓመት በታች ቡድን ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግን በኮከብ ጎል ኣግቢነት ያጠናቀቀው ወጣት አጥቂው አሌክሳንደር ዓወት ከቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ደደቢትን ሲቀላቀል በተመሳሳይ ደደቢቶች በኣጥቂ ቦታ ያላቸውን አማራጭ ለማስፋት ሙሉጌታ ብርሃነ(ቻኩር) ማስፈረም ችለዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ናይጄሪያዊ ተጨዋች አስፈርሟል

ናይጄሪያዊው የ26 ዓመት አጥቂ አሌክስ ኦሮትማል የኬኒያውን ኤኤፍሲ ሊዮፓርድ ለቆ በዛሬው ዕለት ለሁለት ዓመት በሚቆይ የውል ስምምነት ቅዱስ ጊዮርጊስን ተቀላቅሏል።

ክለቡ ትላንትና ከቶጎ ከጋና እና ከኬንያ ሶስት ተጫዋቾችን ያስፈረሙት ጊዮርጊሶች ዛሬ ደግሞ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈርሟል። አሌክስ ኦርትማል ለሳምንታት ከፈረሰኞቹ ጋር ደብረዘይት በሚገኘው የይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ውስጥ ሙከራውን ሲያደርግ ቆይቶ ዛሬ በ1.5 ሚሊዮን የዝውውር ዋጋ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተቀላቅሏል።

ፎቶ © የቅዱስጊዮርጊስ የፋዊ ገፅ

ምንያህል ይመር ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቀለ

በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ እየተመራ 12ተጨዋቾችን ያስፈረመው ድሬዳዋ ከተማ ምንያህል ይመርን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የክረምቱ 13ኛ ፈራሚውን አድርጓል።ባሳለፈነው ዓመት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያሳለፈው የቀድሞው የወልዲያ እና የዳሽን ቢራ ተጨዋች በይፋ አስፈርሟል።

ዮናታን ከበደ ፤ሀይሉ ነጋሽ፣ምንተስኖት የግሌን ጨምሮ 9 ተጨዋቾችን ያስፈረመው ድሬዳዋ ከተማ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት በትግራይ የፍፃሜ ዋንጫ ጨዋታ በእንግዳነት የተጋበዘው ድሬዳዋ ከተማ በመቐለ 70 እንደርታ ተሸንፎ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ እሚታወስ ነው ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 የውጪ ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል

የውጪ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሊዘጋ ሁለት ቀናት እየቀሩት የውጪ ተጫዋቾችን ወደ ክለቦቻቸው ያመጡ የኘሪሜየር ሊግ እና የከፍተኛ ሊግ ቡድኖች አለማቀፉን የዝውውር ቴክኖሎጂ ሲስተም (TMS)ን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት የማጠናቀቅ ስራ ላይ ተጠምደዋል።

ፈረሰኞቹም በዛሬው እለት የኬኒያ ብሔራዊ ቡድን እና የተስካር ግብ ተጠባቂ የሆነውን የ31 ዓመቱ ፖትሪክ ማታሲን የመሀል እና የቀኝ መስመር አጥቂ የሆነውን የ26 ዓመቱ የቶጎ ብሄራዊ ብድን እና የቶጎ ፖርት ክለብ ተጫዋች የሆነውን ኢሲፋ ቡሩሀና እና ጋናዊው የ23 ዓመት የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነውን ካሲው ታይተስ ግሎቨርን አስፈርሟል።

ፎቶ © የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ይፋዊ ገፅ